ፈልጌህ ነበር! ለተነነ ህልሜ.. ለደከመ እግሬ... ብርታት ብትሆነኝ ብዬ ተስፋ አድርጌህ ነበር.... ቀን ቢከዳኝ.... ለተስፋዬ መልህቅ መጣያ ባጣ.... በእቅፍህ እንዳርፍ! በመኖርህ እንድጽናና! ፈልጌህ ነበር.... በእንባ ሌቶቼ.... በሳቅ ቀኖቼ ... እኔና እኔ ብቻ በምናውቃቸው ጊዜዎቼ... ... ..... ....... .......... ............. አልነበርክም!።
Открыть в TelegramПосты канала የኔ ደብዳቤ💌
ከተለያየን ከረጅም ጊዜ በኃላ ከሩቅ አየሁት... ልቀርበዉ ድፍረት አጣዉ ብቀርበዉ በስንት ልመና ያደበ ልቤ እንዳይረብሸኝ አሁንም የምወደዉ አይኑ የረጋ የመሰለኝን መኖር እንዳያናዉጠዉ ፈራሁ... ከሩቅ አየሁት! የመለያየት ህመሙ የሚብሰዉ አሁን ነዉ!! ...ልክ እንዲ እንደድንገት የቢሆን ንፋስ ሲነፍስ.. አሁን እየሮጥኩ ሄጄ ባቅፈዉ ተመኘሁ...መለየት የሰራት እኔን ከወደዳት ብጠይቀዉ ምኔ እንደሚናፍቀዉ የቱ ጋር ትዝ እንደምለዉ ባዉቅ እንደናፈቀኝ እንዳልጠላሁት በነገርኩት..... ከተለያየን አመታት ተቆጠሩ የቀን እርዝማኔ እንዲህ እንደሆነ አላወኩም!!! ስንት እኔን አንስቼ ስንት እኔን ጣልኩ?!!? በእነዚህ ሁሉ አመታት ያልተረሳኝ አይኑ አሁን ካለሁበት አይታይም... የጊዜ ክህደት እዚህ ጋር ነዉ! የምንወደዉን ማራቁ...ስንዝር ታህል ይቀርብ የነበረን እንዲህ ከርቀት ማስቀመጡ... ጊዜ በመዉደድ ላይ ጠባሳ ይጥላል.... .......አይመስልህም??? #vie.. እእእ??
Открыть в Telegramብቻ ትናፍቀኛለህ ... እንደጓጓሁለት የድሮ የማትሪክ ውጤት እርቦኝ እንደምጎርሰው የመጀመሪያ ጉርሻ እንደ መፅሀፎቼ ሽታ እንደ አስቴር አወቀ አዲስ አልበም መውጫ ቀን እንደ እሁድ ጠዋት ቅዳሴ እንደ ልጅነቴ ነፃነት ስደክም ውዬ እንደምተኛው እንቅልፍ እንዳባቴ ኮራሁቡሽ ቃል ሊሳኩ እንደተቃረቡ ህልሞቼ እንደሚሞላልኝ "ግማሽ ቀን" ትናፍቀኛለህ.... #vie 🥀
Открыть в Telegram....አየህ በአንተ ልክ ልወደው እንደማልችል ገብቶኛል.. አሁንም ስልኬ ላይ ፎቶህ አለ አሁንም ያለፍንበትን መንገድ አስታውሳለሁ.. አሁንም የቆጨኝ ህይወት አለ አሁንም ማስታወሻህ ማስታወሻዬ ብቻ አይደለም ኑሮዬ እንጂ ያንተ ትናንት ዛሬዬን አነቀብኝ አየህ አንተ አታውቅም...ትቼህ የሄድኩ ይመስልሀል እኔ ግን ይዤህ እሱ ጋር መጥቻለሁ.. አንተ እያለህ የመውደድ ደህንነት አይሰማኝም.. አንተን እንጂ እሱን እንደማላውቀው ስራዬ ያሳብቃል እሱን እንዳንተ ለመውደድ ልቤ አይፈቅድልኝም እሱን እንደማቅፈው ሳይሆን አንተን እንደማቅፍህ እያቀፍኩት እንደሆነ ሳውቅ ሴትነቴ ያስጠላኛል.. ... #vie¿
Открыть в Telegram...ልዩ አልነበረም የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም.. ገፁ ጨረቃን ወይ ድምፁ ቅዳሴን አላስረሳኝም ቃሉም ሳቁም የሚረሳ! ማንም ነበረ ለ አለም ለኔ ግን --- 'ራሱ አለም!♡ #..
Открыть в Telegramከ ሰማይ በላይ ነው የምወድሽ ይለኝ ነበር...አወዳደዱ ስር አለው..ድንገት ተሰብር ውድቅ ሊል ይችላል የሚባል አይነት አልነበረም.....ይወደኝ ነበር ከሰማይ በላይ ድረስ.... #..
Открыть в Telegramእንዴት ነው ቀንህን መዋል የለመድከው? እኔ እንደሚሰማኝ አይሰማህም ነው? 1 ቀን እውን እንደድሮ 24 ሰዓት ብቻ ነው? ምን ስትሰራ ይመሽልሃል? አንተን ከማሰብና ከማውራት ሌላ ህይወት የሌለኝ እኔ የምሰራው አጣውልህ....አታወራኝም? አልናፈኩህም?... #vie🥀
Открыть в Telegramኖረህ ብቻ አይደለም...አስታውሼህ ደስታዬ የነበርክ አንተ የልቤ ሰው ሆይ! በምኞት ጀምረን በትዝታ ላበቃነው ገፅ ምን ነበር ምላሽህ? #.... 🥀
Открыть в Telegram....ስሜቶቼን እየፈለፈለ ያጋልጣቸውና ግርጌአቸው ላይ ይፈርማል....አለ-ነገር እኮ ስሜት አልባ አልሆንኩም. ደስታዬ ላይ ፊርማው አለ ንዴቴ ላይ......ናፍቆቴ ላይ..... ስጋቴ ላይ......ሙላቴ ላይ... #vie... 🥀
Открыть в Telegramብዙ ከሚመስለኝ ግን ትንሽ ከሆነ እድሜዬ ብዙ ተምሪያለሁ ብስለት የሚመጣው ከሚያጋጥሙን የህይወት ውጣ ውረዶች አይነት እና ከውጣ ውረዶቹ ከቀሰምናቸው ትምህርቶች እንጂ ካከበርናቸው የልደት በዓሎች ብዛት እንዳልሆነ ተምርያለሁ ... To me...🎂
Открыть в Telegram....እየሮጠ የመሰለኝ ጉልበቴ በድካም ዝሎ መቆሙን የዘነጋሁበት የሆነ ጊዜ ነበር...መፍጠን ከመፈለጌ የተነሳ መዘግየቴን የረሳሁበት.... #..🧚♀
Открыть в Telegram