Кабинет

Посты канала 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ™

сначала новые

#531535Фото
Просмотры7 009−83%к среднему
Пересылки0
Реакции74
Комментарии35
#531531Фото
Просмотры8 415−80%к среднему
Пересылки0
Реакции41
Комментарии5
#531528Фотоальбом

‼️  በገላግሌዋ ሁሉም ተገላግሎል! እርሶስ በረሮ እና አይጥ ያስቸግሮታል❓ 💯% አስተማማኝ የሆነ #የበረሮ እና #የአይጥ ማጥፊያ ባሉበት ይቀበሉ! 📍#አዲስ_አበባ    📍#ደሴ 📍#ኮምቦልቻ   🚚 ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በ 30 ደቂቃ ያሉበት ስናደርስ በሌሎች ከተማዎች በፖስታ ቤት እንልካለን! ‼️ ከመጨረሳችን በፊት    ፈጥነዉ ይደዉሉልን‼️ 📞0954633900 📞0954633900 ✍ወይም ስልኮንና አድራሻዎን በ👉@dubaitera_shop ላይ ይላኩልን።   ✅በዓለም አቀፍ ደረጃ የጥራት ማረጋገጫ ያለዉ ኦሪጅናል Ultrasonic pest repeller 🙏 ❇️በፈለጉት ቦታ ላይ በመሰካት ብቻ  👉አይጦችን🐀 👉 በረሮ 🪳 እና ጉንዳን 👉የወባ ትንኝ(ቢምቢ)🕷  👉ማንኛዉንምበራሪ ነፍሳት ላይ ☠ሊቋቋሙት የማይችሉትን frequency  በመልቀቅ ላይመለሱ እሰከ መጨረሻዉ ይሸኛቸዋል! #ሰዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት የሌለዉ ሲሆን ወጥመድ ልግዛ አይጥ ልጎትት ሳይሉ አይጦችን እንዲሁም በረሮን 100 ሜትር የሚያርቅ ድንቅ የዘመኑ ዉጤት👏👏   😱 በ 1699 ብር ብቻ ይገላገሉ። ‼️ጥቂት ፍሬዎች ሰላስገባን ሳንጨረስ ፈጥነዉ ይዘዙን‼️      👇👇👇👇👇👇 👉📞0954633900 👉📞0954633900 ✍ወይም ስልኮንና አድራሻዎን በ👉@dubaitera_shop ላይ ይላኩልን። 🚚አዲስ አበባ  እና ጠበጠቀስናቸዉ ከተሞች ላይ ያሉበት በነፃ ስናደርስ ለሌሎች ከተሞች በፖስታ ቤት እንልካለን። #ሙሉዋስትና ያለዉ ሲሆን ሰክተዉ አይጥ ወይም ተህዋስ ፎቶ ማንሳት ከቻሉ ሽልማት አሎት!(አይችሉም እንጂ) 🌐ሌሎች ዕቃዎችን ለማየት @Dubai_tera2 ን   👆👆👆join ይበሉ!

Открыть в Telegram
Просмотры6 808−84%к среднему
Пересылки0
Реакции11
Комментарии0
#531527Фото
Просмотры7 109−83%к среднему
Пересылки0
Реакции4
Комментарии—
#531526Фото
Просмотры7 119−83%к среднему
Пересылки0
Реакции5
Комментарии0
#531522Фото

.....የቀጠለ #ክፍል_አስር (የመጨረሻ) ከምንጊዜው የእግርኳስ አማካዮች አንዱ የሆነው ፣ የታማኝነት ተምሳሌት ፣ አይደክሜ ፣ በአመራር ብቃቱ የበሰለ ፣ አንፊልዳዊያን (ሊቨርፑላዊያን) እንደ አይን ብሌናቸው የሚወዱት ፣ ታታሪ ፣ ያለው ሁሉ ሳይሰስት የሰጠ የእግር ኳስ ተጨዋች የነበረው #ስቴቨን_ጄራርድ ነው። የሊቨርፑል ደጋፊዎች ምን ግዜም በአንድ ነገር ይፀፀታሉ። 2014 ድንገት ከእጃቸው ስላፈተለከው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ክብር ዋንጫ ሲያስቡ ደሞ የምር ይንገበገባሉ። ያ መጥፎ ቀን ሊቨርፑል ከ ቼልሲ በአንፊልድ ቀዮቹ ለአመታት የጠበቁት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ሊያነሱ ከጫፍ በደረሱበት የውድድር አመት ታማኙ ልጃቸው ድንገት አንቀላፉ ሊቨርፑልን በእጁ የነበረው የዋንጫ ተስፋ ለማንቸስተር ሲቲ አሳልፎ ሰጠ። ስቴቨን ጀራርድ መቼም ማስታወስ የማይፈልገው የተረገመ ቀን 40 አመቱ አማካይ እድሜ ልኩ በለፈባት ክለብ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ፣ ኤፍኤ ካፕ፣ ሊግ ካፕ እና ኮሜንት ሽልድ ቢያሸበርቅም የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ግን መሳም አልቻለም። ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በአንድ ወቅትሲ ወቅት "ጀራርድ በእንግሊዝ በጣም ተፅእኖ ፈጣሪው ተጨዋች ነው። ቬራም የሚጎድለው ነገር የለም ነገር ግን ጀራርድ ከፓርትሪክ ቬራ የበለጠ መስራት ይችላል" ሲሉ አወድሰውታል። ፓትሪክ ቬራም ቢሆን ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስለ ጀራርድ የተናገረው ሰምቻለው፣ ትክክል ብሎ ነበር። ተጠናቀቀ። @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Открыть в Telegram
Просмотры30 040−28%к среднему
Пересылки16
Реакции181
Комментарии28
#531521Фото

....... የቀጠለ #ክፍል_ዘጠኝ ጊል ሞርጋን ይቀጥላል "በዛን ጊዜ ቡድኑ ብዙ ስኬቶች ተቀዳጅቶ ነበር በስቴቨን ጄራርድ ምክንያት።" ጄራርድ በ9 አመቱ የሊቨርፑል አካዳሚ ተቀላቀለ። ታማኝነት በሰው ብትገለፅ ጃራርድን ትመስላለች። ለክለቡ ታማኝ ያለው ሁሉ የሰጠ አለማችን ላይ ከታዩ ምርጥ አማካዮች አንዱ የነበረው እንግሊዛዊው ስቴቨን ጄራርድ ነው። የተሟላ አማካይ ነበር ፣ ከሳጥን ሳጥን ለመሮጥ የማይደክመው ፣ ወደኋላ ተመልሶ የመከላከል ብቃቱ ፣ የሚገራርሙ ሹቶቹ፣ የጭንቅላት ኳስ አጠቃቀሙ፣ ኳስን ይዞ አታሎ የማለፍ ብቃቱ፣ ጎል የማስቆጠር ብቃቱ፣ የጎል እድል ፈጠራው፣ የማይደክመው፣ በአመራርነቱ እና በተፅዕኖ ፈጣሪ ባህርያቱ ይታወቅ ነበር፡፡ ስቴቨን ከረጅም ርቀት ኳሱን ወደ መረብ የማስቆጠር ባለው ችሎታ የተነሳ በዓለም ዙሪያ የሚፈራ ተጨዋች ነበር፡፡  ምንም እንኳን የቀኝ እግር ተጨዋች ቢሆንም በተፈጥሮው ሁለቱንም እግሮቹን በመጠቀም መምታት ይችላል ፡፡ አየር ኳስም በየትም ቦታ ይሁን በማንም ተጨዋች በቀላሉ የበላይነት የሚወስድ ነበር። ሁለገብ ተጫዋች ነበር እና እንደ ሁለተኛ አጥቂ ፣ ከሳጥን እስከ ፔናሊቲ ቦክስ አማካይ ፣ አጥቂ አማካይ እና የተከላካይ አማካይ ያሉ በርካታ ቦታዎችን ተጫውቷል ፡፡  በተጨማሪም በቀኝ ተመላላሽ በሚያንፀባርቅ ብቃት መጫወት ችሏል የመሀል ሜዳው ሞተር ስቴቨን ጀራርድ፡፡ በልጅነቱ ለትውልድ ስፍራው #ዊልስተን_ጁንየር የመጀመሪያው እግርኳስ በህፃንነቱ ሀ ብሎ ጀመረ። ስቴቨን በሊቨርፑል መልማዮች አይን ውስጥ ገባ። በ9 አመቱም ወደ ሊቨርፑል አካዳሚ አስፈረሙት። በሊቨርፑል  ቤት ገና ከህፃንነቱ ጀምሮ በአካዳሚው ምርጥ የሚባል እንቅስቃሴዎች አስደናቂ የኳስ አጨዋወት ያሳይ ነበር። ባሳየው የሚገርም ብቃት ገና በ17 አመቱ ወደ ዋናው የሊቨርፑል ቡድን ፊርማውን አኖረ። ስቴቨን ጀራርድ እ.አ.አ ሕዳር 29 1998 በእንግሊዝ በፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል ከብላክ በርን ሮቨርስ በነበረው ጨዋታ ለመጀመሪያ ግዜ ተሰልፎ መጫወት ቻለ። በዚያው አመትም 13 ጨዋታዎችን ለሀያሉ ሊቨርፑል ማድረግ ቻለ። ለሀገሩ እንግሊዝ የመጀመሪያው ጨዋታ ማድረግ የቻለ ደግሞ በግንቦት 31 2000 እንግሊዝ ከዩክሬን በነበረ ጨዋታ ነው። እ.አ.አ. ከ2000-01 የውድድር ዘመን ጀራርድ በሊቨርፑል ውስጥ ወጥ አቋም ማሳየት ጀመረ፡፡ የቡዱኑ ቁልፍ ተጨዋች፣ ምርጥ አማካይ ለመሆን ግዜ አልፈጀበትም። በወቅቱ ጀራርድ ለሊቨርፑል በሁሉም ውድድር 50 ጨዋታዎችን አድርጎ 10 ጎሎችን ማስቆጠረ ችሎ ነበር፡፡  በተጨማሪም ስቲቨን በዚያ ወቅት የኤፍኤ ካፕ ፣ የእግር ኳስ ሊግ ካፕ እና የዩኤፍ ካፕን ጨምሮ ሶስት ዋንጫዎችን አንስተዋል። እ.ኤ.አ. ከ2001-02 ባለው ጊዜ ውስጥ ጀራርድ የኤፍኤ ቻሪቲ ሺልድ እና የUEFA ሱፐር ካፕ አሸናፊ መሆነ ቻለ፡፡ ይሄንን ሁሉ ዋንጫዎች እና የሊቨርፑል ስኬት እንዲመጣ ትልቅ አስተዋጽኦ ካደረጉ የሊቨርፑል ተጫዋቾች ጀራርድ ግንባር ቀደም ያደርገዋል። ስቲቨን በፕሪሚየር ሊጉ 504 ጨዋታዎችን ለሊቨርፑል እንዲሁም ከ 700 በላይ በሁሉም ውድድሮች ላይ ተጫውቷል፡፡እናም አማካይ ሆኖ 120 ግቦችን አስቆጥሮ 71 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበል ችሏል👏👏። ጀራርድ እ.ኤ.አ. በ 2015  እንዲህ አለ "እኔ ከሊቨርፑል እለቃለሁ ነገር ግን ለማንም የእንግሊዝ ይሁን የአውሮፓ ክለብ አልጫወትም ምክንያቱም በምንም አጋጣሚ የሊቨርፑል ተቃራኒ ሁኜ መጫወት አልችልም" ለዚህም ወደ ኤልኤ ጋላክሲ የአሜሪካን ክለብ በመቀላቀል 34 ጨዋታዎችን የተጫወተ  ሲሆን በ 5 አጋጣሚዎች ጎሎችን አስቆጥሯል። በጥቅምት 2003 ስቴቨን ጀራርድ በነበረው የአመራር ብቃት እና ባህሪያት የሊቨርፑል አምበል(ካፒቴን) ሆኖ ተሾመ፡፡ የሊቨርፑል አምበል መሆን የቻለው በጣም የተሳካለት ካፒቴን የነበረውን ተከላካይ ሳሚ ሂፒያን በመተካት ነው፡፡ በሊቨርፑል የስቴቨን ጀራርድ አስተዋፅዖ ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም ። . . . ይቀጥላል @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Открыть в Telegram
Просмотры26 847−36%к среднему
Пересылки18
Реакции113
Комментарии6
#531520Фотоизменён

.... የቀጠለ #ክፍል_ስምንት ፓውል ወንድሜ ብቻ ሳይሆን ምርጥ የቡድን አጋሬም ነው። እንደዛ ነበር ይሆናልም። በጣም እወደዋለሁ ብዙ ነገር አስተምሮኛል ጥሩ ሰው ነው። ፓውል አንድ አንዴ ይጮህብኝ ነበር። አንዳንዴም ይመክረኛል አለፍ ሲልመ ያኮርፈኛል። እሱ የኛ ጀግና ነው። በቡድኑ የእግርኳስ ቡድን መቀላቀሌ ቅር አልተሰኘም ነገር ግን ጓደኞቹ እና እሱ አብረው በሚያወሩበት ወደ ሌላ ቦታ በሚሄዱበት እንድገኝ አይፈልግም ነበር። ወንድሜ በማንኛውም የእግርኳስ ጨዋታ ከሆነ እንዲሄድ ይፈቅድልኝ ለሌላ ነገር ግን አይፈቅድልኝም ነበር። አንዳንዴ በዚህ እንጣላ ነበር እስከመደባደብ ድረስ ግብግብ እንገጥማለን። አንዳንዴም እጠለሀለሁ ብየ እጮህበት ነበር እውነት ለመናገር ከልቤ አልነበረም እሱም እገለሀለሁ ዝም በል ይለኛል። በመኮራረፍ ውስጥም ፍቅር ነበረን። ወንድሜ ፓውል የኳስ እውቀት ነበረው ስለ አጨዋወት ስለ ታክቲክ ያውቃል። እኔም በተመሳሳይ ደረጃ ነው ያለነው ስል ሁሌ ከጨዋታ በኋላ እነግረው ነበር። እሱም ፈገግ ብሎ ንግግሬ ከቁብ ያስቆጥረው ያልፈዋል። ቤተሰቦቼ እና ዘመዶቼ አባቴ አባቴ ጥሩ የእግር ኳስ ተጨዋች እንደነበረ ይነግሩኛል። በርግጥም ነው። "ያ ሁላ ያገኘሀው ጥበብ ከማን ሆነ እና" ሲል አባቴ ስለዚህ ጉዳይ በጠየኩት ጊዜ መለሰልኝ። በሚያሳዝን ሁኔታ ገና ወጣት እያለ በሚጫወትበት አደገኛ ጉዳት ጉልበት ላይ አጋጥሞት መጫወት እንዲያቆም ተገደደ። በዘመዳችን ብዙ እግርኳስ የሚጫወቱ አሉ። በርግጥ ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱ የሉም ነገር ግን እግርኳስ በዘመዳችን ይወደዳል ይላል ብላቴናው my autobiography በሚል መፅመፉ። ገና ሲወለድ እድሉ እምብዛም ጥሩ አልነበረም። እግሮቹ #የተጣመሙ ነበሩ አይደለም እግርኳስ ለመጫወት ቆሞ ለመሄድ እንኳን የሚመቹ አልነበሩም። ወላጆቹ ልጃቸው ቆሞ እንድሄድ ገና በህፃንነቱ ተገቢ ህክምና አደረጉለት። እግሮቹ ተስተካከሉለት። ሌላው አስቸጋሪ የስቴቬን ጄራርድ የህይወት ጉዞ #ተደጋጋሚ_ጉዳት ያጋጥመው ስለነበረ ነው። ስቴቨን በቅዱስ ሚካኤል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚማርበት ጊዜ ኳስ አዘውትሮ ይጫወት እንደነበረ ይሁን እንጂ አይናፋር እና ቁጡብ እንደነበረ አስተማሪዎቹ ይናገራሉ። "እሱ ሁልጊዜ መልካም ፣ ትሁት ፣ እና በጥሩ አስተዳደግ ያደገ ነው" ይላሉ። "ወደ ታላላቆቹ ኳስ ለመጫወት በሄደበት ጊዜ ትክክለኛ ባህሪው ታወቀ። ስቴቨን ምርጥ መሆኑን ለመረዳት የእግርኳስ ሞያተኛጨመሆን አይጠበቅብህም። ልዩ ነው። በጣም ይወደዳል። እግርኳስ ማለት ለእሱ ትንፋሱ ማለት ነው። እግርኳስ እየተነፈሰ ያደገ ልጅ ነው" ሲል የቀድሞ አስተማሪው ግል ሞሪጋን ይናገራል። . . . ይቀጥላል የቆየነው በአጋጣመን የግል ችግር ነው ይቅርታ @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Открыть в Telegram
Просмотры24 536−42%к среднему
Пересылки16
Реакции111
Комментарии8
#531519Фото

.... የቀጠለ #ክፍል_ሰባት ከዚያ ሁሉ አልፎ ኳስ መጫወት ጀመርኩ። ከእለታት አንድ ቀን እኔ እና ወንድሜ #ፓውል ጭቃ በጭቃ ሆነን ወደ ቤት ገባን። እናቴ ተናዳደች። አባቴ ግን በአንፃሩ በጭቃ ተሸፍነን ሲያየን አልቻለም ሳቁን ለቀቀው። በክረምት ጊዜ ቤተሰብ አንድ ላይ ተሰባስበው ይጠጣሉ ፣ ይጫወታሉ ፣ ይዝናናሉ ህፃናቶችም በሌላ በኩል ይጫወታሉ። በሰፈራችን ኳስ ማንኛውም ሰው ኳስ ሲጫወቱ ሳይ ደስ ይለኛል። #ሊዛ እና #ካሮሊን የሰፈራችን ሴቶች ናቸው። ከእነሱ መዋል እና ጊዜ ማሳለፍ ደስ ይለኛል በጣም እንግባባለን ይሁን እንጂ እነሱ ኳስ መጫወት አይችሉም ነበር። እውነታው ብዙ አልጨነቅም ነበር። ኳስ ለመጫወት ብዙ ርቀት መጓዝም አይጠበቅብኝም ነበር። ለእግርኳስ ጨዋታ #ብሉቤል በቂ ነበረች። ብሉቤል ማለት #በሀይቶን ከተማ የሚገኝ መንደር ነው። ሀይቶን ከተማ Steve McMahon, Joey Barton, Lee Trundle, Peter Reid, Tony Hibbert, Craig Hignett and David Nugent የመሳሰሉ ታዋቂ ተጨዋቾች ያፈራች ከተማ ነች። በዚች ከተማ እሁድ በእግርኳስ የሊግ ጨዋታዎች ይጨናነቃል። እግርኳስ እንደ ሀይማኖት ነው። #በብሉቤል እናቴ እስክትጮሁብን 7 ወይም 8 ጓደኞች ሆነን በየሰአቱ ኳስ እንጫወታለን። ይሁን እንጂ ከሰፈር ልጆች ደና ጨዋታ መጫወት አልቻልኩም እውነት ለመናገር ከእነሱ የተሻልኩ ተጨዋች ነበርኩ። በ3 አመት ከሚበልጠኝ ፓውል ወንድሜ መጫወት እመርጥ ነበር። ፓውል 15 የሚጠጉ የቡድን አጋር ነበሩት። ጨዋታቸውም ማራኪ እና ጥበብ የተሞላበት ነበር። በ6 አመት ከፓውል እና የፓውል 9 አመት የሞላቸው ጓደኞቹ መጫወት እችል ነበር። የፓውል ጓደኞች እኔ ከእነሱጋ እንድጫወት ይፈልጉ ነበር። ፉክክራቸው ይመቸኛል ለመጫወት ቦታ የምመርጥ ሰው ስላልነበርኩ እነሱም አብርያአቸው እንድጫወት ፈቀዱሉኝ። ምርጥ ተጨዋቾች ናቸው። ፓውል ለራሱ በቦልተን ወንደረርስ ሙከራ አድርጎ ነበር። ፓውል እና ጓደኞቹ ከ10 አመት በታች በቶሎጌት የአከባቢው ሊግ መጫወት ጀመሩ። አንድ ቀን ፓውልን ተከትየው በመሄድ የቶልጌት አስተባባሪዎች መግባት እችል እንደሆነ ጠየኳቸው። "እድሜህ ስንት ነው?" ብለው ጠየቁኝ። 7 ብየ መለስኩላቸው። "ገና ህፃን ነህ" መለሱ። እንባየ ድንገት ሲወርድ ታወቀኝ. "ተሳስታችኋል እኔ ለጨዋታ ብቁ ነኝ" አልኳቸው ግን ማንም ትኩረት አልሰጠኝም። ተቀባይነት ባለማግኘት ውስጤ እርር ብሏል። አያቴ በጣም ደግ ሰው ነው። ልጆቹ ሁሉም ነገር እንዳላቸው እርግጠኛ ሁኚ አላት። . . . ይቀጥላል @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Открыть в Telegram
Просмотры30 605−27%к среднему
Пересылки12
Реакции142
Комментарии11
#531518Фото

.... የቀጠለ #ክፍል_ስድስት ወንድ ሳይቀር እኔን ሲመለከት ፊቱ ላይ ፍርሃት እና መደናገጥ ፊቱ ላይ ይታይ ነበር። በዚህ የተረገመ አደጋ ምክንያት 3 ሳምንታት ከትምህርት ቤት ቀረሁ። ለትምህርት የሚሆን ጊዜ አልነበረኝም እንዴትስ እማራለሁ? አንድ ነገር ግን ከህመሜ ጋር እየታገልኩ ሳደርግ ነበር። አልጋየ ላይ ሆኜ የሊቨርፑል ቪድዮዎች እመለከት ነበር። ዋውው የሚያሳዩት ብቃት ማራኪ ነው። እነሱን ባየሁ ቁጥር ህመሜን በኖ ይጠፋል ፍፁም እረሰዋለው። ጆን ባርነስ ፣ ኬኒ ዳግልሽ እና ኢያን ሩሽ በፍቅር በተደጋጋሚ አያቸዋለሁ። ከህመሜ ቶሎ እንዳገግም ረድቶኛል። ሀኪሙ በየቀኑ ቁስሌን ታፀደዋለች። ቀስ በቀስ የምታደርግልኝ የጥጥ መጠንም እየቀነሰች መጣች እኔም በየጊዜው ለውጥ እያመጣሁ ነበር። ከሳምንታት በኋላ ትምህርት ቤት በክራንች ሄድኩ። እግርኳስ ሲጫወቱ ተመልከቱ። ቅናት ቢጤ ተሰማኝ። ጄራርድ ለትንሽ ጊዜ ታገስ እያልኩ ውስጤን እነግረዋለሁ። ለመጀመሪያ ጊዜ ከምወደው እግርኳስ እንዳልጫወት ተከለከልኩ። ያጋጠመኝ አደጋ እና ለመዳን የወሰደብኝ ጊዜ እግርኳስ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስታወሰኝ። ከዚያ ቀን በኋላ ቪድዮዎች እንኳን ስመለከት በስርዓት ነው። ከኳስ ከዚህ በኋላ በፍጹም መራቅ አልፈልግም። ከአምስት ሳምንታት በኋላ ኳስ መምታት ጀመርኩ። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ያለ እግርኳስ ህይወቴ ባዶ ይሆን ነበር። ኳስ ማለት የህይወቴ እያንዳንዷ ትንፋሽ ናት። እግሬ የተመታሁት በዛገ ብረት ስለነበረ ሌላ ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር ተጨማሪ ክትትል አድርጊያለሁ። በዚህ ማህል እናቴም አባቴም እኔ ለማስደሰት የበኩላቸው እየተወጡ ነው። አሁን ድረስ ያ አደጋ ሳስበው እንደ ኤሌክትሪክ ይነዝረኛል። አሁንም ድረስ ያ የገባ ብረት ይታየኛል። እያንዳንዱ ህመም ይሰማኛል። ስለ አደጋው ከአባቴ ጋር አንዴ ወይም ሁለቴ አውርተናል። እውነት ለመናገር አባቴ ፍፁም ጉራ የለውም። እርግጠኛ ሁኜ እምነግራችሁ አባቴም ቢሆንም እያየ የእግር አውራ ጣቴ እንዲቆረጥ አያደርግም ነበር። ሁላችንም እናውቃለን የእግሬ አውራ ጣቴ ተቆረጠ ማለት በሊቨርፑልም ሆነ በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ህልም ሙሉ በሙሉ ይከሽፋል። . . . ይቀጥላል @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Открыть в Telegram
Просмотры31 058−26%к среднему
Пересылки13
Реакции132
Комментарии16
#531517Фото

... የቀጠለ #ክፍል_አምስት "አይሆንም እኔና አባቱ ሌላ መንገድ እንፈልጋለን" አላት የልጇን እግር ኳስ ለመጫወት ዘወትር የሚያልመውን ልጅ የሚያፅናና ቃል እየሰማች እንባዋ ይወርዳል። ጅሩ አውራ ጣቱ ወደሚቆረጥበት ቀዶ ጥገና ክፍል በአይኖቹ መንትያ እንባ እያነባ ገባ። አባት ፖል ስቴቨን የስልክ ጥሪውን አንስቶ ሲያወራ በድንጋጤ ፈዘዘ #የአካዳሚው_ኮች ነበር። በቻለው ፍጥነት ሁሉ  ወደ ሆስፒታሉ ሮጠ፡፡ በየመንገዱ ለአላፊ አግዳሚው ሰላምታ እየሰጠ በእግሩ በረረ፡፡ ሆስፒታሉ የቅርብ ሩቅ ሆነበት፡፡ እንደደረሰ የቀዶ ጥገናውን ክፍል በር በኃይል ገፍትሮ ወደ ውስጥ ዘለቀ። አትኩሮ አየኝ። ረጋ አለ እና "ይሄማ ጣት የሚያስቆርጥ ችግር አይደለም ብዙም እየደማ አይደለም" ሲል ተናገረ። ዶክተሩም "ማድረግ አለብን። ሕክምናው በቀዶ ጥገና ሀኪሞች ይከናወናል" ሲል መለሰ። ስቲቭ ፅናተኛ ነበር። "አይሆንም በፍፁም አይቆረጥም" አሁንም በሀሳቡ ፀንተዋል። በመጨረሻም ስቲቭ አሸነፈ። ጄራርድ እግሩ አይቆረጥም። ዶክተሮች ጄራርድን የማደንዘዣ መድሀኒት ሰጡት እና እግሩ ውስጥ ገብቶ የነበረውን ብረት አወጡት። በጣም ትልቅ ብረት ነበር የገባው ብረቱ ሲወጣ በእግሩ ትልቅ ቀዳዳ ፈጠረ። በጣም ያስጠላ ነበር ብያንስ ግን እግሬን ከመቆረጥ ተርፈዋል። "አንተ በጣም በጣም እድለኛ ሰው ነህ" አለ። "እንደዚህ ነገር ከዚህ በፊት አይተን አናውቅም" እያሉ ሁሉም ሲናገር ይደመጣሉ። . . . ይቀጥላል @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Открыть в Telegram
Просмотры29 351−30%к среднему
Пересылки12
Реакции121
Комментарии9
#531516Фото

.....የቀጠለ #ክፍል_አራት አባት ትንሽ አሰበና በማግስቱ የስታዲየም ትኬት ገዝቶ ልጁን ወደ ስታዲየም ይዞት ሔደ። በkops በሚቀመጡበት ቦታ ተቀመጠ  ወደ ታች ሲመለከት የሜዳው ሳር ንፁህነት ልቡን ማረከው ቀና ብሎ ሲመለከት  የመብራት ፓውዛ  ድምቀት  አንድ ወደማያዉቀው አለም ወሰደው። ጨዋታው አይቶ ሲጨርስ በደስታ ሃሴት እያረገ ወደ ቤቱ ሄደ። በጠዋት ተነስቶ  ከጓደኝቹ ጋር ኳስ ሲጫወት  ሜዳው ረጠብ ያለ ነበር።  በድንገት አንዱ ኳሱን ሲጠልዘው ወደ ጓሮ ገባች። ጅሩ ኳሱዋን ሊያመጣ እየሮጠ ወደ ጓሮው ሔደ እንደደረሰም ኳሱዋን መታሁ ብሎ #መቆፈሪያውን በኃይል ነረተው። የቀኝ እግሩ አውራ ጣት #በደም ጨቀየች። የመታውን መቆፈሪያ ሲመለከት በጣም የዛገ ነበር። "አምላኬ ሆይ በጣም ያማል" ሲል ብቻውን ይናገራል። ደም ከእግሩ እየፈሰሰ ነው። እግሩ ውስጥ ብረት ነገርም ገብቷል። ብላቴናው ልጅ ህመሙ መቋቋም ያቀተው ይመስላል። በህይወቴ እንደዛ ቀን ህመም ተሰምቶኝ አያውቅም ይላል። በጣም ከባድ ነው። አባቱ እና እናቱ እግሩን እየደመ ባዩ ጊዜ በጣም ደነገጡ። ያለው ስቃይ እየፈሰሰ ያለው ደሙ  ሲመለከቱ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ወሰዱት። ሆስፒታል ደረሱ ዶክተሮች ወዲያ ወዲህ እያሉ ነው። ጄራርድ እግሩን ተመለከቱት እየደማ ነው በዛላይ ብረት ገብቷል። በጣም የዛገ ብረት ነው። የሆስፒታሉ ዶክተር "የአውራ ጣቱን ከመቁረጥ ሌላ አማራጭ የለም" ሲላቸው  ከስቴቨን ጋር አብረው የሔዱት መብረቅ እንደመታው ሰው በድንጋጤ ፈዘው ቀሩ። "ከእንግዲህ በኃላ ኳስ መጫወት አልችልም ጣቴ ሊቆረጥ ነው ማለት ነው"አለ ጅሩ ከወላጅ እናቱ መልስ እየፈለገ እናት ጥያቄውን ስትሰማ ወደ ጅሩ ተመልክታ እንባዋን በእጆቿ ጠረግ በማድረግ ላይ እያለች የአካዳሚው ኮች ደወለ።ሁኔታውን እያለቀሰች ነገረችው። . . . ይቀጥላል @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Открыть в Telegram
Просмотры30 295−28%к среднему
Пересылки13
Реакции128
Комментарии5
#531515Фото

... የቀጠለ #ክፍል_ሦስት ጄራርድ ወደ መርሲሳይድ ጎዳና በጧት ደረሰ አካባቢውን ቢቃኝ ማንም የለም  ከጓደኞቹ ቀድሞ ነበር የደረሰው። ጓደኞቹ እስከሚመጡ ኳሱን ከግድግዳ ጋር እያጋጨ ለብቻው መጫወት ጀመረ። የጄራርድ ቤተሰቦች ልጥጥ ሃብታም ባይሆኑም እንኳን  በእግር ኳስ ፍቅር ያበደውን ልጃቸውን ከመደገፍ ወደኋላ አላሉም፡፡ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ያቀርቡለታል።     የሊቨርፑል አካዳሚ ዳይሬክተር ስቲቭ ሃይዌይ እና አባቱ  በጎዳናው ላይ ብቃቱን ሲመለከቱ  አሰገረማቸው #በዘጠኝ አመቱም ወደ አካዳሚው ተቀላቀለ... የታዳጊነቱ ዘመን አልፎ ጉርምስና ከተፍ ያለለት ጄራርድ ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ ለመስራት ያለው ፍላጎት  ሲያስጨንቀው ኖሯል ፤ አንድ ቀን በቤቱ ቁጭ ብሎ የሆነ ሃሳብ በአዕምሮው እየተመላለሰ አስቸገረው። የስፖርት ትጥቁን ለባበሰና ወደ #ማንችስተር_ዩናይትድ ልምምድ ማዕከል አመራ  ክለቡም የልምምድ ጊዜ ሰጡት በብቃቱ ተገረሙ። ድንቅ ቴክኒክ ፥ግሩም የአየር ላይ ኳስ፤ የአንድ ለአንድ ግንኙነት የማይታለፍ፥የአዕምሮው ጥንካሬ ፈጣን፤ አሰልጣኙን እና መልማዩን በግርምት አፍ ሲያዘጋቸው ፊርማ እንደሚሰጡት ነገረውት ወደ ቤቱ ተመለሰ። አባት ያደረገውን ነገር ሲሰሙ እየተናደደም ፤ እየተበሳጨም በጥድፊያ ወደ ቤት ሄዶ "ጅሩ ከቶ ይሔን ሃሳብ ከየትስ መጣልህ እንዴት እንደዛህ ታደርጋለህ በኛ እና በነሱ መካከል ያለውን ጉዳይ ሳታውቅ ቀርተህ ነው። ከልጅነትህ ጀምሬስ ደጋግሜ አልነገርኩህም" አለው። ጅሩም በፈገግታ "አባ ሊቨርፑልን ኮንትራት ሳይሰጡኝ ዝም አሉ።እንደዛ ያደረኩት ፕሮፌሽናል ኮንትራት እንዲሰጡኝ ለማስገደድ ነው" ሲል ይመልስለታል" . . . ይቀጥላል @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Открыть в Telegram
Просмотры30 311−28%к среднему
Пересылки13
Реакции142
Комментарии12
#531514Фото

.... የቀጠለ) #ክፍል_ሁለት እግር ኳስ መጫወት ነብሱ ነው ሁሌም ቢሆን በማለዳ ነው የሚነሳው  ጎደኞቹን ለነገ ጨዋታ በጧት እንዲመጡ ነገራቸው። በዚያች ታላቅ የመርሲሳይድ ጎዳና የጨዋታ ቀን ግን  ከእንቅልፉ ሲነቃ ጤናማ እንዳልሆነ ተሰማው፡፡ ከትምህርት ቤት ለመቅረት ሆን ብሎ አመመኝ የሚለው አይነት ህመም አልነበረም፡፡ ከአልጋ መነሳት እስኪያቅተው ድረስ ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጸጉሩ ድረስ ጠፍንጎ ያዘው፡፡ እናቱ ወደ ክፍሉ ገባች፡፡ ሰውነቱ በትኩሳት ግሏል፡፡  ‘‘ዛሬ ከቤት አትወጣም፣ ታመሃል፡፡ ዕረፍት አድርግ፡፡ ሾርባ እሰራልሃለሁ’’ አለች እናት እንደመደንገጥ ብላ፡፡ ‘‘እንዴ! እማዬ! ዛሬማ ቤት መቀመጥ አልችልም መውጣት አለብኝ፡፡"  ጆሮዋን ማመን አልቻለችም፡፡ ዞር ብላ የእናትነትዋን መልስ ሰጠችው፡፡‘‘ዛሬ ትምህርት ቤት ዝግ ነው ለካ፡፡ ቅዳሜ ስለሆነ ያ መከረኛ ጨዋታ አለኝ ልትለኝ ነው አይደል? በቃ ምንም ዓይነት በሽታ አያቆምህም ማለት ነው?" ሁልጊዜም ከልጆቿ ጋር ስትሟገት እንደምታደርገው ፊቷን ወደ እርሱ አዙራ እጁዋን አጣምራ ከፊት ለፊቱ ቆመች፡፡ "የዛሬው ይለያል እኮ የሰፈር ዋንጫ ነው የምናደርገው" አለ። ሙግቱን ልትረታው እንደማትችል ስታውቅ እጆቿን አጣምራ ተሟጋቹ ፊት ቆማ እንደፈለክ ብላው ወጣች። . . . ይቀጥላል @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Открыть в Telegram
Просмотры31 193−26%к среднему
Пересылки11
Реакции153
Комментарии8
#531513Фото

ስቴቨን ጄራርድ ከልጅነት እስከ ስኬታማነት #ክፍል_አንድ እኔ በዚህ ዓለም ስፈጠር  ለቀዩ ማልያ ላገለግል ነው።በህይወቴ ውስጥ ሃይለኛ የሆነ ዝምታና ብቸኝነት አለ። በብቸኝነቴ ውስጥ ስለ አንድ ነበልባል ስታዲየም አስላስላለሁ። ይህ ተመስጦም አዕምሮዬ እና አይኖቼ አይተውት በማያውቁት አንድ ታላቅ ስታዲየምና ክለብ ውስጤን ሃሴት ታደርጋለች። ይለናል ታላቁ ሰው ባለ ታሪካችን My autobiography በተሰኘው መፅሀፉ። ቤተሰብ በአንድ ላይ ተሰባስበው እያሉ  ኮሪደሩን ተመለከተ  እና ቤተሰቦቹን  ዓይን ዓይናቸውን እየተመለከተ  አባ ብሎ ሲጠራው አባትየው ካጎነበሰበት ትንሽ ቀና አለ ''ስሞት ወደ ሆስፒታል እንዳትወስዱኝ" አላቸው ቤተሰቦቹም በግርምት "እና የት ነው የምንወስድህ? አሉት እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው "እንግዲያውስ እወቁልኝ ኑዛዜየን ልንገራችሁ እኔ የሞትኩኝ እንደሆን በጭራሽ ወደ ሆስፒታል አትውሰዱኝ ይልቁንም ወደ ቤቴ ወደሆነው #አንፊልድ ውሰዱኝ" ይላል የታማኝነት ተምሳሌቱ የሊቨርፑሉ ልዑል አንፊልዳዊያን እንደ ዓይን ብሌናቸው  የሚወዱት ታላቁ ሰው ስቴቨን ጄራርድ፤ እ.ኤ.አ ግንቦት 30,1980 ከአባቱ ከስቴቨን ፖል እና ከእናቱ ከጁሊያን አን ተወለደ።ለቤተሰቦቹ ሁለተኛ ልጅ ነው። . . . ይቀጥላል @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Открыть в Telegram
Просмотры34 527−18%к среднему
Пересылки22
Реакции220
Комментарии14
#531512Фотоизменён
Просмотры39 260−6%к среднему
Пересылки0
Реакции417
Комментарии18
#531511Фото
Просмотры43 858+4%к среднему
Пересылки0
Реакции384
Комментарии15
#531505Фото
Просмотры41 013−2%к среднему
Пересылки1
Реакции118
Комментарии1
#531504Фото
Просмотры40 470−4%к среднему
Пересылки0
Реакции156
Комментарии2