Кабинет
አርምሞ🧘🏽‍♂

አርምሞ🧘🏽‍♂

ጥ ቂ ት ም ና ኔ. .🧘🏽‍♂️

Юзернейм
@armemo_offical
Категория
Блоги
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики12 284
Просмотров на пост, 7 дн.1 938−35,5% к пред. 7 дн.
ERR15,77 %Са 7 дноК

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
8 нояб. 2026 г.2 870
9 нояб. 2026 г.2 520
10 нояб. 2026 г.2 745
11 нояб. 2026 г.2 900
12 нояб. 2026 г.2 780
15 нояб. 2026 г.4 420
20 нояб. 2026 г.2 565
21 нояб. 2026 г.1 500
22 нояб. 2026 г.1 120

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры4,42 тыс.
    Пересылки—
    Реакции33
    Комментарии—
  2. 02

    🗣 ለሚኖር መሰንበት አጥሮ ፥ ሰባና ሰማንያ 'ራቀው በለሱን አንቆሮ ተፍቶ ፥ በዋጠ ማግስት አነቀው፤ ሙታንም ለራስ አንብቶ ፥ በቁሙ ህይወት ተራበ ሰማየ ሰማያት ሲመኝ ፥ ከጽድቁ ውድቁ ቀረበ፤               ያ ምስኪን ድሃ ገበሬ               ቢጸልይ ለመኖር ዛሬ               ምሽቱን ሽፍታ ላከበት               ተኝቶ በደረቅ ቁርበት             ቀረለት ዛሬን መሰንበት         ማጣት ላይ ሞት አክሎበት። እናማ እንዲህ ቢገጥመው ፥ አምላኩን ቆሞ ከሰሰው አምላክም የዋዛ አይደለም ፥ ድጋሚ በመኖር ካሰው፤ መታተር የማይሰለቸው ፥ ይህ ምስኪን ድሃ ገበሬ ሰማይን ዝናብ ሲለምን ፥ ማዕልቱን አጥምዶ በሬ ምሽቱን ገዳይ ላከበት ፥ ከስቃይ ሊገላግለው አምርሮ አምላኩን ሲከስ ፥ ዘላለም ህይወት አደለው። ነገር ግን ደስ አላለውም ፥ አምርሮ ቃሉን ደገመ      በስጋው ስቃይ የበላ ፥ ከነፍሱ ያላገገመ ድጋሚ መኖር መቀጣት ፥ መሰንበት የተረገመ..   ነገር ግን ደስ አላለውም ፥ ይልቅ ይህን አነሳ      በደሌን ይቅር ብትለኝ ያንተንም እንደምረሳ     አባት ሆይ ፈተና በቅቶ ፥ ከክፉ የምታድነን ሞት የለሽ ሞት እየሰጠ ፥ መከራን 'ምትገላግለን ዘላለም ህይወት ሰርዘ ፥ ከመኖር ቀድመ ስትገድለን!             @Imagination_officially

    Фото
    Просмотры3,57 тыс.
    Пересылки—
    Реакции35
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры3,5 тыс.
    Пересылки—
    Реакции86
    Комментарии—
  4. 04

    ላይብረሪ እየሄዳችሁ መፅሐፍ ካነበባችሁ ስንት ግዜ ሆናችሁ?። ይህን የሾፐንሃወር መፅሐፍ እንደጸበልተኛ እየተመላለስኩ አንብቤ ዛሬ ገና መጨረሴ ነው። ባለፈው «DEATH COMES TO SCHOPENHAUER» ጠቅሼ አብራርቼ ነበር። ዛሬ ደግሞ ባለፈው ሳልናገረው ካለፍኩት ቅር ያለኝን ላጋራችሁ። አርተር ሾፐንሃወር ስለ ሞት ያለውን አስተሳሰብ በጥልቀት ሲገነዘብ «ከሞት በኋላ ምን ይሆናል?» የሚለውን አልነበረም የጠየቀው። ይልቅ «ከመወለዳችን በፊት ምን ነበርን?» ነው የሚለን። እስቲ አስቡት፤ ከመወለዳችን በፊት ለሚሊዮን ዓመታት በዚች ምድር ላይ አልነበርንም። ዓለም ግን እኛ ከመኖራችን በፊት በራሷ ሕልውና ስር ቀጥላለች። ዋናው የሞትን ምንነት የምንረዳበት መንገድ ይህ ነው። ከመወለዳችን በፊት ሞትን እንደ ስቃይ፣ እንደ ኪሳራ ወይም እንደ ፍርሃት አልተረዳነውም። ምክንያቱም ለመፍራትም ሆነ ለመጠየቅ እኛ በዛ አልነበርንም ነበር። እዚህ ላይ ሾፐንሃወር የሚያነሳው ሀሳብ እጅግ አስደናቂ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እሱ የሚለን ከመወለዳችን በፊት ባለመኖራችን ውስጥ ለዘመናት ኖረናል ነው። በዚያ አለመኖር ውስጥ ሞት ወይም የሞት ፍርሃት አልነበረም። ለዛም ነው ሞት ለእኛ ፈጽሞ እንግዳ ነገር አይደለም የምላችሁ፤ ይልቅ ሞት ወደቀድሞ አለመኖር የምንመለስበት ድልድይ ነው። በሌላ አነጋገር ከመወለዳችን በፊት ባለመኖር ውስጥ ያሳለፍነውን ዘላለማዊነት እንደ ሞት መቁጠር ብንችል ኖሮ ሞት የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ከምናስበው በላይ የተለመደ የህይወት ክፍላችን ይሆን ነበር። በእርግጥ እኛ ያንን አለመኖር በንቃተ ህሊና አልተለማመድነውም፤ ቢሆንም ግን ለምንድነው ከመወለዳችን በፊት የነበረው አለመኖር የማያስፈራን? ወይም ከሞት በኋላ ስለሚመጣው ነገር ለምን እንጠይቃለን?። መልሱ ያለው የሞት ምንነት ላይ ሳይሆን ከሕይወት ጋር በፈጠርነው ቁርኝት ውስጥ ተቀምጧል። አሁን ማንነት አለን፤ ትዝታዎች፣ ፍላጎቶች፣ ምኞቶችና የወደፊት ዕቅዶች አሉን። ራሳችንን ከእነዚህ ሁሉ ውጭ ማሰብ ይከብደናል። ስለዚህ የምንፈራው አለመኖርን ብቻ ሳይሆን አሁን ያለንን ማንነት የማጣት ሃሳብንም ጭምር ነው። ባንኖር ኖሮ አለመኖራችን ጥያቄ የሚያስነሳ ስጋት አይሆንም ነበር። ይህን ለመረዳት የአርተር ሾፐንሃወር «The World as Will and Representation» የሚለውን መፅሐፍ ማንበብ ያስፈልጋችኋል። እዚህ መፅሐፍ ላይ ሾፐንሃወር በስፋት የሚናገረው ስለWill/ፈቃድ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚያነሱት ጥልቅ የፍልስፍና ጥያቄዎች እነዚህ ናቸው፦«በእውነት የሚሞተው ማን ነው? ግለሰቡ ወይስ ከግለሰቡ በስተጀርባ ያለው የመኖር መሠረታዊ ፈቃድ?» በThe World as Will and Representation ከገፅ54 ጀምሮ ሾፐንሃወር ዓለምን «Objectification of the Will» የፈቃድ መገለጫ አድርጎ ያቀርባታል። በእሱ አስተሳሰብ Will ማለት የሰው የግል ፍላጎት ወይም በአዕምሮ የሚደረግ ውሳኔ ብቻ አይደለም፤ ይልቅ ከአዕምሮ እና ከንቃተ ህሊና በፊት ያለ፣ በመላው ተፈጥሮ ውስጥ የሚገለጥ የማያቋርጥ የመኖር ግፊት ነው። ሰው ይህንን ፈቃድ ከሚገልጡ የተፈጥሮ ፍጥረቶች መካከል አንዱ ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ የደነቀኝ አንድ የሾፐንሃወር ሐሳብ አለች። ሃሳቡም የግለሰብ ሕይወት የሚጀምረውና የሚያበቃው በጊዜ ውስጥ ነው። መወለድና ሞት የዚህ ጊዜያዊ ሕልውና ሁለት ወሰኖች ናቸው። ነገር ግን «ፈቃድ» በጊዜ፣ በቦታና በግለሰባዊ መለያየት የማይገደብ የዓለም ውስጣዊ መሠረት ነው ይለናል። ያም ማለት አንድ ሰው ሲሞት የሚያበቃው ነገር በዚያ ሰው ውስጥ ይገለጥ የነበረው የመኖር ፈቃድ ብቻ ነው። ሰው የመኖር ምርጫውን በገዛ ፈቃዱ አይመርጥም። መምጣት ሳንፈልግ ነው የተወለድነው፤ በተመሳሳይ መልኩ መሄድ ሳንፈልግ እንሞታለን። በመኖር እና በመሞት መካከል የምኖረው ህይወት በራሱ የእኛ ፈቃድ የሌለበት በትዝታ፣ በስሜት፣ በምንወዳቸው ሰዎች እና ሁኔታዎች የታጠረ የነፃ ፈቃድ እስረኞች አድርጎናል። ነፃ-ፈቃድ ማለት ፍጹም ነፃነት አይደለም። ይልቅ ቀድሞ በተቀመጠልን ፈቃዶች መካከል የመምረጥ ነፃነት አለን ማለት ነው። በድጋሚ በመፅሐፉ ምዕራፍ 41 ላይ «On Death and its Relation to the Indestructibility of our Essence in Itself» የምትል አርዕስት አለች። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ሾፐንሃወር ሞትን የግለሰብ መጥፋት ብቻ አድርጎ አይመለከተውም፤ ከግለሰባዊ ሕልውና በላይ ያለውን የተፈጥሮ እረቂቅነት ያብራራልናል። ከእዚህ ቀጥሎ በምዕራፍ 42 «Life of the Species»  ላይ ደግሞ ትኩረቱን ከግለሰባዊነት ወደሰው የዘር ፍጥረት ይቀይረዋል። ሰዎች ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ፤ የተፈጥሮ ሕይወት ግን በአዲስ ሰዎች መገለጧን ትቀጥላለች ይለናል። አንድ ሰው ይህን ማሰብ መቻሉ ሞትን ባያስቀርለትም፤ የእሱ መሞት ግን በዓለም እና በሌሎች ዘንድ እንብዛም ተጽህኖ የማይፈጥር እውነት መሆኑን ይገነዘባል። ይሁንና ሾፐንሃወር የመኖር ፈቃድን ለዘላለም የሚያስደስት ኃይል ነው እያለን አይደለም። ይህንኑ ደግሞ በምዕራፍ 46 «On the Vanity and Suffering of Life» ላይ መኖር ከፍላጎት፣ ከእጦትና ከሥቃይ ጋር የተሳሰረ መሆኑን ያብራራል። ያን ያለበት ምክንያትም Will ሁልጊዜ ፈላጊ ስለሆነና አንዱ ፍላጎት ቢሟላለትም ሌላኛው ይቀሰቀስበታል። ስለዚህ ሕይወት የሆነ ግዜ ላይ የምታበቃ ፍላጎት ሳትሆን በተደጋጋሚ የምትመላለስ የመፈለግ እና ያለመፈለግ ሂደት ናት። በድጋሚ በምዕራፍ 48 «On the Doctrine of the Denial of the Will to Life» ደግሞ ከዚህ የማያቋርጥ ፍላጎት እንዴት መላቀቅ እንችላለን የሚለውን ከመንፈስ እና ከፍልስፍና ጋር አጣምሮ ያስረዳናል። በመጨረሻም የሾፐንሃወር የሞት ፍልስፍና ዋና ጥያቄ አድርጌ የምወስደው፦«አንድ ሰው ከሞት በኋላ ወዴት ይሄዳል?» ሳይሆን፤ «ያ ሰው ከግል ማንነቱ ጋር ለምን ይለያያል?» የሚለው ነው። ሞትንም የምንፈራው የመኖር ፈቃዳችንን ስለሚያጠፋው ብቻ አይደለም፤ ይልቅ ያ ፈቃድ በእኛ ውስጥ የፈጠረውን የግል ዓለም ለመልቀቅ ስለሚከብደን ጭምር ነው። እኛ ራሳችንን ለዓለም አስፈላጊ ፍጡር አድርገን ብንቆጥርም፤ ሞት ግን ዓለም ያለእኛ መቀጠል እንደምትችል የሚያሳየን ሌላኛው የህይወት መስታወታችን ነው። Maybe the greatest mystery of death is not what comes after it, but why we fear returning to a state in which we once existed without even knowing it 🙂 ይህን መፅሐፍ አንብቤ የጨረስኩት ዛሬ ነው። በማነብበት ሰዓት አንድ ጥያቄ ተፈጥሮብኝ ነበርና እናንተን ልጠይቃችሁ ወደድኩ፦«እኛ ሳንፈልግ ወደዚህ ዓለም ከመጣን እና ሳንፈልግም ከዚህ ዓለም ከሄድን በሁለቱም ላይ የእኛ ፈቃድ የለም። ታድያ በመወለድ እና በመሞት በመካከል ያለውን አሁን የምንኖረውን ሕይወት በእኛ ፈቃድ እየመራነው ነው? ወይስ እኛን እየመራን ያለው ዕውር የመኖር ፈዳችን Will-to-Live ነው?» @Armemo_offical

    Текст
    Просмотры3,21 тыс.
    Пересылки—
    Реакции56
    Комментарии—

Новые посты

#6180Текст

ከ11 ወራቶች በፊት ስለ PRISON MINDSET አንድ አርቲክል ጽፌ ነበር። ይህ ጽሁፍ ዝም ብሎ የተጻፈ አይደለም። የክፍለ ሃገር ልጅ ሆኖ ጥይት የማይተኩስ ወንድ የለም እንደሚባለው ሁሉ የአዲስ አበባ ልጅ ሆኖ እስርቤትን ቀምሶ የማያውቅ ወንድ የለም። ይህን ስል Real የጎዳና ህይወትን የኖረ ዱርዬ የሸገር ልጅን እየጠቀስኩ ነው። ደግሞ እስር ቤት መግባት የእርድና ምልክት ነው እያልኩ አይደለም። ይልቅ እዛ ውስጥ መግባት የሚያስተምር የህይወት ክፍል አለው እያልኩ ነው። እንደኔ አይነቱ እዛ ከመመላለሱ ብዛት ትምህርት ይማርበታል። አንዳንዱ ደግሞ እየተመላለሰ እድሜ ይጨርስበታል። እንደ ሁለተኞችሁ መሆን ሙሉ ለሙሉ ኪሳራ ነው። አንዳንዴ ሰዎች ጥፋት ሲያጠፉ ማረሚያ ቤት መክተት፤ የባሰ ሆነው እንዲወጡ ማመቻቻ መንገድ ነው። ምክንያቱም በሌብነት የገባው ከእሱ የባሰ ሌባን እስር ቤት ውስጥ ስለሚያገኝ የበለጠውን ተምሮ እንዲወጣ ምክንያት ይሆነዋል። እኔ እያወራው ያለውት PRISON MINDSET በእስር ቤት ውስጥ መሆን ብቻን መቅረት እንደሆነ ለማመላከት ነው። እዛ ውስጥ የሚያግዝልን ታላቅ ወንድም የለም ወይም የምታስብልን እናት የለችም። እኛን በጉልበት የሚበልጡን ሰዎች የግል ድንበሮቻችንን የማለፍ መብት አላቸው። እራስን ለማትረፍ ብቻ ሳይሆን በዛ ቦታ ተከብሮ ለመቆየት አንድ ወንድ ሰውነቱን በስፖርት፣ መንፈሱን በማይበገር እምነት፣ ዓይኑን ደግሞ በአራቱም አቅጣጫ ለሊት እንኳን ሳይቀር ንቁ አድርጎ መጠበቅ አለበት። ዛሬ የመጣውት ስለ «Survival of Struggle» በአጭሩ ላወራችሁ ነው። በህይወት ጉዞ ውስጥ ውድቀታችን ቢበዛም ማንም ስለኛ ግድ አይሰጠውም። ምክንያቱም እኛ ወንድ ነን!። ሰዎች ስለኛ የሚያወሩት አሸናፊ ሆነን ከቆየን ብቻ ነው!። አንዲት ሴት መልክ ስላላት ብቻ በአለም ደረጃ እውቅናን ታገኛለች ወይም ምንአልባት ጥሩ የሆነ የሰውነት አቋም ስላላት የተሻለ ህይወት ይኖራታል። ወንድ ጋር ግን ይህ ጉዳይ ጌጥ ብቻ ነው። ወንድነትና የመኖር ትግል የማይነጣጠሉ የህይወት ክሮች ናቸው። ወንድ ልጅ ሆኖ ወደዚህ ዓለም መምጣት ብቻውን የሕይወት ዋስትናን በእራስ ላይ መጣል ነው። ከልጅነት እስከ ጉልምስና ድረስ የሚጠብቁት ፈተናዎች ብዙ ናቸው። አንዳንዱ በገንዘብ፣ አንዳንዱ በማኅበራዊ ግፊት፣ ሌላው ደግሞ በአካላዊ ጥንካሬና በሥነ-ልቦናዊ ጽናት ፈተና ያበዛበታል። ይህች ዓለም ለወንድ የምትሰጠው ርህራሄ ሳይሆን የማያልቅ ፈተናን ነው። በከተማ መሃል በሚገኙ ጎዳናዎች ላይ ያደገ ወጣት የሚያጋጥመው ማኅበራዊ እውነታ ምን ያህል የተለየ እንደሆነ አስተውላችሁ ታውቃላችሁ። የፖለቲካ ግፊት፣ የጎዳና ግጭቶች፣ የጉልበት ማሳያ ፌስቱ ፌስ፣ የጀማ ጸቦችና የማኀበረሰቡ የመኖር መስፈርት ማስፈራሪያዎች የዕለት ተዕለት ክስተቱ ነው። በእንዲህ ያለ አካባቢ ራሱን የማይንከባከብ፣ አካሉን የማያጠናክርና የራሱን ድንበር መጠበቅ የማይችል ሰው ለብዝበዛና ለግፍ ተጋላጭ የሆነ ልፍስፍስ ይሆናል። ስለዚህ Physical Strength ለወንድ ልጅ የጌጥ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ ራስን ለመጠበቅና በራስ መተማመንን ለመገንባት አስፈላጊ መሠረቱ ነው። እዚህ ጋር እንድታስተውሉ የምፈልገው፤ ወንድነት በጡንቻ ብቻ እንደማይለካ ነው። የሰውነት ጥንካሬ እንዳለ ሁሉ የአዕምሮ ጥንካሬም ግድ ነው። በዛ ላይ ገንዘብ የሌለው ወንድ በብዙ ማኅበራዊ ሁኔታዎች የሚያጋጥመው ጫና ከባድ ይሆንበታል። በዚህ ዓለም ገንዘብ የምርጫ ነፃነትን፣ የመኖር አቅምንና የራስን ውሳኔ የመወሰን ነፃነት የሚሰጥ መሳርያ ነው። ሥራ የሌለው፣ የራሱን ኑሮ ለመምራት ያቃተው ወጣት በሌሎች ላይ ጥገኛ ለመሆን ይገደዳል። ወንድ ልጅ በማኅበረሰቡ ዘንድ ያለው ጥቅም በሚያመጣው ነገር ላይ ይመዘናል። ስራ የሌለው ወንድ እንደ እንደማያገለግል ዕቃ ወደውጭ ይጣላል። ወይም ደግሞ እንደትርፍ ቁስ በቤት ይቀመጣል። ለዛም ነው ገንዘብ እና ጥንካሬ ለወንድ ልጅ ከቁሳዊ ነገሮች በላይ የሕይወት መሠረታዊ መሣሪያዎች የሆኑት። አንደኛው የኑሮ ነፃነት ሲሰጠው፤ ሌላኛው ደግሞ ራሱን የሚጠብቅበት አቅም መገንቢያው ነው። ታዲያ ግን ከዚህ ሁሉ በፊት አንድ የወንድነት ባህርይ መገንባት ግድ ይለናል፤ እርሱም «SILENCE» ዝምታ ይባላል። ሁሉንም ነገር ለሁሉም ሰው ማስረዳት አያስፈልግም። ሁሉንም ትችት መመለስ፣ ለሁሉም ስድብ መመለስና በየትኛውም ግጭት ውስጥ ድምፅን ማሰማት ጥንካሬ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ዝም ብሎ ማለፍ ከሺህ ቃላት የበለጠ ክብር ያለው ወንድነት ነው። የሰው ልጅ ስለራሱ የሚያውቀውን እውነት ለሌሎች ለማረጋገጥ በየቀኑ መጣሩ የድክመት መገለጫው ነው። በመጨረሻም የSurvival Mindset ዋና ትርጉም ሌሎችን ማሸነፍ ሳይሆን በራስ ላይ ድል መቀዳጀት ነው። የራሱን ገንዘብ የሚያገኝ፣ ሰውነቱን የሚንከባከብ፣ አዕምሮውን የሚያሰለጥን፣ ስሜቱን የሚቆጣጠርና ክብሩን የማያስነካ ወንድ በሕይወት ውስጥ የራሱን ቦታ የገነባ ጀግና ነው!። «A man must learn to survive before he learns to live» ይላሉ ፈረንጆች። አተ! ዓለም ቆማ አትጠብቅህም፤ ሰዎችም ሁልጊዜ አይረዱህም፤ ስለዚህ ራስህን በአካል፣ በአዕምሮና በኢኮኖሚ ገንባ። ምክንያቱም በዚህ የሕይወት ትግል ውስጥ ከሁሉም በላይ ልትተማመንበት የምትችለው ብቸኛ ሰው አንተና አንተ ብቻ ነህ!!።               What's important now Win! 🔥 @Armemo_offical

Открыть в Telegram
Просмотры1 120−58%к среднему
Пересылки—
Реакции27
Комментарии—
#6179Фото
Просмотры1 500−44%к среднему
Пересылки—
Реакции56
Комментарии—
#6178Текст
Просмотры2 570−4%к среднему
Пересылки—
Реакции53
Комментарии—
#6176Текст

COMING SOON 📖 እንኳን ደስ አለኝ «እሳት የወለደችው ሞት» የተሰኘ የመጀመሪያ የበኩር መፅሐፌን በቅርቡ ላንባቢ አደርሳለሁ። ከረጅም ጊዜ የጽሑፍ ጉዞ በኋላ የመጀመሪያ መጽሐፌን ወደ ማጠናቀቅ አድርሻለሁ። ጥቂት የመጨረሻ ማስተካከያዎች ብቻ ይቀሩኛል። «እሳት የወለደችው ሞት» የህልውናዊ ግጥሞችን (Existential Poetry) አጫጭር ትረካ ድርሰቶችን (Short Prose) እና ዕለታዊ የዕውነት ማስታወሻዎችን (Aphoristic Reflections) የያዘ የሥነ-ጽሑፍ ሥራ ነው። በመጽሐፉ ውስጥ የአንድ ገፀባህርይ ድምፅ በተለያዩ የጽሑፍ ቅርጾች ይመላለሳል። ይህ የመጀመሪያዬ መጽሐፍ ሲሆን በዲጂታል ቅርጽ (PDF Edition) ለአንባቢዎች የማቀርበው ይሆናል። ያም የሆነበት ምክንያትን አሳታሚ ማጣቴ ነው። በየወሩ ልዩነት በፌስቡክ ፕላትፎርም ብዙ ሰዎች መፅሐፍ አሳተምኩ እያሉ ብቅ ይላሉ። እንደውም በአመት ውስጥ ሦስቴም የሚያሳትሙ አልታጡም። በተለይ ሴቶችሁ የተለየ ቦታ ነው የሚሰጣቸው። በዚህ አንድ ነገር ነው የታዘብኩት፤ እንኳን መፅሐፍ መጻፍ ይቅርና መፅሐፍ አንብበው በጥልቀት የማይረዱ እንደሆነ ከስነጽሁፍ ቃላት አጣጣላቸው ማወቅ የሚቻልበት መራር ሀቅ በየገጹ ቅርንጫፍ ተጽፎ አስተውያለሁ። እኔም ጊዜ እየጠበቅኩ እድሜ ከሚያመልጠኝ በSoft copy መግዛት ለሚፈልጉ ሰዎች የመጀመርያ መፅሐፌን እስከተቻለኝ አቅም ትንሽ ከሸጥኩ በኋላ ሙሉ ለሙሉ በቴሌግራም ቻናሌ ኦፊሻሊ አጋራዋለሁ። በተያያዘ ወሬ ስለሁለተኛው መጽሐፌ አንድ የምነግራችሁ ነገር ለፍቼበታለሁ። እናም ደግሞ ከመጀመርያው ለቅምሻ ከማወጣው መፅሐፌ በተለየ አቅጣጫ የቀረበ ነው። ስለዚህ በሰፊው ልመጣበት እንደገና ጀምሬያለሁ። ሁለተኛው መፅሐፌ በማኅበረሰብ ሞራሊዝም (Social Moralism) ላይ የሚያተኩር፣ የፍልስፍናን፣ የሶሺዮሎጂንና የሳይኮሎጂን እይታዎችን በአንድ የሚያቀናጅ ሥራ ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን የሃይማኖት ምንነት በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ያለውን ሚና፣ በኢትዮጵያ የተከሰቱ የእርስ በርስ ግጭቶች በሰዎች እምነት፣ በማኅበራዊ እሴቶችና በጋራ መኖር ላይ ያሳደሩትን ተጽዕኖ ይመረምራል። ፖለቲካ እንዴት ከርዕዮተ ዓለም ልዩነት ተሻግሮ ወደ ማኅበራዊ ጥላቻና የማንነት መከፋፈል እንደሚሸጋገርም የጥናቱ አንድ አካል ነው። በተለይም ራሱን ወግ አጥባቂ (Conservative) እና ሞራላዊ እሴቶችን ጠባቂ አድርጎ የሚገልጽ ማኅበረሰብ፤ በተግባር ግን የተቀመጠውን ማኀበራዊ ባህልን ሲጥስ የሚፈጠረውን የሞራል ተቃርኖ (Moral Contradiction) በጥልቀት ይዳስሳል። በተጨማሪም የማኅበራዊ ግብዝነት (Social Hypocrisy) የግንዛቤ ተቃርኖ (Cognitive Dissonance) የቡድን ማንነት (Social Identity) እና የሞራል መላላት (Moral Disengagement) በማጠቃለል አናላይሲስ የወጣለት መፅሐፌ ነው። ይህን መፅሐፌን ቀድሞሁኑ ጀምሬው የነበረ ጽሁፍ ቢሆንም፤ ብዙም ሳልሄድበት በጭንቀትና በግል ምክንያቶች ሳቢያ ለጊዜው አቋርጬው ነበር። አሁን ግን ወደመፃፍ ተመልሻለሁ። እስከዚያው ግን «እሳት የወለደችው ሞት»ን እንደ ቅምሻ ወይም በአፍ እንዳለች ከረሜላ እየመጠጣችሁ ጠብቁኝ። ይህ የመጀመሪያዬ የግጥምና የአጫጭር መጣጥፍ ስራዬ ነው፤ ከዚያ በኋላ ግን ሌላ ጠለቅ ያለ መራር ሀሞት በሁለተኛው መፅሐፌ ይጠብቃችኋል። በመጨረሻም ከመፅሐፉ ጋር በተያያዘ ለመፅሐፉ እና እኔም ለመጻፌ እገዛ ማድረግ የምትፈልጉ ሰዎች በአዋሽ ባንክ የበኩላችሁን አስተዋጾ ማድረግ ትችላላችሁ አመሰግናለሁ፦       013201281880800 Moges beyene @Armemo_offical

Открыть в Telegram
Просмотры2 560−4%к среднему
Пересылки—
Реакции56
Комментарии—
#6175Фото
Просмотры4 420+66%к среднему
Пересылки—
Реакции33
Комментарии—
#6171Фото

🗣 ለሚኖር መሰንበት አጥሮ ፥ ሰባና ሰማንያ 'ራቀው በለሱን አንቆሮ ተፍቶ ፥ በዋጠ ማግስት አነቀው፤ ሙታንም ለራስ አንብቶ ፥ በቁሙ ህይወት ተራበ ሰማየ ሰማያት ሲመኝ ፥ ከጽድቁ ውድቁ ቀረበ፤               ያ ምስኪን ድሃ ገበሬ               ቢጸልይ ለመኖር ዛሬ               ምሽቱን ሽፍታ ላከበት               ተኝቶ በደረቅ ቁርበት             ቀረለት ዛሬን መሰንበት         ማጣት ላይ ሞት አክሎበት። እናማ እንዲህ ቢገጥመው ፥ አምላኩን ቆሞ ከሰሰው አምላክም የዋዛ አይደለም ፥ ድጋሚ በመኖር ካሰው፤ መታተር የማይሰለቸው ፥ ይህ ምስኪን ድሃ ገበሬ ሰማይን ዝናብ ሲለምን ፥ ማዕልቱን አጥምዶ በሬ ምሽቱን ገዳይ ላከበት ፥ ከስቃይ ሊገላግለው አምርሮ አምላኩን ሲከስ ፥ ዘላለም ህይወት አደለው። ነገር ግን ደስ አላለውም ፥ አምርሮ ቃሉን ደገመ      በስጋው ስቃይ የበላ ፥ ከነፍሱ ያላገገመ ድጋሚ መኖር መቀጣት ፥ መሰንበት የተረገመ..   ነገር ግን ደስ አላለውም ፥ ይልቅ ይህን አነሳ      በደሌን ይቅር ብትለኝ ያንተንም እንደምረሳ     አባት ሆይ ፈተና በቅቶ ፥ ከክፉ የምታድነን ሞት የለሽ ሞት እየሰጠ ፥ መከራን 'ምትገላግለን ዘላለም ህይወት ሰርዘ ፥ ከመኖር ቀድመ ስትገድለን!             @Imagination_officially

Открыть в Telegram
Просмотры3 570+34%к среднему
Пересылки—
Реакции35
Комментарии—
#6170Текст

ስለዚህም ነው ይህን የምላችሁ፤ የምታነሱት ሃሳብ ከአንድ መፅሃፍ ጥቅስ በዘለለ የተሻለ የአዕምሮ ፈተና አይጠይቅም!። ስለፈጣሪያችሁ መኖር ከዚህ ቅዱስ መፅሃፍት በተሻለ ተፈጥሮ ትመሰክራለች። ልክ እንደ ሱፊው ታሪክ ነው። ይህን ታሪክ ያገኘውት ኃይለጊዮርጊስ ማሞ ከተረጎመው ጥበብ ከጲላጦስ መፅሐፍ ላይ ነው። ሰውዬው የሱፊውን መምህር እየዘለፈ ነው፦«በአይናችሁ አይታችሁ በእጃችሁ ዳሳችሁ የማታውቁትን አምላክ አለ ብላችሁ ታመልኩታላችሁ!። እሰቲ ምን ማረጋገጫ ኖሯችሁ ነው የምታመልኩት?» መምህሩ ጥያቄውን በጥያቄ መለሱ፦«በበረዓ መንገድ ላይ በትልቁ የግመል ዱካ ተዘርግቶ ብታይ በዛ ቦታ ግመል ማለፉን ትጠራጠራለህ?» ሰውዬው፦«በርግጥ ዱካውን ካየው ስለምን እጠራጠራለሁ። አዎ አምናለሁ ማስረጃው በዛው አለ» መምህሩ፦«እኛም ፈጣሪ ስለመኖሩ ለማመን የግድ እሱን ማየትና መዳሰስ አይጠበቅብንም። ዛፉ፣ ባህሩ፣ ሰዎችና ተፈጥሮ በጠቅላላ ፈጣሪ ስለመኖሩ የማስረጃ ዱካ ናቸው።» መጨረሻም ላይ የዚህ ታሪክ መዝግያ ያደረግኩበት ምክንያት «Natural Theology» ማለትም የተፈጥሮ ሥነ መለኮት ፍጥረታት የፈጣሪ መኖር ለማረጋገጥ የሚቀርቡ በቂ ማስረጃ መሆናቸውን ለመናገር ነው። እቺ ታሪክ ብቻ ሦስት የፍልስፍና ክርክሮችን ታስነሳለች። አንደኛው «Argument from design» የዲዛይን ንድፈ-ሃሳብ ክርክር፤ ሁለተኛው «Cosmological argument» ቅድመ መነሻዊ የህልውና ክርክር፤ እና ሦስተኛው «Inference to the best explanation» ካገኘናቸው ማስረጃዎች በመነሳት ጠለቅ ያለ ማብራርያ መስጠት። ለምሳሌ ግመሉን ባናየውም ዱካውን ብናየው ከዛ በመነሳት ግመሉ በበረዓ ማለፉን እንደአንድ ማስረጃ መያዝ ሲሆን፤ የፈጣሪ መኖር ማረጋገጫ የፍጥረቶች መኖር ማስረጃ ይሆኑናል። ፍጡር ወይም ፍጥረታት በአንድ አካልና በአንድ ፈጣሪ ካልተፈጠሩ ካለመኖር ወደመኖር ሊመጡ አይቻለውም። ያለግመል የግመል ዱካ በምድር አይኖርም እንደማለት ያለ ነው። ያን በማመን የግመሉን ድካ ተከትለን አርባም ሠላሳም እርምጃ ብንራመድ ግመሉ ጋር መድረሳችን አይቀሬ ነው። ነገር ግን እስከዛሬ ድረስ ወደግመሉ እንዳንደርስ ያደረገን የግመሉ አለመኖር ሳይሆን ብዙ የግመል ዱካ በሰሜን፣  በደቡብ፣ በምዕራብ እና በምስራቅ በአራቱም አቅጣጫ በበረዓ ላይ አርፎ ግራ ስላጋባን ነው። በተሳሳቱ የግመል ዱካዎች ተመርቶ የሄደ ሰው ደግሞ መጨረሻው ላይ የሚጠብቀው ሌላ አውሬ ነው!። @Armemo_offical

Открыть в Telegram
Просмотры2 960+11%к среднему
Пересылки—
Реакции30
Комментарии—
#6169Текст

ከዛሬ 3 ዓመት በፊት ያጋራዋችሁ የካህሊል ጅብራን «The madman» መፅሃፍት ላይ «The two learned men» የምትል ታሪክ አለች። ታሪኩን በትንሹ እነሆ፦ በአንድ ወቅት በጥንታዊቷ አፍቃር ከተማ አንዳቸው የሌላኛቸውን ትምህርት የሚነቅፋና የሚያጥላሉ ሁለት የተማሩ ሰዎች ይኖሩ ነበር። አንደኛው የጣዖታትን መኖር ሲክድ ሌላኛው በበኩሉ ያምናል።        አንድ ዕለት በገብያ መሃል ይገናኙና ስለ ጣዖታቱ መኖርና አለመኖር መከራከር  ይጀምራሉ። ለሰዓታት ከተጨቃጨቁ በኋላ ይለያያሉ። የዛኑ ዕለት ምሽት አላማኙ ወደ መቅደስ ሄዶ ከመሰዊያው ፊት በመቆም እስከዛሬ ላጠፋው ጥፋት ይቅርታን ለመነ። በተመሳሳይ ሰዓት በአማልክት መኖር ያምን የነበረው ሌላኛው ሰው ቅዱስ መፃህፍቱን በጠቅላላ አውጥቶ አቃጠላቸው። ለካ ይህ ሰው ኢ-አማኝ ወደ መሆን ተቀይሮ ነበር። ይህ ታሪክ አንድ ፍልስፍናዊ ጥያቄ ያስነሳል፦«Do we believe what we truly understand, or do we defend what we have become accustomed to believing?» ማለትም እምነታችንን በጥልቀት ተረድተነው ነው የምናምነው ወይስ ከእምነታችን ጋር ተላምደን ስለኖርን በደፈናው የምናምነው?። ምን መሰላችሁ የእምነት ተጋድሎ እና የሃይማኖት ጦርነት ለእኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር አይደለም። ጥንት ከሰለሞን ስርወ-መንግስት በፊት ጀምሮ ፊውዳል የነበረው የክርስትና አገዛዝ በጥንት ሙስሊሞች ላይ የባርነት እና የጭቆና ስርዓትን ያራምድ ነበር። ይህን ስል በኢትዮጵያ ሁሉም ክልሎች ሙስሉሞችን ይጨቁን የነበረ ክርስትናዊ አገዛዝ አለ እያልኩ አይደለም፤ ግን አብዛኛው በሚባል ደረጃ የዚህ ስርዓት አራማጅ ነበሩ። በዛው ልክ ከርስቲያን እና ሙስሊሞች በእኩል ዜግነት የሚኖሩበት ክልሎችም አይታጡም!። በተቃራኒው ከዮዲት ጉዲት ጀምሮ እስከ ግራኝ አህመድ የሚያበቃው ክርስትና-ጠል ማኀበር ክርስቲያኖች ላይ አላስፈላጊ የግድያና የሃይማኖት ልዋጤን አስተናግዷል። ከ13ኛው ክፍለ ዘመን እስከ 16ኛው ክፍለዘመን የነበረው የኦቶማን ቱርክ በቀጥታ ባይሆን በተዘዋዋሪ ወደኢትዮጵያ የሰነዘረው ሃይማኖታዊ ጦርነት በእስልምና ደረጃ ትልቅ ተጽህኖን በሃበሻ ላይ ጥሎ አልፏል። ይህ የክርስተናና እስልምና ሃይማኖታዊ ጦርነት ለእኛ ሐበሻዎች ባህላዊ ጨዋታችን ነው። በዛው ልክ አንዱ አንደኛውን ሌላኛውን ሲቆጣጠር በማፍረስና በማቃጠል የሚደመስሳቸው ጥንታዊ ቤተክርስቲያን እና መስጂድ ብሎም ቅዱስ የታሪክ መዛግብት መፅሃፍት እንደእውነት ትልቅ ጠባሳን ጥሎብን አልፏል። በተለይም አንድ ዜጋ ማንነቱን እና ምንነቱን እንዳይገነዘብ የሚያደረግ የኋላ ታሪክ የማጥፋት፣ የሃይማኖት ልዋጤ፣ የባርነት ግዞት በጠቅላላ ላልተገባ አስተሳሰብ ዳርጎናል። ልክ ከላይ እንደጻፍኩት የካህሊል ጅብራን ታሪክ አይነት የምርም አንባቢ ሃይማኞተኛ ቢኖር ቅዱስ መፅሃፉን ለማቃጠል በተነሳ ነበር። አብዝተን የምናወራለት የማናምነውን ነገር ነው። በእኛ ሀገር «ጀማሪ ምዕመን ከጳጳስ ይበልጣል» እንደሚባለው ነን። እምነት እና እውነት በሌለበት ቦታ ብዙ ቃላት ይንጸባረቃል። ያን አለመተማመን ለማጥፋት ሰው እጅግ አማኝና ስለሃይማኖቱ ተናገሪ ይሆናል። ለሃይማኖቱ ግንባር ቀደም ሟች የሚባለው ወደቤተእምነቱ በመሄድ ስርዓተ አምልኮ የማይፈጽመው፣ የማይሰግደው እና የማይጸልየው ነው። እንዲህ አይነቱ ሰው ለሃይማኖቱ ለመሞት ዝግጁ ቢሆንም ለሃይማኖቱ ሲል መኖርን ግን አያውቅበትም። ለሃይማኖት መኖር ፈጣሪው ያስቀመጠለትን ትዕዛዝ አክብሮ እድሜ ማስቆጠር ነው። ነገር ግን የሰማዕትን ተጋድሎ ታሪኮች የአብዛኛውን አማኝ አስተሳሰብ ለውጠውታል። ሰዎች እድሜ ዘመናቸውን የፈለጉትን አድርገው በመኖር ከዛ መካከል አንድ ቀን ላይ በምትከሰት እራስን ለሃይማኖት አሳልፎ የመስጠት መስዋትነት ውስጥ የእስከዛሬ ኀጢአታቸውን ያስተሰርያሉ። የሃይማኖት ስርዓትን አለመከተል ፈጣሪን አለመከት እንደሆነው ሁሉ፤ ስለምናምነው ነገር አለማወቅ ፈጣሪን አለማወቅ ጭምር ነው። እስቲ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንቺ ጭዌ ላንሳላችሁ፦ ሁለት የዜን ቤተመቅደሶች ነበሩ፤ እና በነዚያ የተለያዩ ቤተመቅደስ ውስጥ ያሉ መነኩሴዎቹ እያንዳንዳቸው ተላላኪ ሁለት ልጆች ነበራቸው። ታድያ አንድ ቀን የአንዱ ቤተመቅደስ ተላላኪ ልጅ በጠዋት እንጨት ሊለቅም ከመቅደሱ ወጥቶ በመንገድ  ሳለ ከሌላው የመነኩሴ ተላላኪ ጋር ይገናኛሉ፦«ወዴት እየሄድክ ነው?» እንጨት ሊለቅም የወጣው ደቀመዝሙር ጠየቀ። «እግሮቼ ወደመሩኝ እሄዳለሁ» ሲል ሌላኛው መለሰ። ይህ መልስ ግራ የገባው የመጀመርያው ደቀመዝሙር እንጨት መልቀሙን ትቶ ወደ መምህሩ በመሄድ የተፈጠረው ነገር ነገረው። መምህሩም፦«ነገ ጠዋት ያንን ትንሽ ልጅ ስታገኘው ተመሳሳይ ጥያቄ ጠይቀው። እሱም ተመሳሳይ መልስ ይሰጥሃል፤ ከዚያ አንተ ‘እግር ከሌለህ ወዴት ትሄዳለህ?’ በማለት አፉን አዘጋው።» በማግስቱ ጠዋት ሁለቱም ደቀመዝሙሮች እንዲሁ በመንገድ ላይ ይገናኛሉ። «ወዴት እየሄድክ ነው?» የመጀመሪያው ልጅ ጠየቀ፤ «ንፋሱ ወደሚነፍስበት ሁሉ እሄዳለሁ» ሲል ሌላኛው መለሰት። የመጀመርያው ልጅ ይህ መልስም በድጋሚ ግራ አጋብቶት ለሽንፈት ሲጋብዘው ወደ መምህሩ በመሄድ የተባለውን ተናገረ። «ነፋስ ባይኖር ኖሮ ወዴት እንደሚሄድ ጠይቀው» ሲል መምህሩም በድጋሚ ሐሳብ አቀረበለት። ደቀመዝሙሩም የሚናገረውን መልስ እያሰበበ ሙሉ ለሊቱን ሳይተኛ አሳለፈ። በማግስቱ ልጆቹ ለሦስተኛ ጊዜ ተገናኙ። «ወዴት እየሄድክ ነው?» የመጀመሪያውን ልጅ ጠየቀ። «አትክልት ልገዛ ወደ ገበያ እየሄድኩ ነው» በማለት ሁለተኛው ልጅ መለሰለት። እንግዲህ የመጀመርያው ደቀመዝሙር ለአራተኛ ጊዜ መልስን ፍለጋ ከመምህሩ እግር ስር ሊወድቅ መሆኑ ነው። አብዛኛው የሃይማኖት ደቀመዝሙሩ የታጨቀው በዚህ መሠል ታሪክ ነው። የመጀመርያው ደቀመዝሙር ማሰቢያ የሆነውን የግል ሃብቱን ሙሉ በሙሉ በመተው በመምህሩ አዕምሮ እየኖረ ነው። «እንዲህ ካለኝ እንዲህ እለዋለሁ፤ ያንን ጥቅስ ካነሳብኝ መምህሬ የነገረኝ ጥቅስ በመንገር አፉን አዘጋዋለሁ» በሚል ቀሽም አስተሳሰብ ተውጧል። ለአባባሉ ሌላ አባባል ሲነሳበት መልስ ለማግኘት መምህሩ ጋር በመመላለስ አዕምሮውን ሽጦታል። በዚህ መመላለስ ደግሞ እድሜውን ይጨርሳል ወይንም ሰልችቶት ይተወዋል። ምክንያቱም በእራሱ እምነት ያለው አትክልት ሊገዛ የወጣው ልጅ በሚመጡት ቀናቶች ውስጥ ምንአልባት እንጨት ሊለቅም፣ ውሃ ሊቀዳ ወይንም ቆብ እና መቁጠርያ ሊገዛ ከመንገድ ዳር መውጣቱ አይቀሬ ነውና!።

Открыть в Telegram
Просмотры2 090−22%к среднему
Пересылки—
Реакции25
Комментарии—
#6168Фото
Просмотры1 780−33%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—

Все посты

Связи