Кабинет

Посты канала AS-HABULE YEMINE

сначала новые

#6021Файл

Переслано из የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

አልሐምዱሊላህ! በመጨረሻም ተለቀቀ! አስጀምሮ ላስጨረሰን አላህ (ሱ.ወ) ምስጋና ሁሉ ለእርሱ የተገባው ይሁን! ላለፉት 45 ቀናት ገደማ ሌት ተቀን በጥልቀት ስንሠራበት የነበረው «ጽልመቱን የገፈፈው ብርሃን» የተሰኘው የተሟላ የምላሽ መጽሐፋችን፣ በአላህ ፈቃድ ተጠናቆ ይኸው ዛሬ በእናንተ እጅ ደርሷል! "ማንም አይመልሰውም፣ ከምዕራፍ 2 አያልፉም" እየተባለ ሲፎከርበት የነበረውን መጽሐፍ ከምዕራፍ 1 እስከ ምዕራፍ 13 ድረስ ገጽ በገጽ እየተከታተለ የጸሐፊውን የማጣቀሻ ሸፍጦች፣ የትርጉም ቅጥፈቶችና የአመክንዮ ክስረቶች እርቃናቸውን ያስቀረው ይህ ታሪካዊ ሥራ አሁን ለሁሉም አንባቢ ክፍት ሆኗል። ለሙስሊም ወንድምና እህቶች፣ መጽሐፉን አውርዳችሁ እንድታነቡት፣ ሐሳብና ገንቢ አስተያየታችሁን እንድትሰጡን፣ እንዲሁም ሼር በማድረግ ለሁሉም እንዲዳረስ የበኩላችሁን እንድትወጡ እንጋብዛለን። ለክርስቲያን ወገኖቻችን፣ የአንድ ወገን ፕሮፓጋንዳ ብቻ ሳያታልላችሁ፣ ይህንን በማስረጃ የተደገፈ ምላሽ አንብባችሁ እውነታውን እንድትመዝኑ፣ በሐሳቡ ዙሪያም በጨዋነት ሀሳብ አስተያየትና ትችት መስጠት ለምትፈልጉ ሁሉ በራችን ክፍት መሆኑን እየገለጽን ሙሉውን ታነቡ ዘንድ ግብዣችንን እናቀርባለን። ኢንሻአላህ! መጽሐፉን በተመለከተና በውስጡ በተካተቱት ወሳኝ ነጥቦች ዙሪያ ከዚህ በኋላ ለእናንተ የምንሰጣቸው ተከታታይ ትምህርቶችና ማብራሪያዎች የሚቀጥሉ ይሆናሉ። መጽሐፉን ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ ገብታችሁ ማውረድ ትችላላችሁ! ሼር በማድረግ ለሁሉም ያድርሱ! https://t.me/Yahyanuhe/4578 https://t.me/Abuyusra3/564

Открыть в Telegram
Просмотры2050%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#6020Текст

ይህንን ኮሜንት ስመለከት የአንድ ሠለምቴ ታሪክ ትዝ አለኝ። ሠለምቴዋ በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ላይ ታሪኳን ስታካፍለን እነምህረትአብን በጣም እንደምትከተል እና ሙሥሊሞች ባየች ቁጥር እንደምትሳደብ ብሎም ሥለ እሥልምና ምንም እውቀት እንደሌላት እና ብቻ ባገኘችው አጋጣሚ እሥልምናን እንደምታጥላላ ነበር። ታዲያ እህታችን ብርቱካን በአጋጣሚ መምህሮች ቆርጠው እያብጠለጠሉ የነበረው የኡስታዝን አቡ ሃይደር ሙሉ ትምህርት ታገኘዋለች። ከዚያን ቀን ጀምሮ ከመምህሮቿ ስህተት እንዳለ እና እርሷም በእምነት ላይ እውቀትን ሳይሆን ጥላቻን የዘራች ሰው መሆኗን በማረጋገጥ በቀጥታ የእሥልምናን መምህራኖች ትከታተል ጀመር። ልጂቷ በክርስትና እምነት ላይ እያለች የትዳር አጋር ይሆነኛል የምትለው በጣም የምትወደውም ሰውም ነበራት ። መንገዷን ቀጠለች አንባቢ ሆነች በውስጧ የታመቁት ያለ እውቅና ጥላቻ መብነን ጀመሩ እውነት በልቧ መስረግ ጀመረ በመጨረሻም ሠለመች። ስትሰልም ህይወቴን አሳልፌ እሰጥሃለው ያለችውን የትዳር ጓደኛዋን ዞር በል እኔ እኮ ሙሥሊም ነኝ በማለት ታስደነግጠዋለች ልጁም በጣም ይወዳታል እና ለአንች ሥም እኔም ልስለም እና አብረን እንኑር በማለት መልስ ይሰጣታል። እሥልምና በልቧ ሰርጎ የተደላደለው ምርጥ ሴትም እንዲህ ስትል መልስ ትሰጠዋላች። እኔን ሳይሆን ጌታህን ፈርተህ ስለም እኔን ሳይሆን ነቢይህን ፈልገህ ስለም እኔን ሳይሆን ጀነትን ፈልገህ ስለም እኔን ሳይሆን ጌታህን እወቅ ከዚያ እኔን ታገኘኛለህ የሚል መልስ ሰጠች። ከልጁም እራቀች። ይህ ልጅ በቅጽበት እንዲህ ልትሆንበት የቻለችውን እምነት ማውምቅ አለብኝ በማለት መመራመር ጀመር በቆይታ እሥምልናንም ተቀበለ ። ለአንች ብዬ ሳይሆን የተፈጠርኩበትን እሥምናን ለእራሴ ስል ተቀበልኩ በማለት አበሰራት ።አሁን ተጋብተው አንድ ወንድ ልጅ ዑመር የሚባል ወልደዋል። እሥልምናን እንብቡት መልስ አለው እሥልምናን አድምጡት መልእክት አለው...! ✍️ ሳራ ነኝ ሰለምቴዋ https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg

Открыть в Telegram
Просмотры633+209%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#6017Превью ссылки

ማን ነው አህዛብ እኛ ወይስ እናንተ..? አንዳንድ ከእውቀት ነጻ የሆኑ ወይም ባይብልን ሳያነቡ በጭፉኑ ያለ እውቀት የሚሰብኩ የክርስቲያ እምነት መምህራን ሁሌም የሚናገሯት ቃል አለች እርሷም ሙሥሊሞችን አህዛብ እያሉ ሲጣሩ ወይም የራሳቸውን ሥምና ባህሪ ለሙሥሊሞች ለማልበስ ደፋ ቀና ይላሉ። https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg አህዛብ ማን ነው ካልን አህዛብ ሙሥሊሞች ሳይሆኑ እነዛ ከወርቅ ከብር ከእንጨት የተሠሩ ጣዖትን እና ስእላስእልን አምላኪዎች ናቸው ። ሙሥሊሞች አንዱን አምላክ በብቸኝነት የሚገዙ እና የነቢያትን ፈለግ ተከታይ እንጅ ጣዖት አምላኪ አይደሉም። አህዛብ” ተብሎ በግሪክ ብሉይ ሰፕቱአጀን እና በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ ላይ “ኤትኖስ” ἔθνος የሚለው የግሪኩ ቃል “ኤትኒኮስ” ἐθνικός ከሚለው ገላጭ የመጣ ሲሆን በዕብራይስጡ ደሃራይ እደ-ክታባት ላይ ደግሞ “ጎይ” גוי ተብሎ ተቀምጧል፤ ይህ ቃል እንደየ አውዱ ለተለያየ ትርጉም አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን “ህዝብ” “ብሔር” “አረማዊ” “ይሁዲ ያልሆነ” የሚል ፍቺ እንዳለው የግሪክና የዕብራይስጥ ሙዳየ-ቃላት ያትታሉ፤ ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እዚህ አርስት ላይ “አህዛብ” ብለን የምንመለከተው “አረማዊ”pagan” የሚለው እሳቤ ነው፤ ሰዎች ይህ ስም የአብርሃምን አምላክ ለሚያመልኩ ለሙስሊሞች እንደ ቅፅል ስም ሲጠቀሙ እጅግ ስላስደመመኝ ይህ ስም ማንን እንደሚመለከትና ማንን አህዛብ እንደሚል ለመፅሐፍ ቅዱስ ቦታውን እንልቀቅ፦ በመፅሐፍ ቅዱስ “የአሕዛብን ርኵሰት” ተብሎ የተቀመጠው ምዋርት፥ ሞራ ገላጭ፥ አስማት፥ መተተት፥ ድግምት፣ ጥንቆላ፥ መናፍስትንም መጥራት፥ ሙታን መሳብ ነው፦ ዘዳግም 18፥9-11 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ “”አሕዛብ”” የሚያደርጉትን “ርኵሰት” ታደርግ ዘንድ አትማር። ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ታዲያ ይህ በኢሥላም ትልቁ ሽርክ ነው። ከኢሥላም አጥርስ የሚያስወጣ አይደለምን? ይህንን ድርጊትስ ማን ነው በዘመናዊ መልክ የሚያደርገው ሙሥሊሙ ወይስ ስም ለጣፊው? አላህ የፈጠረው ተቃራኒ ፃታ”hetro-sexual” እያለ ዛሬ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሆነው ግብረ-ሰዶም”homo-sexual” ማድረግ የአሕዛብን ርኵሰት ነው፦ 1ኛ ነገሥት 14፥24 በምድርም ውስጥ “ሰዶማውያን” ነበሩ፤ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸውን “”የአሕዛብን ርኵሰት” ሁሉ ያደርጉ ነበር። ታዲያ ይህ በኢሥላም አይደለም መጋባት ይቅርና ድርጊቱ ሃራም ነው፤ ማን ነው ታዲያ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሚያጋባው ቤተክርስቲያን ወይስ መስኪድ? ህሊና ይፍረደዋ። ነቢያት “የአሕዛብ ልማድ” ብለው ያስቀመጡት ከእንጨት፣ ከብረት፣ ከብር እና ከወርቅ የተሰሩትን የተቀረፁ ምስሎች ነው፤ እነዚህ ምስሎች አፍ አላቸው አይናገሩም፤ ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፤ እጅ አላቸው አይዳስሱም፤ እግር አላቸው አይሄዱም፤ ክፉ መሥራትም አይቻላቸውም ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉም፣ አህዛብ ግን ወደ እነርሱ ይፀልያሉ፣ ይለማመናሉ፣ እጣን ያጨሳሉ፣ ይጎባደዳሉ፣ ያሸረግዳሉ፣ ይሰግዳሉ፣ -ያመልካሉ፦ 2ኛ ነገሥት17፥41 እነዚህም “አሕዛብ” እግዚአብሔርን ይፈሩ ነበር፤ ደግሞም “የተቀረጹ ምስሎቻቸውን” ያመልኩ ነበር፤ 2ኛ ዜና 16፥26 “የአሕዛብ አማልክት” ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። መዝሙር 115፥4-7 የአሕዛብ ጣዖታቶች “የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ” ናቸው፤ አፍ አላቸው አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው አያዩምም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤ በጕሮሮአቸውም አይናገሩም። ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ “ከአሕዛብ” ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ “የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት” የሚሸከሙና ያድን ዘንድ “ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ” እውቀት የላቸውም። ኤርምያስ 10፥2-5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና። “የአሕዛብ ልማድ” ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል። እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውማን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው። https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg ማን ነው የተቀረፀ ምስል አድርጎ ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት እና ለሶስቱ አካላት የአምልኮ ስግደት የሚሰግደው? በስዕልና በሃውልት ፊት የሚለማመን፣ የሚያመልክ፣ እጣን የሚያጨስ፣ ስለት የሚሳል? ሙስሊሙ ወይስ እውነተኛው አህዛብ? ህሊና እያለ ምን ይኮናል። 33 - 22 አማኞቹም አሕዛብን ባዩ ጊዜ «ይህ አላህና መልክተኛው የቀጠሩን ነው፡፡ አላህና መልክተኛውም እውነትን ተናገሩ» አሉ፡፡ (ይህ) እምነትንና መታዘዝንም እንጂ ሌላን አልጨመረላቸውም፡፡ ወደ ሙሥሊም ስንመጣ ሙሥሊም ማለት ሙሥሊም የሚለው ቃል አስለመ ታዘዘ ተገዛ አመለከ ሁሉ ነገሩን ሰጠ ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙ አቢድ ማለትም አምላኪ አሊያም ቃኒት ማለትም ታዛዥ ማለት ነው። እራሱን ለፈጣሪ ያስገዛና ትእዛዛቱን የፈፀመ ሰው ማለት ነው:: በዚህ ዙሪያ ያለውን የአምልኮ ስርአት በትክክል የሚተገብር ሰው ሁሉ ሙስሊም ይባላል። 2- 132 በርሷም (በሕግጋቲቱ) ኢብራሂም ልጆቹን አዘዘ፡፡ ያዕቁብም (እንደዚሁ ልጆቹን አዘዘ)፡፡ «ልጆቼ ሆይ! አላህ ለናንተ ሃይማኖትን መረጠ፤ ስለዚህ እናንተ ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ» (አላቸው)፡፡ 3- 102 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፡፡ እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ፡፡ ኢሥላም ማለት ደግሞ ለአላህ እጂ መስጠት ያለ ተቃውሞ መታዘዝ (ኢስቲስላም) አንድ ፈጣሪን በማምለክ የሚገኝ (ሰላም) ማለት ነው ። የአላህ ሃይማኖት ነው። አላህ ዘንድ ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡ አምላካችንን አላህን መገዛት እራስን ለአላህ ማስገዛት አላህን በብቸኝነት ማምለክ ነው ያዘዘውን መታዘዝ የከለከለውን መከልከል ሲሆን አምላካችን አላህ ነብያቶችን ሁሉ ያዘዘበት ሃይማኖት ኢስላም ብቻ መሆኑን ይነግረናል ። አህዛብ ከሓዲያን እንጅ አማኝ ሙሥሊም እንዳልሆነ መረዳት ይቻላል ።አህዛብ እነዛ የፈጠራን ሥራ የሚከተሉ እና ከአምላክ ዘንድ ታዋቂ ያልሆነውን እና ነቢያት ያልሰበኩትን እምነት የሚከተሉ ናቸው ። https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg

Открыть в Telegram
Просмотры638+211%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#6016Текст
Просмотры825+302%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
#6015Текст

ኡስታዝ ጀማል በሽር እና የታቦተ ጽዮን ትርክት! ከአመት በፊት ገደማ ኡስታዝ ጀማል በሽር አንድ አረብኛ ተናጋሪ ግለሰብ "የሙሴ የቃል ኪዳን ታቦት (ታቦተ ጽዮን) ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል" በሚል ስሜት የተናገረውን ቪዲዮ ወደ አማርኛ ተርጉሞና የራሱን አገላለጾች በመጨመር ሲያጋራ ተመልክተናል። ይህ ድርጊት በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ እንደ በጎ አቀራረብ ቢታይም፣ ከታሪክ፣ ከሥነ-መለኮት እና ከእውነተኛ ማስረጃዎች አንጻር ሲመዘን ግን ትልቅ ስህተትና ሚዛኑን የሳተ አካሄድ ነው። እንደ ኡስታዝ ጀማል ያለ በእስልምናውም ሆነ በሌሎች እውቀቶች ግንዛቤ አለው ተብሎ የሚታሰብ ሰው፣ የክርስትናውን አማኝ ስሜት ለማስደሰት (crowd-pleasing) ብቻ ሲል፣ በራሱ በክርስትናው መሠረታዊ መጽሐፍት ጭምር ውድቅ የተደረገን "ትውፊታዊ ተረት" አጉልቶ ማቅረቡ በእጅጉ ያሳዝናል። እውነታው ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ታቦተ ጽዮን ምን ይላል? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታቦቱ ወደ ኢትዮጵያ የገባው በንጉሥ ሰሎሞን ጊዜ (በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት) ነው ብላ ታስተምራለች። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ትርክት ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደርገዋል። እንዴት ካሉ ከዚህ በታች በዝርዝር እንመልከተው፦ • ከሰሎሞን በኋላ ከ300 ዓመታት በላይ ታቦቱ እስራኤል ነበር። ከሰሎሞን በኋላ 16ኛ ንጉሥ በሆነው በኢዮስያስ ዘመነ-መንግሥት ታቦቱ እዛው እስራኤል ውስጥ መኖሩን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይዘግባል፦ "እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት... እንዲህ አለ፦ ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም" (ዜና መዋዕል ካልዕ 35፥3)። • ለምን በትከሻቸው ይሸከሙት ነበር? ከኢዮስያስ በፊት ምናሴ በነገሰበት ዘመን ቤተ መቅደሱ ውስጥ ጣዖት አስገብቶ ስለነበር (ዜና መዋዕል ካልዕ 33፥7-8) ካህናቱ ታቦቱን ላለማስነካት ተሸክመውት ይዞሩ ነበር። ኢዮስያስ ይህን አስቁሞ ታቦቱን ወደ መቅደሱ መለሰው። እንግዲህ ታቦቱ በኢዮስያስ ዘመን (ከሰሎሞን ሞት 300 ዓመት በኋላ) በእስራኤል ከነበረ፣ "በሰሎሞን ጊዜ ኢትዮጵያ ገባ" የሚለው ትርክት መሠረተ ቢስ መሆኑን መጽሐፉ ራሱ ያረጋግጣል። የታቦቱ የመጨረሻ እጣ ፈንታ (በባቢሎን ምርኮ) በመጨረሻም እስራኤላውያን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር ሲወረሩ ቤተ መቅደሱ ፈረሰ፤ ንዋየ ቅዱሳቱም ተዘረፉ። • "የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ ታላቁንና ታናሹን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት መዝገብ... እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ... የእግዚአብሔርንም ቤት አቃጠሉ" (ዜና መዋዕል ካልዕ 36፥17-20)። በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ ብቻ ተቀባይነት ያለው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ በሆነው "መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል" ላይ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደተማረከና እንደጠፋ በግልጽ ሰፍሯል፦ • "...የእግዚአብሔርንም ማደሪያ ታቦትንም ከቤተ መንግስት ቤትም ያለውን ሳጥኑን ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱ" (ዕዝራ ሱቱኤል ካልዕ 1፥54)። • "...የህጋችን ማደሪያ ታቦተ ጽዮን እንደተማረከች፣ ንዋየ ቅዱሳት እንዳደፉ... ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ጽዮን እንደጠፋች ቀረች፤ ከሷም ንዋየ ቅዱሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎን እጅ ወደቅን" (ዕዝራ ሱቱኤል 9፥21-23)። የአክሱሙ ታቦትና የፓትርያርኩ ምላሽ ከጥቂት ዓመታት በፊት የአሁኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ጋዜጠኛዋ ታቦቱ በአክሱም ስለመገኘቱ አንስታ "እንደ ፓትርያርክ እርስዎ አይተውታል ወይ?" ብላ ለጠየቀቻቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ "አባቶቻችን አይተውታል፣ በእርግጥ እኔ እስካሁን አላየሁትም" ማለታቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። መስቀልም ሲመጣ "እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው" የሚባለውን ትውፊት ስንሰማ ይህ የፓትርያርኩ ንግግር እውነታውን ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል። ታሪካዊና ምሁራዊ ጥናቶችም "ክብረ ነገሥት" በተሰኘው የ14ኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ድርሳን ላይ ከተጻፈው ትውፊት ባለፈ፣ በአክሱም የሙሴ ጽላት መኖሩን የሚያረጋግጥ አንዳችም ታሪካዊም ሆነ አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃ አላገኙም። ለኡስታዝ ጀማል በሽር እና ለመሰል ወንድሞች የሚሰጥ ምክር ኡስታዝ ጀማል በሽር እንደ አንድ ሙስሊም ምሁር፣ እስልምና ስለ ታሪካዊ እውነታዎች የሚያስተምረውንና በተጨባጭ የታሪክ መዛግብት የተረጋገጠውን እውነት መከተል እንጂ፣ የሰዎችን ስሜት ለማስደሰት ሲባል የስህተት ትርክቶችን ማራገብ አልነበረበትም። በእስልምናም ቢሆን ቁርኣን ስለ "ታቡት" (የቃል ኪዳኑ ታቦት) ሲያወራ፣ ታቦቱ በእስራኤላውያን (በጧሉት/ሳኦል ዘመን) እጅ እንደነበር እና መላእክት ተሸክመውት እንደመጡ (ሱረቱል በቀራህ 2፡248) ይገልጻል እንጂ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመኖሩ የሚጠቁም ምንም አይነት ኢስላማዊ መሠረት የለም። የሌላውን እምነት ተከታይ ማክበርና አብሮ መኖር ማለት፣ የማናምንባቸውን መሠረተ-ቢስ የሆኑ ትውፊቶቻቸውን እንደ እውነት እያጋነኑ ማቅረብ ማለት አይደለም። ሃይማኖታዊ መቻቻል የሚገነባው እርስ በርስ መብትን በማክበር እንጂ፣ በነገረ-መለኮት እና በታሪክ ተቀባይነት የሌላቸውን ትርክቶችን በማዳነቅ አይደለም። ኡስታዝ ጀማልም ሆነ ሌሎች የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ከተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች ቪዲዮዎችን ሲተረጉሙ ታሪካዊ እውነታን፣ የነገረ-መለኮት ሚዛንን እና የምክንያታዊነትን መነጽር ሊጠቀሙ ይገባል። ከምንም በላይ ሙስሊምነት ደግሞ ለነዚህ ስራዎች ሁሉ ሚዛን መሆኑን አለመዘንጋት ተገቢ ነው። በኡስታዝ የህያ ኢብኑ ኑህ | ፌስቡክ | ዋትስአፕ |

Открыть в Telegram
Просмотры1 130+451%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#6013Текст

Переслано из የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

ውድ ወንድምና እህቶቼ፤ በጽሑፌ ላይ ጀማል በሽርን "ኡስታዝ" ብዬ በመጥራቴ ከብዙዎቻችሁ የተለያዩ ወቀሳዎችና ጥያቄዎች በኮመንት ደርሰውኛል። በዚህ ዙሪያ ያለኝን አቋም አጠር ባለች እና ግልጽ በሆነች መልኩ እንደሚከተለው ላስቀምጥ፦ የጽሑፉ ዋና ዓላማ የተላለፈውን የተሳሳተ ሐሳብና ትርክት በመረጃ ማረም እንጂ፣ ግለሰቡን ማዋረድ፣ ማበሻቀጥ ወይም ስብዕናውን ማጥቃት (Ad hominem Fallacy) አይደለም። የፈለገውን ያህል በሐሳቡ ባንስማማም፣ ስህተት ነው ብለን ያሰብነውን ትምህርት የወሰዱ ሰዎችን በጨዋ ደንብና በምክንያት ማቃናት እንጂ የስድብና የብሽሽቅ መንገድ የኛ መስመር ሊሆን አይገባም። "ኡስታዝ" የሚለው ቃል በቋንቋው "መምህር" ወይም "አስተማሪ" ማለት ሲሆን፣ በዓረቡ ዓለም የክርስትና ምሁራን ሳይቀር የሚጠሩበት የተለመደ የክብር መጠሪያ ነው። ጀማል በሽር እኔ እስከማውቀው ድረስ በመዲና የተማረና የሸሪዓ መሠረታዊ ዕውቀት ያለው ይህንንም ሲያስተምር የነበረ ሰው ነው። ከዚህ በፊትም ሲያስተምር ይጠራበት የነበረ ስም እንደመሆኑ፣ አሁን ላይ ባሉ አቋሞቹ በሐሳብ ስለተለያየን ብቻ ማዕረጉን ነጥዬ መግፈፍ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘሁትም። እርግጥ ነው፣ "ይህ መጠሪያ አይገባውም" ብሎ የሚያስብ ሰው በፈለገውና በሚመቸው መንገድ ሊጠራው መብቱ የተጠበቀ ነው። ለእኔ ግን የሰዎችን ስምና ማዕረግ በመንጠቅ የምናገኘው የሞራል ልዕልና የለም ብየ በማመኔ ሰዎች በሚያውቁት መጠሪያ መጥራትን መርጫለሁ። ​ዋናው ቁም ነገር፦ ግለሰቡ ያለው የትምህርት ዳራና ስም ቢኖርም፣ አሁን አሁን እየሄደባቸው ያሉ አንዳንድ መንገዶችና አቅጣጫዎች ከእውነት ጋር የማይግባቡ መሆናቸውን ግን አበክረን እንጠቁማለን። ስህተቶቹን ከነማስረጃው እያወጣን እንሞግታለን። ልዩነቶቻችንን በሰለጠነ፣ በጨዋ ደንብና በአደብ የማስተናገድ ባህልን በማዳበር፣ ትኩረታችንን ከግለሰቦች ይልቅ ሐሳቦች ላይ እናድርግ! ​ጀዛኩሙላሁ ኸይራ

Открыть в Telegram
Просмотры808+294%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#6012Фото

ትልቅ ውይይት ተብሎ ሲታወጅ የውይይቱ ቀን ደርሶ እስክንሰማው ምን እንደሚያሳስበኝ ታውቃላችሁ ? ያ ሰው እውነት ይመጣ ይሆን የሚለው ብቻ ። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ለውይይት ቀን ቀጠሮ ሳያከብሩ ወደ ኋላ ስለሚሸሹ ። የእነርሱ መምጣት ደግሞ የብዙን ሰው እይታም ስለሚቀይር ብዙ አላዋቂዎችም ትልቅ ትምህርት ስለሚወስዱ መምጣታቸው ያስደስተኛል ። እንጅ እሥልምና ውስጥ እማ ምን ጎድሎበት ለምንስ መልስ ጠፍቶ እሰጋለሁ? እርሱ እኮ ሙሉ ነው እርሱ እኮ ከአምላካችን ከአሏህ የተሰጠን ትልቁ እና ዋነኛው ፀጋ ነው ። ቁርኣን የእርሱ ቅዱስ ንግግር ነው ። ጠባቂውም ራሱ አምላካችን ነው። እኛ በእሥልምና እንከበራለን እውነተኞችም ሆነን በአለም እንታያለን። እሥልምና እውነተኛ የሰው ልጆች ሃይማኖት ነው ። እሥልምናም ሙሉ ነው ሁሌም ቢሆን በእርሱ እሸናፊዎች ሆነን እንጅ አፍረን እናውቅም በሙሉነቱ ልብን ሐሴት ያደርጋል ። እሥልምና በሰይፍ ተስፋፋ የሚል ሁሉ ሊያውቅ የሚገባው ኢሥላም በሰይፍ አልተስፋፋም ። ኢሥላም በእውነተኝነቱ ብቻ ባጢልን ያሸንፋል ይስፋፋልም ። ለዚህም እኛ ምስክር ነን እኛ ሠለምቴዎች እሥልምናን የያዝነው በሰይፍ ተማርከን ሳይሆን በእሥልምና እውነተኝነት ተማርከን ልባችን በእውነት ሐሴት ተሞልቶ ነው ። በሃይማኖት ማስገደድ የለም የሚለው አስተምሮ ከኢሥላም አስተምሮ ውስጥ አንዱ ነው ። አሏህ የተመሰገነ ይሁን ። የትላንቱ ውይይት ላይ ዳያቆን ዳዊት ለተጠየቀው ተገቢ መልስ ባይሰጥም ግን ለብዙዎች አድማጮች እይታን ገልጧል ። የሳላህም ንግግር ብዙዎችን አስደምሟል ።🙂 https://t.me/AshaBuleyamine

Открыть в Telegram
Просмотры561+174%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#6011Текст

የቱ ነው መጤው ክርስትና ወይስ እስልምና...! በጭፉኑ የሰውን እምነት ከማብጠልጠል ይልቅ ቅድሚያ እውቀት ይቀድማል ። አፋቸውን ሞልተው እስልምናን ማጠልሸት የለመደባቸው ሰዎች እውነት ስለ እስልምና አጥንተው ይሆን..! አይደለም። የሰው ልጅ ወደ ምድር መጣ እንጅ ምድር ወደ ሰዎች አልሄደችም ። ይህ ማለት ምድር የማንም አይደለችም ። የአንዱ ፈጣሪ ብትሆን እንጅ ። አንዱ አንዱን መጤ ማለት አይችልም...! አንዳንድ ደብተራዎች ሙሥሊሞች መጤ ናቸው የሚል ቃል ይወረውራሉ ። እውነት ሙሥሊም መጤ ነው..!? ሙሥሊም ማለት ምንድን ነው እምነቱስ...? እምነቱ ኢስላም ነው ። ኢስላም ማለት ለአንዱ አምላክ መታዘዝ ትእዛዙን ሁሉ መፈጸም ሲሆን ሙሥሊም ደግሞ ታዛዥ እና ትእዛዙን ፈጻሚው ሲሆን የነቢያቶችን ፈለግ የሚከተል ነው . .! ታዲያ ለአንዱ አምላክ መታዘዝና አንዱን አምላክ ብቻ መገዛት የተጀመረው ከነብያችን ﷺ ወዲህ ብቻ ነው እንዴ..!? ሌሎቹስ ነብያቶች ስለ አንዱ አምላክ አልሰበኩም...? አንዱን አምላክ አይታዘዙም ነበር...?! ይህ እምነት መጤ እንዴት ይባላል..!? ከአንድ ሃገር ወደ አንድ ሃገር መሸጋገር መጤ ካስባለ ጥሩ ። ሙሥሊሞች ተሰደው ወደ ኢትዮ መጡ እንጅ እምነቱ መች መጣ ታዲያ..!? እምነቱ ቅድሚያም እንዳለ አለ..! እንድ እምነት ወደ አንድ ሃገር የገባበት ታሪክና ወይም አምኮአዊ ነክ ነገሮች ከገቡ አዎ ያ እምነት መች እንደመጣና ምንጩ ከየት እንደሆነ ማወቅ እንችላለን ። ይህንን ስልን ሙሥሊሞች ኢትዮ ውስጥ ተሰደው ቢመጡ የትም ይሁኑ የት በብቸኝነት የሚገዙትና የሚሰግዱለት ለአንዱ አምላክ ብቻ ነው ።መለኮታዊ የሆንን ጣዖት በብር የተሰራ ወይም በወርቅ እንዲሁም ከእንጨት የተጠረበ የማይዳሰስ የማይሰማ ጣዖትን ይዘው አይዞሩም ወይም አልገቡም ። ወደ ክርስትና ስገባ ለምሳሌ 44ቱ ታቦት ከወርቅ ከብር እና ከእንጨት የተጠረቡ አሉ..! በተጨማሪ ስእላስእል ። 2ኛ ነገሥት17፥41 እነዚህም አሕዛብ” እግዚአብሔርን ይፈሩ ነበር ደግሞም የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ያመልኩ ነበር፤ 2ኛ ዜና 16፥ 26 የአሕዛብ አማልክት” ሁሉ ጣዖታት ናቸው ፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። መዝሙር 115 -4-7 የአሕዛብ ጣዖታቶች የወርቅና የብር የሰው እጅ ሥራ ናቸው፤ አፍ አላቸው አይናገሩምም ዓይን አላቸው አያዩምም ጆሮ አላቸው አይሰሙምም አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም እጅ አላቸው አይዳሰሱምም እግር አላቸው አይሄዱምም በጕሮሮአቸውም አይናገሩም። ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ” እውቀት የላቸውም። ኤርምያስ 10፥2-5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና። የአሕዛብ ልማድ” ከንቱ ነውና ዛፍ ከዱር ይቈረጣል በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል። እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም መራመድም አይቻላቸውማን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው። ማን ነው የተቀረፀ ምስል አድርጎ ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት እና ለሶስቱ አካላት የአምልኮ ስግደት የሚሰግደው? በስእልና በሃውልት ፊት የሚለምን የሚያመልክ..!? መልሰው ሙሥሊሞችን አሕዛብ ብለው ሲሳደብ ሳይ ይገርመኛል ..! 🔵 ቀጣይ ዘጠኙ ቅዱሳን ። ዘጠኙ ቅዱሳን ኢየሱስን ይጠሉትና ይቃወሙት ከነበሩት ሃገራቶች መካከል ከሮም ከእስያ ከአንጾኪያ ከቁስጥንጥንያ ከቂሳርያና ከኪልቂያ በስደት የመጡ ናቸው። ቀስ በቀስ ወደ ኢትዮ በምሪት ገብተዋል እንደገቡም ክርስትናን ሰብከዋል ። እነርሱም ፦ 1.አባ አሌፍ፦ 2.አባ አረጋዊ፦ 3.አባ ጰንጠሌዎን፦ 4.አባ ገሪማ፦ 5.አባ ጽሕማ፦ 6.አባ አፍጼ፦ 7.አባ ሊቃኖስ፦ 8.አባ ይምዓታ ፦ 9.አባ ጉባ ይባላሉ። ዘጠኙ ቅዱሳን በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት እንዲስፋፋ ከፍተኛ አስተዋፆ አድርገዋል ። አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል ነው ነገሩ ። በእውነት ላይ ሀሰትን ለመጣል ከመሮጥ ሀሰትን በእውነት ለመቀር ይጣሩ....! https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg ✍ሳራ ነኝ ሰለምቴዋ

Открыть в Telegram
Просмотры667+225%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#6003Текст

የሰሞኑን "ሥላሴ ጾታ አለው" ውዝግብ ተከትሎ የቀረበው ይቅርታና የተደረገው ማስተባበያ፣ አንድ እጅግ መሠረታዊ የሆነ የሥነ-መለኮት ጥያቄን በውስጡ አምቆ ይዟል። "መለኮት ረቂቅ ነው፣ ጾታ የለውም" የሚለውን አጠቃላይ መርህ ለማስጠበቅ ሲባል የሀይማኖት አባቱ በደቦ ቢወገዙም፣ የቤተ ክርስቲያኗ የራሷ የሆነው የነገረ-ክርስቶስ ዶክትሪን ግን ከዚህ ጋር የሚላተም ሌላ ግዙፍ እውነታን እንደሚያነሳ መረሳት የለበትም። ይኸውም፣ ሥላሴዎች በአንድነታቸው ጾታ የላቸውም ቢባል እንኳ፣ ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነው «ወልድ» ሥጋን በመልበሱ ምክንያት የተሟላ የወንድነት ጾታ እንደነበረውና ግዝረትንም እንደፈጸመ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል። የክርስትና አስተምህሮ "እግዚአብሔር ቃል (ወልድ) ሰው ሆነ" ብሎ ሲያምን፣ ሰው የሆነው ጾታ በሌለው ረቂቅ ማንነት ሳይሆን፣ በተጨባጭ የወንድነት ተፈጥሮ ነው። ይህንንም የሉቃስ ወንጌል 2፡21 በሚከተለው መልኩ ያረጋግጠዋል፦ "ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።" ይህ አንቀጽ፣ ኢየሱስ (እንደ ክርስትናው እምነት አምላክ የሆነው ወልድ) የተሟላ የሰውነት አካልና የወንድነት ጾታ እንደነበረው ማረጋገጫ ነው። ግዝረት ደግሞ በቀጥታ ከወንድ ልጅ የመራቢያ አካል ጋር የተያያዘ ሥርዓት በመሆኑ፣ የአንዱ የሥላሴ አካል (ወልድ) ጾታ ባለቤትነት ፈጽሞ ሊካድ የማይችል ሃይማኖታዊ እውነታ ነው። ይህን የሥነ-መለኮት አጣብቂኝ የቀደምት አባቶችና የስኮላስቲክ ሊቃውንት በጥልቀት ተከራክረውበታል። በነገረ-ክርስቶስ ጥናት ውስጥ፣ "የባሕርያት መለዋወጥ" (Communicatio Idiomatum) የሚባል መሠረታዊ መርህ አለ። ይህ መርህ "መለኮት የሥጋን ገንዘብ የራሱ አደረገ፤ ሥጋም የመለኮትን ገንዘብ የራሱ አደረገ" የሚል ነው። የእስክንድርያው ሊቅ ቄርሎስ "ተዋሕዶ" በሚለው ጽንሰ-ሐሳቡ፣ ቃል (ወልድ) ሥጋን ሲለብስ የሥጋን ባሕርይ (ጾታን፣ መወለድን፣ መራብን፣ መገረዝን) ሙሉ በሙሉ የራሱ (ገንዘቡ) እንዳደረገ ያስተምራል። በተመሳሳይ፣ እንደ ቶማስ አኩዊናስ ያሉት የኋለኛው ዘመን ስኮላስቲክ ሊቃውንትም፣ ክርስቶስ የተሟላ ሰብዓዊ ተፈጥሮን (ወንድነትን) መላበሱን በስፋት አብራርተዋል። በነዚህ አባቶች ትምህርት መሠረት፣ "ተገረዘ" የተባለው ተራ ሥጋ ሳይሆን፣ ራሱ አምላክ የሆነው ወልድ ነው። እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ትልቁ የሎጂክ እና የሥነ-መለኮት ቀውስ ወይንም ፓራዶክስ የሚፈጠረው። ዛሬ ላይ የሶሻል ሚዲያው መንጋ "እግዚአብሔር እንዴት ጾታ አለው ይባላል?" ብለው የነገረ-መለኮት ቅንዓት ያደረባቸው መስለው ሲቆጡ፣ የራሳቸውን መሠረታዊ ቀኖና በሚገባ ያልተረዱ መሆናቸውን ያሳብቃል። ሥላሴን በአንድነት "ጾታ አልባ" ብሎ መደምደም፣ "ሰው ሆነ" የተባለውን አንዱን አካል (ወልድ) ተፈጥሮአዊ ማንነት ከመካድ ጋር እኩል ነው። የሃይማኖት አባቱ "ሥላሴ ጾታ አለው" በማለታቸው ቢወገዙም፣ ቢያንስ አንደኛው አካል በምድር ላይ በነበረው ቆይታ የተሟላ የጾታ መገለጫና የመራቢያ አካል (ለግዝረት የበቃ) እንደነበረው መዘንጋት ግን የለበትም። ስለሆነም ሥላሴ በጅምላ ጾታ የላቸውም ብለህ ስለተናገርክ እግዚአብሔር ጾታ እንደነበረው ከማመን መሸሽና ማምለጥ ግን አትችልም..! © የሕያ ኢብኑ ኑህ

Открыть в Telegram
Просмотры1 080+427%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#6000Текст

Переслано из Eliyah Mahmoud

ከሰሞኑን የኦርቶው ስብስብ በስላሴ ባሕራያት ዙሪያ እርስ በርስ መነታረክ ይዟል። ከነርሱ ጋር በተደረገ አንድ ውይይት ሙስሊሙን ወክሎ የገባው ተወያይ አንዳንድ ከአላህ ባሕሪያት አኳያ ለተነሱለት ጥያቄዎች አልተገለጸም እያለ መመለሱ አስፈንጥዟቸው ነበር። እንዴት ማንነቱ ያልተገለጸ አምላክ ታመልካላችኹም እያሉ ሲያፌዙ ቆዩ። በኋላ ላይ ጉዳዩ በራሳቸው ላይ ሲነሳና ሊቃውንታቸውም "ለሰው ያለው ኹሉ ጾታን ጨምሮ ለስላሴም አላቸው" ብለው መጨቃጨቅ ጀመሩ። ይሕንን አስተምሕሮ ተከትሎ ራሱ ከሙስሊሙ ጋር ሲወያይ የነበረው ግለሰብ በሚዲያ ብቅ ብሎ "ለሰው ያለው ኹሉ ለእግዚአብሄር አለው" የሚለውን አስተምሕሮ እንደማይቀበል አወጀ። መቼም ቢኾን ሰው አምላክ አንድም ሶስትም ነው፤ ሰውም አምላክም ነው፤ ብሎ ሊስማማም ሌላውንም ሊያሳምን አይችልም። ኦርቶዎቹ አኹን ላይ ሚዲያ ላይ እያደረጉት ያለው ውይይት እንደ ቀድሞው ውይይቶቻቸው በድምጽ ብዛት ወደ አንድ አቋም ካልመጡ በስተቀር በፍጹም አይስማሙም። https://t.me/E_M_ahmoud

Открыть в Telegram
Просмотры1 140+456%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#5998Текст
Просмотры681+232%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—