Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 202 |
| 5 ч | 349 |
- Через 1 час202
- Через 6 часов349
- Всего сейчас349
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 202 |
| 5 ч | 349 |
"...ፆም ትፌውስ ቍስለ ነፍስ ወታፀምም ኵሎ ፍትወታተ ዘሥጋ ትሜህሮሙ ለወራዙት ፅሙና..." ፆመ ድጓ ዘምኵራብ ❤ "... ፆመ የነፍስን ቍስል ትፈውሳለች ፤ የስጋን ፍትወት ሁሉ ፀጥ ታደርጋለች ፤ ለወጣቶች ፅሙናን ታስተምራለች ..." @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram"... ንጉሥ ዉእቱ ክርስቶስ ፤ ዘገብረ ብርሃናተ ዓበይተ ፤ ንጉሥ ዉእቱ ክርስቶስ ፤ ዘይኌልቆሙ ለከዋክብት በምልዖሙ፤ ንጉሥ ዉእቱ ክርስቶስ ፤ ዘአልበሶ ብርሃነ ለፀሐይ ፤ ንጉሥ ዉእቱ ክርስቶስ ፤ ንጉሠ ነገሥት ዘኢየኃይድዎ ስልጣኖ፤ ..." አቡን ዘቅዱስ ያሬድ ❤ "...ታላላቅ ብርሃናትን የፈጠረ ፤ ክርስቶስ ንጉስ ነው፤ ከዋክብትን በሙሉ የሚቆጥራቸው፤ ክርስቶስ ንጉስ ነው ፤ ለፀሐይ ብርሐንን ያለበሰው፤ ክርስቶስ ንጉስ ነው ፤ ስልጣኑን የማይቀሙት የነገስታት ንጉስ፤..." @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram"...ዘሰበኩ ነቢያት ናሁ ይመፅእ ወልድ በስብሐት ፤ ዘሰበከ ሙሴ በኦሪት ፤ ወኢሳይያስ ነገረ በትንቢት ፤ ዳዊትኒ ይቤ በርሕ ሠረቀ ለፃድቃን ወለርቱዓነ ልብ ትፍስሕት ..." ዝማሬ ዘቅዱስ ያሬድ ዘብርሀን ❤️ " ነብያት የሰበኩት ወልድ(ክርስቶስ) እነሆ በምስጋና ይመጣል ፤ ሙሴ በኦሪት የሰበከው ፤ ኢሳይያስ በትንቢት የተናገረለት ፤ ዳዊት ለፃድቃን ብርሀን ለልበ ንፁሀንም ደስታ ወጣላቸው ብሎ የተነበየለት ..." @amlake_birhan @waaqa_ifaa መልካም ፆመ ነብያት እንኳን አደረሳችሁ። ከቅድስት ድንግል የተወለደ ጌታ በኦሪት እና በነብያት የተሰበከ መሆኑን በማሰብ ከነብያቱ ጋራ ልደቱን ተስፋ እያደረግን የምንፆመው ፆም ነው ። በዚህ ወር ውስጥ ያሉ የቤተክርስቲያን ውስጥ ፀሎቶች በአብዛኛው በኦሪት እና በነብያት ስለጌታ የተነገሩትን ምሳሌዎች እና ሕብረ አምሳሎች በማስታወስ የተደረሱ ናቸው።
Открыть в Telegramካቶሊካውያን ወንድሞች ቅዳሴውን ከኛ ወስደው ከኛ ግን በተሻለ መንገድ ስርአቱን ጠብቀው ሲቀድሱት ማየት ይደንቃል ። እርስ በእርሳችሁ ሰላም ተባባሉ ሲባል እንዴት ሰላም እንደሚባባሉ ተመልከቱ ። እኛ ጋ በስርአት አይደረግም ። ካህናቱም ሰላም አይባባሉም። በጣም ጥንታዊ የሆነ የቤተክርስቲያን ስርአት ነበር ግን ። እንዴት አድርገን ይሆን ወደ ስርአታችን የምንመለሰው ። መፅሀፉ ላይ በግልፅ ተፅፎ እንዴት መጠበቅ እንዳልቻልን የሚገርም ነውኮ በውነት።
Открыть в Telegram"... ኖኅን የጠበቀው እርሱ ነው ፤ አብርሃምን የመራው ፤ ከይስሐቅ ጋር የታሰረ ፤ ከያዕቆብ ጋር እንግዳ የሆነ፤ ከዮሴፍ ጋር የተሸጠ እርሱ ነው ፤ በሙሴ አድሮ ህዝቡን የመራ ህግን የሰራላቸው ፤ ለኢያሱ ርስትን የሰጠው ፤ በእርሱም አድሮ ለእስራኤል ልጆች ያወረሳቸው እርሱ ነው ፤ በዳዊት አድሮ ትንቢትን የተናገረ ፤ በነብያት አድሮ ህዝብን ያስተማረ እርሱ ብቻ ነው፤ ከቅድስት ድንግል ሰው የሆነው እርሱ ነው ..." ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ሄሬኔዎስ ❤ @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram"... አዳም ሆይ ደስታ ባለበት በገነት በጌታ ማደሪያ ደስ ይለን ዘንድ ያልተውኸን ምን አደረግንህ? ሔዋን ሆይ ምን አደረግንሽ ? እነሆ በኃጢአት ብዛት ሥጋችን ጠቆረ ፤ በሰማያውያን አምሳል በኖርን ነበር ፤ ሔዋን ሆይ እነሆ ልጆችሽ በጭንቅና በሕማም በወለዱ ጊዜ ያለቅሳሉ ፤ አንቺ ያቺን በገነት ያለችውን እንጨት እንዳደማሻት ..." ቅዳሴ አትናቴዎስ ❤ @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram"... መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዐቢይ..." ሰላም ዘህዳር ሚካኤል ❤ "... የሰላማችን መልአክ ሊቀ መልዓክ ሚካኤል ሆይ ስለኛ ጸልይ ለምን ፤ ፀሎታችንን ታላቁ ንጉሥ መንበር ፊት አቅርብ ..." @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegramበጣም የሚያናዱኝ ሰዎች ለምሳሌ አንዲት እህት ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ትንሽ ለመቅረብ እየሞከረ ያለ ወንድም ስለ ቅዳሴ ወይ ስለ ማህሌት የሆነ ነገር ሲናገር በየኮሜንቱ እየመጡ "ምናለ ቢቀርብሽ " " አበላሸሽው " " እንደዚህ አይባልም" ... ምናምን እያሉ የሚፅፉ የቤተክህነት ሰዎች ደሜን ነው የሚያፈሉት 😁... አብዛኞቹ ይታወቃሉ ለራሳቸውም ምንም የማያውቁ ዲያቆናት እና ቄስ ተማሪዎች ናቸው ... አንዷ ቅድም ስለ ቅዳሴ ደስ የሚለኝ ክፍል ምናምን ብላ እያወራች በቃ ኮሜንት ላይ ያለው የፈሪሳዊ መዓት አይጣል ነው ... "ምን አገባህ የኔ ወንድም " ብዬ ለመፃፉ ይከጅለኝና እተወዋለሁ ... ቤተክርስቲያኗ የእነርሱ የግል ንብረታቸው ነው የሚመስላቸው ወገን ... ሲጀመር ኮሜንት መክፈት በጣም ነው የምፈራው የሆነ መንፈሳዊ video ራሱ ካየሁ
Открыть в Telegram"... ኢትሑር በምክረ ረሲአን ወኅሥሣ ለሰላም ኅድግ ወልድየ ሚጥ ልበከ ፤ ዕቀብ ወስማዕ ቃለ መክብብ ዘይቤ ኲሉ ከንቱ ኲሉ ከንቱ ከንቱ ንብረቱ ለዝንቱ ዓለም ኀላፊ ..." ፆመ ድጓ ዘምኲራብ ❤ "...በኃጢአተኞች መንገድ አትሂድ ፤ ሰላምን ፈልጋት ፤ ልጄ ሆይ ተዉ ልብህን መልስ ፤ የመክብብን ቃል ስማ ጠብቀውም እንዲህ የሚለውን ፤ የዚህ ከለም ነገር ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው ..." @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegramግራህን ሲመታህ ቀኝህን ስጥ ማለት ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ሲያቃጥል ገብርኤልን ደግሞ ጠቁመው ማለት ነው እንዴ ወገን? ኧረ ወፍ ! እኔ አይመስለኝም። ጥቅሱ For personal cause ነው የተነገረው ማለትም በግል ስለ ክርስቶስ ለሚመጣብህ ፈተና ነው ... መከራ ቢያበዛብህም ስለ ስሙ ታገስ ፤ ክርስቶስን አትካደው ፤ ክፉ አድራጊውንም ለመበቀል አትፈልግ እንደማለት ነው ። እንጂ የእግዚአብሔርን መንግስት ቤተክርስቲያንን( ጉባኤውንም ህንፃውንም) ሊያጠፋ የመጣውን መንገድ ምራው አይደለም እንደዚህ አይነቱንማ ግንባሩን ብሎ ወደ 7ተኛ ሰማይ መላክ ነው ። እስከሚገባኝ
Открыть в Telegram"... ነፍሳችሁን መርምሩ ፤ ሰውነታችሁንም አንፁ ፤ ከእኛ ወገን ማንም በበደልና በኃጢአት ብዛት አይታመም ፤ የእግዚአብሔር በግ አማኑኤል እነሆ ዛሬ ከእኛ ጋራ በዚህ ማዕድ አለ ፤ እነሆ ብርሀን አብ ከልጁ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አለ..." ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት ❤ @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram"... ነጽር ላዕሌነ አቡነ ክርስቶስ ለዘበእንቲአነ መጦከ ነፍሰከ ፤ ወንሕነኒ ንትአመነከ ከመ ንርከብ ሞገሰ ቃልከ ..." ፆመ ድጓ ዘምኲራብ ሰኑይ ❤ "... ነፍስህን ስለኛ የሰጠህ አባታችን ክርስቶስ ሆይ ወደኛ ተመልከት ፤ እኛም ባንተ እንታመናለን የቃልህን ሞገስ እናገኝ ዘንድ ..." @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram"... የምህረትህን ጎዳና ጥረግልን ፤ የኃጢአታችንን ማሰሪያ ሁሉ ፈፅመህ አጥፋልን ፤ አቤቱ አንተን ብንበድል በማወቅም ባለማወቅ በተንኰልም ቢሆን በልቡና ክፋት ፤ በመስራትም ቢሆን በመናገር በዕውቀት ማነስም ቢሆን ፤ የሰውን ድካሙን ታውቃለህና ..." ፍትሐት ዘወልድ ❤ @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram"... ክርስቶስ ብነ ፀወንነ ወኃይልነ ጽንዕነ ቤዛነ መድኃኒተ ነፍስነ ፤ ኪያሁ ነአኵት ኵልነ ለዘአንቅሐነ እምንዋም ..." ፆመ ድጓ ዘምኵራብ ❤ "... የነፍሳችን መድኃኒት ፤ ቤዛችን ፤ ብርታታችን ፤ ኃይላችን ፤ መጠጊያችን ክርስቶስ አለልን ፤ ከእንቅልፋችን ያነቃንን እርሱን እናመስግን ..." @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram"... አብርሂ አብርሂ ናዝሬት ሀገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መፆሩ፤ ጣዖታተ ግብፅ ኲሎ ቀጥቂጦ በበትሩ፤ ይጒየዩ ወይትኃፈሩ ሠራዊተ ሄሮድስ ፀሩ፤ ዘበላዕሌሁ እኩየ መከሩ ..." ሰቆቃወ ድንግል ❤ "... ናዝሬት ሀገሩ ሆይ ደስ ይበልሽ አብሪ ፤ ንጉስሽ የግብፅ ጣኦታትን ሰባብሮ ከእናቱ ከማርያም ጋር መጥቷልና ፤ በእርሱ ላይ ክፉትን የመከሩ የሄድሮስ ሠራዊት ወደ ኋላ ይሽሹ ይፈሩ ..." ደብረ ቍስቋም : ጌታችን እና እመቤታችን ከስደት ወደ ናዝሬት በሚመለሱበት ጊዜ ያረፉበት ተራራ ፤ በኋለኛው ዘመን ጌታችን ተገልጦ መሰዊያ ባርኮ ቤተክርስቲያን አድርጓታል። የስደታቸው መጨረሻ ዛሬ ይታሰባል። እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
Открыть в Telegramምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤ ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ፤ ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትፁሪዮ ይበኪ፤ አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤ ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ። ሰቆቃወ ድንግል ❤ "... ሕፃኑን ልጅሽን አንድ ጊዜ በጀርባሽ አንድ ጊዜ በጎንሽ በማዘል ማርያም ሆይ ብዙ ደከምሽ ፤ በእግሩ ሲሄድ ታዝይው ዘንድ ያለቅሳል ፤ ከሰሎሜ ውጪ የሚረዳሽ የለም ፤ አረጋዊው ዮሴፍም ስንቃችሁን ተሸክሟል ..." @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram"... ዓይነ ልቡናችንን ወደ አንተ እናንጋጥጣለን ፤ ክሣደ ልቡናችንን እናዘነብልልሃለን ፤ ላንተ መገዛት ይገባል ፤ ለመንግስትህም ምስጋና ይገባል ፤ ከሊቃነ መላዕክትም ጋር ንጹሕ እጣን እናቀርብልሃለን ..." ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ❤ @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram"... አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ የሚገባን ሳንሆን የምንሰግድልህ እኛ ኃጥአን አገልጋዮችህ አንተን እንማልዳለን ፤ በፊትህ ወደተሰራው ወደዚህ ቍርባን በአባትህ ፈቃድ መንፈስ ቅዱስን ትልክ ዘንድ ፤ ታነፃው ዘንድ ፤ እኛንም በቅድሳትህ ታከብረን ዘንድ ..." ቅዳሴ ባስልዮስ ❤ @amlake_birhan @waaqa_ifaa
Открыть в Telegram