#የማለዳ_ቃል 🌤 መጽሐፈ ምሳሌ 3 ³ ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው። ⁴ በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ። መልካም ቀን ! ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
Открыть в TelegramПосты канала CHRIST TUBE - ETH🇪🇹
Переслано из Hesed (חֶסֶד)
COMPOUND OLD TESTAMENT NAMES 1. El Elyon - "The most high" (Gen 14:22). 2. El Olam - "The everlasting God" (Gen 21:33). 3. El Shaddai -"The Almighty God" (Gen 17:1) 4. Yahweh Jireh - The Lord provides (Gen 22:14). 5. Yahweh Nissi - The Lord is my Banner (Ex 17:15). 6. Yahweh Shalom - The Lord is peace (Judg 6:24). 7. Yahweh Sabbaoth -"The LORD of hosts" (1 Sa 1:3). 8. Yahweh Maccaddeshcem - The Lord thy Sanctifier (Ex 31:13). 9. Yahweh Roi - "The LORD . . . My shepherd" (Ps 23: 1). 10. Yahweh Tsidkenu - The Lord our Righteousness (Jer 23:6). 11. Yahweh Shammah —The LORD is there" (Eze 48: 35). 12. Yahweh Elohim Israel - "The IORD God of Israel" (Judg 5:3). 13. Qadosh Israel - "The Holy One of Israel" (Is 1:4).
Открыть в Telegram#Spiritual_speech 🗣 ❞Jesus will never let you down!❞ ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው ➥ @CHRIST_TUBE ➥@CHRISTFAMILY ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
Открыть в Telegram❤️ CHRISTIAN RELATIONSHIP | ክርስቲያናዊ ግንኙነት 🕊️ ዓላማችን ፍቅርን በስሜት ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል ላይ መመሥረት ነው። ይህ ገጽ ክርስቶስን በመሃል ያደረገ ግንኙነት፣ ንጹህ ፍቅር፣ ታማኝነት፣ መከባበር፣ የጸሎት ሕይወት፣ የጋብቻ ዝግጅትና መንፈሳዊ እድገት ላይ የሚያተኩር ነው። እውነተኛ ፍቅር አንዱ ሌላውን ብቻ የሚያገኝበት ሳይሆን፣ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚያገኙበት ጉዞ ነው። እግዚአብሔር በመሃል ያለበት ፍቅር የተሻለ መሠረት አለው! ❤️ 📖 “ሶስት ክር ያለው ገመድ በቀላሉ አይበጠስም።” — መክብብ 4፥12 ለ ክርስቲያኖች ስለ Relationship መወያያ እና መተዋወቂያ የሚሆን ግሩፕ ነው Join በሉ! 👇👇 https://t.me/+4Q9Pvs49jpNmMGQ0 https://t.me/+4Q9Pvs49jpNmMGQ0
Открыть в Telegramስላም ለእናንተ... 🙌 ለ ክርስቲያኖች ስለ Relationship መወያያ እና መተዋወቂያ የሚሆን ግሩፕ ነው Join በሉ! 👇👇 https://t.me/+4Q9Pvs49jpNmMGQ0 https://t.me/+4Q9Pvs49jpNmMGQ0
Открыть в TelegramПереслано из Hesed (חֶסֶד)
መዝሙረ ዳዊት 19:14 ¹⁴ አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።
Открыть в Telegramተወዳጆቼ፣ እኛ አሁን መልስ እንፈልጋለን፤ እግዚአብሔር ግን ከመልሱ በላይ የሆነውን ዓላማ ያውቃል። ስለዚህ በመዘግየቱ ተስፋ አንቁረጥ በመዘግየት ውስጥ ትልቅ የከበረ ተስፋ አለ! መልካም ምሽት ! ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
Открыть в TelegramПереслано из Hesed (חֶסֶד)
ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት ፤ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ ተጠርቻለሁና፣ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ። ኤርምያስ 15:16
Открыть в TelegramПереслано из Hesed (חֶסֶד)
ገድለ አብርሃም አብርሃም በእውነት የእምነትና የመታዘዝ አባት ነው። መታዘዙም ከንቱ አልነበረም። ለአብርሃም እውነተኛው ርስት ምን ነበር? ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ወዳጅነት ካልሆነ። የአብርሃም ሕይወት እጅግ አስደናቂ ነው። ከሁሉ አስቀድሞ፣ መጽሐፍ ስለ አብርሃም እንድናስተውል የሚያደርገን አንድ ነገር፣ እግዚአብሔር ለእርሱ የተገለጠው በመጀመሪያ በሜሶጶጣሚያ፣ በከለዳውያን ኡር ሳለ መሆኑ ነው። ይህም ወደ ካራን ከመምጣቱ በፊት ነበር (ሐዋ. 7፡2)። ካራን እስከሚደርስ ድረስ እግዚአብሔር አብርሃም የሚወርሰውን ምድር በግልጽ አልነገረውም፤ ከነዓንም ርስቱ እንደምትሆን አልገለጠለትም። ካራን ከደረሰ በኋላ ነው ወደ ከነዓን እንዲሄድ ያዘዘው። የእግዚአብሔር ጥሪ ምን ነበር? «ከአገርህና ከወገንህ ከአባትህም ቤት ውጣ፤ ወደማሳይህም ምድር ሂድ።» አጭርና ግልጽ ትእዛዝ! ግን ወዴት? የት እንደሚሄድ አልተነገረውም። ወዴት እንደሚኬድ ሳይታወቅ ቤትንና ንብረትን ጠቅልሎ መውጣት ምን ያህል ከባድ ይሆን? ዝም ብሎ መሄድ ! ወዴት? እኔንጃ! እርሱ ወደሚመራን ብቻ። አብርሃም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ ታምኖ ወደ ካራን፣ ከዚያም ወደ ከነዓን መጣ። ሆኖም ወደ ከነዓን በደረሰ ጊዜ፣ እስጢፋኖስ እንደሚነግረን፣ «እግዚአብሔር የእግር መረገጫ ስንኳ ርስት አልሰጠውም» (ሐዋ. 7፡5)። ይህን ሳነብ የዘመናችን ሰው ይህን «Scam» ሊል እንደሚችል አሰብኩ ። ጌታ ሆይ፣ ታዲያ ርስቱ የታለ? 😁 ነገሩ ግን ይህ ብቻ አልነበረም። በዚያ ዘመን ከአብራኩ የወጣ ልጅ ባልኖረበት ሁኔታ፣ እግዚአብሔር ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለሚመጣው ዘሩ ይህንን ምድር ርስት አድርጎ እንደሚሰጠው ተስፋ ሰጠው። እንግዲህ ርስቱ የታሰበው ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ለዘሩም ነበር ማለት ነው። እንደምናውቀው፣ አብርሃም ለሚስቱ የመቃብር ስፍራ የሚሆነውን ዋሻ እስከገዛበት ጊዜ ድረስ የራሱ የሆነ ትንሽ መሬት እንኳን አልነበረውም። ዘሮቹ አንድ ቀን ምድሪቱን እንደሚወርሱ ማወቁ ለአብርሃም የመጽናት ምክንያት ነበር። ጉዳዩ ግን የዋዛ አልነበረም። መጠበቅ ቀላል አደለም፤ለርሱና ለሳራ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ለረጅም ጊዜ ልጅ አልነበረውም። አብርሃም መጨነቅ ጀመረ። እርሱም እንደእኛው ሰው ነውና። «እሺ፣ ርስት እንደምትሰጠኝ አምናለሁ፤ ይህም በዘሬ እንዲሆን አውቃለው። ግን ኤሌዔዘር ሊወርሰኝ ነው?» የሚል ሐሳብ ውስጡ አለ። እግዚያብሔርም የአብራኩ ክፋይ እንደሚወርሰው ያፀናለታል። የተጠበቀው ልጅ መጣ፤ ለሳራ ያሳቃት ሆነ፤ ለቤታቸውም ይስሐቅ ሆነላቸው። እኔም የአብርሃም ሕይወት የተፈፀመ የተፈፀመ መሰለኝ ። «ተመስገን ቀላል አልነበረም፤ ሆኖም ሩጫዬን ጨርሻለሁ። ባሪያህን አሰናብት» እሚል መሰለኝ። ሆኖም እግዚአብሔር ግን ሌላ አለው። ወገን ስለ «እግዚአብሔር ሌላ አለው» ሳስብ ቤት ባርኮኝ ከነበረ፣ ትዳር አለው፣ መኪና አለው፣ PhD አለው የሚሉትን ብቻ ብቻ ነበር የምጠብቀው 😊። እግዚአብሔር ግን ይሄም አለው! እግዚአብሔር የሚወደውን አንድ ልጁን እንዲሠዋ ጠየቀው። ይህ ልጅ አብርሃም ይህንን ሁሉ ዋጋ የከፈለበት ነው፣ በብዙ መጠበቅና በብዙ ተስፋ የተቀበለው ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ወዳጅነትም በዚህ ተስፋ ላይ የተመሠረተ የሚመስል ነው። ሆኖም የአብርሃም ቀጣይ እርምጃ እምነቱ በእግዚአብሔር ላይ እንጂ በተቀበለው በረከት ላይ እንዳልተመሠረተ አሳየን አብርሃም ከራሱ ሕይወት ጭምር ያለውን ሁሉ ቢሰጥ ምናልባት ይቀለው ይሆን ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን አብርሃም ማልዶ ተነሳ፣ የሚያስፈልገውንም አዘጋጅቶ ለእግዚአብሔር ያለውን ፍቅርና እምነት በተግባር ወዳሳየበት ተራራ በመውጣት ታላቅ ገድል ሠራ የአብርሃምን እምነት የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ግሩም አድርጎ ነው የሚያቀርበው። ከተናገራቸው ብዙ ነገሮች ውስጥ ሁለቱን እንሆ «ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠር ከዚህ ከአንድ ሰው፣ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ተቈጥሮ የማያልቅ ዘር ተገኘ።» (ዕብ. 11፡12) አብርሃም ከዚህ ውስጥ ነው ሕይወትን የጠበቀው ለእኔ ግን የአብርሃም እምነት በከፍታ የተገለጠው በዚህ ሁለተኛው ሐሳብ ነው ባይ ነኝ «እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቦአል።» (ዕብ. 11፡19) ላብራራው አልችልም የአብርሃም መንገድ አላበቃም። እግዚአብሔር ዘሮቹ ለአራት መቶ ዓመታት በግብፅ እንደሚቆዩ፣ በባርነትና በግዞት እንደሚሰቃዩ ነገረው። ከዚያ በኋላ ተመልሰው ምድሪቱን እንደሚወርሱም አሳወቀው (ሐዋ. 7፡6) በድጋሚ ለእኔና ለቢጤዎቼ ከእግዚአብሔር ጊዜና አሰራር ይልቅ የዘመኑ እሽቅድድምና አቋራጭ ፍለጋ ለሚያናውዘን «What a scam» የሚያስብለን ነው😁 ሆኖም አብርሃም «ምነው አሁንስ በዛ» ሳይል፣ ሳይማረር፣ ተስፋውንም ሳይጠራጠር፣ በሕይወቱ ውስጥ እግዚአብሔር የሚሠራውን በእምነት የሚጠብቅ ሰው ነበር። በታማኝነት እንደ እንግዳና መጻተኛ ሆኖ አለፈ። በጣም መሳጩ ታሪክ ግን ከዚህ በኋላ ያለው ነው፦ እግዚአብሔር ለዘሩ ርስት አድርጎ ሊሰጣቸው ያዘጋጃት ምድር ዝም ብላ የምትወረስ አልነበረችም። በእምነት የአብርሃም ልጆች የሆኑት፣ እንደ ካሌብና ኢያሱ ያሉት እንጂ፣ በሥጋ የአብርሃም ዘር መሆን ብቻ ርስቱን ለመውረስ አያበቃም። እንደምናውቀው፣ ለአብርሃም የተሰጠው ተስፋ እንዲፈጸም ዘሮቹ በምድረ በዳ መሻገር ነበረባቸው። ሆኖም የበረሃው ጉዞ ሕዝቡን የፈተነ ነበር። ተስፋይቱ ከነዓን ደግሞ በኃያላን ነገሥታት፣ በግዙፍ ሰዎችና በታላቅ ስምና ክብር ባላቸው መንግሥታት ተይዛ ነበር። እነርሱም ተሰነካክለው በምድረበዳ ቀሩ። እንጠቅለለው፤ ይህ ሁሉ የሚያሳየን እምነት ተስፋን በሰጠው እግዚአብሔር ላይ የሚመሠረት መሆኑን ነው። አብርሃም የእግዚአብሔርን ቃል አምኖ፣ ተስፋውን በራሱ ጊዜ እንዲፈጽም ታግሦ ጠበቀ። ዘሮቹ ግን ከሰሙት የእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የልባቸው ምኞትና ከምድራዊው ነገር ጋር የተጣበቀው አስተሳሰባቸው በምድረ በዳ አስቀራቸው። እንደ አብርሃም ያሉት ግን በዚህ ምድር ሲኖሩ መጻተኞችና እንግዶች መሆናቸውን ተገንዝበው፣ ከምድራዊውና ከሚያልፈው ነገር የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር እየናፈቁ ይኖራሉ። በመጨረሻም ወደ ርስታቸው፣ ወደ እግዚአብሔር ከተማ ይገባሉ። 🙏
Открыть в TelegramПереслано из Fellowship with God
kingdom sound የዝማሬ ህብረት የተዘመሩ አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ዝማሬዎችን ለማግኘት ከታች ያለውን button ተጭነው ይቀላቀሉ
Открыть в TelegramПереслано из Hesed (חֶסֶד)
በጌተ ሰማኒ ጌታ ኢየሱስ ቃቶ በቀራንዮ ላይ ከጠላት ተዋግቶ በጐቹን አድኗል ነፍሱን ለሞት ሰጥቶ እንዲህ ያለ ፍቅር ከየት ይገኛል ከቶ መልካም እረኛ ስለ በጐቹ ነፍሱን ያኖራል በእርሱ የሚገባ በእርሱም የሚሰማራ ለዘለዓለም ይድናል ዘለዓለም ይኖራል መንጋውን ሊበትን እረኛውን መቶ ሰይጣን ቢጣጣርም እጅግ ተበራቶ ምርኮውንም መልሷል ኢየሱስ ድል ነስቶ ዛሬም ይደግመዋል ሕዝቦቹን ጐብኝቶ አዎን ይሆናል መቼ ይቀራል እንጠብቃለን ለቅሷችንን በደስታ ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን ሃዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል ዓለም የሌላትን መድህን አግኝተናል ስለዚህም እኛ ምንም ብንገፋ ማንም አይጥለንም ከዚህ ፅኑ ተስፋ አዎን ይሆናል መቼ ይቀራል እንጠብቃለን ለቅሷችንን በደስታ ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን በቅርብ በሩቅ የተበተናችሁ ጌታ ቅርብ ነውና ፍፁም አይግፋችሁ የእርሱን በጐነት ለዓለም ተናግራችሁ ለጽዮን ስብሰባ በእግዚአብሔር ያብቃችሁ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ቶሎ ና ናና ሰብስበን ከተበታተንበት ወደ ውድ አገራችን ጥራን አከማቸን አዎን ይሆናል መቼ ይቀራል እንጠብቃለም ለቅሷችንን በደስታ ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ
Открыть в Telegram#የማለዳ_ቃል 🌤 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው። — የዮሐንስ ወንጌል 1:52 መልካም ቀን ! ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
Открыть в Telegram#የማለዳ_ቃል 🌤 መዝሙረ ዳዊት 121 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም። ⁴ እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም። መልካም ቀን ! ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
Открыть в Telegramጥበበኛ ሁን! ሰውየው እንጨት የመቁረጥ ችሎታ አለው። በዚህ ችሎታው ወደ አንድ መስሪያ ቤት ሄዶ አመለከተ አለቃው ጠንክሮ እንዲሰራ አሳስቦ ቦታና መጥረቢያ ሰጥቶት ስራውን ጀመረ። እንጨት ቆራጩ በመጀመሪያ ቀን18 ዛፎችን ቆረጠ አለቃው እንኳን ደስ ያለህ በማለት በሌሎችም ቀን ከዚህ የተሻለ እንዲሰራ አዘዘው። ዛፍ ቆራጩ በሁለተኛው ቀን የሚችለውን ያህል አደረገ ነገርግን የቆረጠው ዛፍ ቁጥር 10 ብቻ ኾነ። ቀናት እያስቆጠረ ቢመጣም እየቀነሰ እንጂ እየጨመረ ባለመምጣቱ ወደ አለቃው ሄዶ ምን እንደሚሻል አላውቅም ሲል ይቅርታ ጠየቀ። አለቃውም "መቼ ነበር ለመጨረሻ ጊዜ መጥረቢያህን የሳልኸው?" ሲል ጠየቀው እንጨት ቆራጩ፦ "እኔ ጊዜ አግኝቼ መጥረቢያዬን ሞርጄው አላውቅም ምክኒያቱም ዛፎቹን በመቁረጥ ተጠምጄ ነበር" ሲል መለሰለት። ብዙ ነገር እንሰራለን ግን ጥበብ የሌለበት ድርጊት ውጤቱ ድካም ነው! " ብረት ቢደነዝዝ ሰውም ባይስለው ኃይልን ሊያበዛ ይገባዋል፤ ጥበብ ግን ሥራውን ለማከናወን ትጠቅመዋለች።" (መጽሐፈ መክብብ 10: 10) ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
Открыть в Telegram