Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 115 |
| 7 ч | 228 |
- Через 6 часов228
- Всего сейчас228
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 115 |
| 7 ч | 228 |
‹‹ጥቁር ጽጌረዳ›› (የታሪክ ሃሳብ -Coffee to Go አጭር ፊልም) ❤️❤️❤️❤️-------❤️❤️❤️❤️ በሰው ወደታጨቀው ካፌ ከመግባቷ በፊት ስልኳን ይዛ የምታናግረው ሰው ላይ ትጮኻለች። “ሜሪ! …ምን….ምኑ ነው ይሄን ያህል የሚከብደው? …ስንቴ ነው የምነግርሽ? ….ጽጌረዳ አልፈልግም…ታኪ ነው…እኔ ቱሊፕ አበባ ነው የፈለግኩት። ቱሊፕ አበባ በአማርኛ ምንድነው ስሙ? …እኔ ዲክሽነሪ ነኝ እንዴ? ….እ? …አላውቅም አልኩሽ እኮ! ….እንዴ…ብትፈልጊ ለምን ጎግል አታደርጊውም? ወይ ደግሞ ቻት ጂፒቲን አትጠይቂውም? …ሲሪየስሊ… ሁሉንም ነገር እኔ ነኝ እንዴ የምሰራው…? ታዲያ ምኑ ላይ ነው አንደኛ ሚዜነትሽ….? ሆ….ምን? …ኦኬ…እ…ጉገል ምናለኝ? …… እሺ… ጥሩምባ አበባ…ጥሩ! አሁን ሄደሽ ነጭ ጥሩምባ አበባ ፈልጊልኝ…አለቀ……እንዴት አይኖርም? ኢትዮጵያ እኮ አበባ ኤክስፖርተር ናት….እንዴት ነው የማይኖረው? ብዙ ባይሆን እንኳን ለእኔ ሰርግ ያህል አታጪም…አትስነፊ…ነቃ በይ…አንደኛ ሚዜ ብሎ ዝም ነሽ መቼም…. እሺ… በቃ አሁን አንጎሌ ሳይፈነዳ ማኪያቶዬን ልጠጣ…እንዳትደውይልኝ…ቻው!” ስልኩን ዘግታ ወደ ካፌው ገባችና ከሚያብረቀርቁት የእንጨት ወንበሮች አንዱን ስባ ተቀመጠች፡፡ ድምቡሽቡሽዋን አስተናጋጅ “ማኪያቶ… ጠቆር ያለ” ብላ አዘዘች። አስተናጋጇ ከአጠገቧ እንደሄደች ትልቅ ቦርሳዋን ከፍታ ሚዜዋ ለጠረጴዛ ልብስ ይሆናሉ ብላ የሰበሰበቻቸውን ወረቀት ላይ በስቴፕለር የተያያዙ ቁርጥራጭ የጨርቅ ናሙናዎች አወጣች። ልክ በዚያች ቅጽበት ነበር አንድ ሰው አጠገቧ መቆሙን አይኖቿ ሳይሆኑ ቀልቧ የነገራት። “አሁንም ጠቆር ያለ ማኪያቶ ወዳጅ ነሽ ማለት ነው?” አላት ፈገግ ብሎ። ሳምሶን። ለአፍታ ለግላጋ ሰውነቱን በዝምታ ቀና ብላ አየችው፡፡ ከዚያ የምትፈልጋቸውን ቃላት ድንገት ያገኘች ይመስል ፈጠን ብላ፣ “ሳሚ? …እኔ እኮ አላምንም! … ከየት ዱብ አልክ?” አለችውና ተነስታ አቀፈችው። “ወይ ጉድ አንቺ…በጣም አምሮብሻል” አላት ወንበር ስቦ አጠገቧ እየተቀመጠ። “ነው ብለህ ነው? …አንተም ጥሩ ነው ያለኸው” አለች በፈገግታ እየተሽኮረመመች። “ለነገሩ አንቺ መቼ ነው የማያምርብሽ?” አላት ፊቷን በጥንቃቄ እያጠና። መቀመጫዋና እጆቿ በላብ ሲረጥቡ ተሰማት፡፡ ለጥቂት ሰከንዶች ከከበባቸው የካፌ ሁካታ ውጪ በመሃከላቸው ዝምታ ሰፈነ። “ይሄ ደግሞ ምንድነው?” አላት ጠረጴዛው ላይ ያለውን የጨርቅ ስብስብ እያመለከተ። “እ…ይሄ… ተወው ባክህ! በጣም የሚያስጠሉ የፐርፕል ጨርቅ አይነት ናቸው” አለችው እየሳቀች። “እሱንማ አየሁ። ምን ሊያደርጉልሽ ይዘሻቸው ነው? ነው ወይስ ጨለልሽ…?” “ሃሃሃ…. ለሰርግ ነው… ለጠረጴዛ ልብስ የሚሆን ምረጪ ብለውኝ ነው። …ሁሉ ነገር መቀናጀት አለበት አይደል? …ላገባ እኮ ነው” አለች አይኖቿን በሃፍረት ሰበር አድርጋ። “እሱንስ ሰምቻለሁ።” ረጋ ብሎ መለሰላት፡፡ መንፈሷን ቅልል አላት፡፡ እፎይታ ተሰማት፡፡ በሆዷ ‹‹እንኳን የሰማህ›› ብላ ቀና ብላ አየችው፡፡ አስተናጋጇ በፍጥነት ያመጣችላት ማኪያቶ ሳይነካ ተቀምጧል። “እህስ… እንዴት ነህ ታዲያ?” አለች ጸጉሩን እያየች። አሁን ትንሽ ሽበት ጣል አድርጎበታል፣ ግን አሁንም እንደ በፊቱ ጥቅጥቅ እንዳለ ነው። “ደህና ነኝ… ብዬ አስባለሁ።” ፈገግ ብሎ መለሰላት፡፡ “ብለህ ታስባለህ?” “ሰው እኮ ራሱን አያውቅም ኪዱ። እኔ ደግሞ ታውቂኛለሽ…ደህና መሆኔን የሚያረጋግጥልኝ ሶስት ምስክር እፈልጋለሁ። ለራሴ ደህንነት ታማኝ ምስክር መሆን አልችልም…ብዋሽስ? …” አላት። “አሄሄ…ያቺ የደራሲ ፍልስፍናህ አሁንም አለቀቀችህም ማለት ነው?” አለች እየሳቀች። ለጥያቄዋ መልስ ሳይሰጥ- “ቡና ባዝዝ ይከፋሻል ኪዱ?” አላት፡፡ “ለምን ብሎ ይከፋኛል?” “ማለቴ… አብሬሽ ብቀመጥና ቡናዬን ብጠጣ። ምናልባት ሰው እየጠበቅሽ ከሆነ ብዬ ነው?” “አይ…አይደለም…ቀጠሮ ምናምን የለኝም። በዚህ የእብደት ቀን መሃል ትንሽ ተንፈስ ልበል ብዬ ነው የገባሁት። ይሄ ሰርግ ሊያሳብደኝ ነው ብታይ!” “አይ ጥሩ እንደዛ ከሆነ ቡናዬን ልዘዝ” አስተናጋጇን ጠቅሶ ጠራትና ወፍራም ቡና አዘዘ። ዳግም ጸጥታ ሰፈነ። “እና… እንዴት ነው ኑሮ…? ምን አዲስ አለ?” አለች የቀዘቀዘ ማኪያቶዋ ላይ ሶስት ማንኪያ ስኳር ሞጅራ እየጠጣች። “ኑሮ ደህና ነው…ስራ እየሰራሁ ነው… እኔም እንደሁልሽም የገፈቱ ቀማሽ ሆንኩ እኮ…የቅጥር ስራ ጀመርኩ” “አይደረግም!” አለች በመገረም። “ተደረገ ኪዱዬ….የማይሰራው ሰራ…የማይቀጠረው ተቀጠረ” ‹‹አላምንህም!›› ‹‹እውነቴን ነው…በመጨረሻ በሰልኩ መሰለኝ… እጄን ሰጠሁ።›› “እና ታዲያ…አሁን የት ነው የምትሰራው?” “ማተሚያ ቤት… ” ‹‹አባትህ ጋር?›› ‹‹አዎ…አባባ ጋር…በመጨረሻ ተሳካለት…›› “ውሸትህን ነው!” “በእውነት።” ‹‹እንዴት እሺ አልካቸው?›› ‹‹ግድ ሆነብኛ…አፈር አይበላ…አየር አይጠጣ…ዛፍ ስር አይኖር…›› “ዋው..እና ታዲያ ድርሰት አቆምክ?” “ለጊዜው።” “ምን ሆነህ ነው? ስንት አመት ሙሉ ብራብም ድርሰቴ ይበልጥብኛል ስትል አልነበርም? …እኔ እንኳን ስለምን ሳስለምንህ…›› “ሀላፊነት መጣአ! መቼም ዘላለም ልጅነት የለም…የሆነ ጊዜ መንቃት አለብሽ..” ፊቱን ወደ ውጪ፣ ወደ ዋናው ጎዳና አዞረ። ዝምታ። “ያንቺስ ስራ እንዴት ነው?” ሲል ጠየቃት ዞር ብሎ እያያት። “ኦ…ባለፈው አመት ፕሮሞት ተደረግኩ እኮ። የዲፓርትመንት ኃላፊ ሆኛለሁ።” “እንኳን ደስ አለሽ። ይገባሻል። አንቺ እኮ ሁሌም ስራሽ ላይ ጎበዝ ነበርሽ።” “አመሰግናለሁ ሳሚዬ። ደስ ብሎኛል…ደሞም አሪፍ ሃላፊ ወጥቶኛል ብዬ አስባለሁ።›› “እርግጠኛ ነኝ ነሽ።” ሌላ ዝምታ። “እሺ ታዲያስ…ሰርጉስ?” አላት። “ሰርጉ ምን?” “መቼ ነው?” “ከአንድ ወር በኋላ።” “አንቺ ነገ ነዋ…ደርሷል።” ትከሻዋን በግዴለሽነት ሰበቅ አደረገች። ትክ ብሎ አያት። “ዳግማዊስ… እንዴት ነው?” “ሳሚ… በናትህ። ስለሱ አትጠይቀኝ…። ከአራት አመት በኋላ ተገናኝተን በጣም ደስ የሚል ጊዜ እያሳለፍን አይደል? …የማይሆን ነገር አታድርግ” ተፃፈ በሕይወት እምሻው
Открыть в Telegramመዳፍ ፤ የሰው አድማስ (በእውቀቱ ስዩም) ማነው የሚያደምጥህ? አየሩን ቢሞላው፤ ዜማህ ተንቆርቁሮ በገዛ ጫጫታው፤ ሁሉም ተደናቁሮ፤ ባዘቦት በሰንበት፤ ሰው በሚጎርፍበት ባደባባይ መሀል ወበቅና ጠኔ አዙሮ ቢጥልሽ ማነው ልብ የሚልሽ ? ንስር ክንፉን ትቶ ከልማዱ ወጥቶ ቢሳብ በደረቱ፤ አባብ ቢሄድ ባየር የቀስተ ደመና፤ ቀለሙ ቢቀየር፤ ጀነበር ኩበት ብትሆን፤ ጨረቃዋ ብትፍም የሰው እይታ አድማስ፤ ከመዳፉ አያልፍም፤
Открыть в Telegramውልብታ (በእውቀቱ ስዩም) በደራው ጎዳና፤ ብቅ ብትይ ድንገት ተበደርኩኝና የሎጥን ሚስት አንገት ዞሬ ባስተውልሽ ፤ ድፍርስ አይኔ ጠራ፤ ማየት ፍዳን ሳይሆን፤ ጽድቅን እየጠራ፤ ፈገግታሽ አንደ ህልም የሁዋሊት ያስኬዳል፤ በዚህ መጠን ማማር፤ በህግ ይፈቀዳል ?
Открыть в TelegramПереслано из Post Maker Bot
ኤደን የልቧ ምት በጆሮዎቿ ውስጥ እየተሰማት ነበር። ሴቷ ጥያቄዋን ጠየቀች። «ናትናኤል ድንግል መሆንሽን ለምን እንደፈለገ ነግሮሻል?» ኤደን ደነዘዘች። በዚያ ቅጽበት ናቲ ወደ ሴቷ ተመለከተ። በዓይኖቹ ውስጥ ኤደን ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ነገር ነበር። ፍርሃት። እውነተኛ ፍርሃት። ሴቷ የመጨረሻዋን አረፍተ ነገር በቀስታ ጨመረች። «ምክንያቱም አንቺ የመጀመሪያዋ አይደለሽም፣ ኤደን።» እና በዚያው ቅጽበት ናቲ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ወሰደ። «እሷን አትንኪ!» ሴቷ ግን ሽጉጡን ከናቲ ላይ ወደ ኤደን አዞረችው። «እኔ እሷን ልንካት? ናቲ፣ እኔ ልጠብቃት ነው የመጣሁት። ከአንተ!»
Открыть в TelegramПереслано из Post Maker Bot
ዉዴ አንቺ ባትኖሪ ምን ይዉጠኝ ነበር ናትናኤል ነበር ኤደንን ደረቱ ላይ አስተኝቶ እጆቹን ፀጉሮቿ ላይ እያተራመሰ የተናገረዉ ኤደን ደክማለች ከ ደቂቃዎች በፊት ከ ናቲ ጋር የነበረችበት ጥልቅ የ ፍቅር አለም ፍፁም አድክሟታል በ እርግጥ በቀላሉ አልጋ ላይ አልወደቀችለትም እሷን ወደ አልጋ ይዞ ለመዉጣት ለ ስድስት ወራት መልፉት አስፈልጎታል በ እርግጥ ድንግልናዋ አጓጉቶት እንጂ ይሄን ያክል መጠበቅ ፍፁም አልፈጠረበትም ከ ጥልቅ ዝምታ በሀላ እንዳያይባት የምትታገለዉን እንባ ቀስ ብላ ጠረገች ና ናቲ አለች ወዬ አላት አትተወኝማ አለችዉ ጥርጣሬ በተሞላዉ ድምፅ አንቺን እንዳለ በሩ በሀይል መንኳኳት ጀመረ ከደረቱ ላይ ተነሳችና ሰዉነቷን በ አንሶላ እየሸፈነች ማነዉ አለችዉ ናቲ ድንጋጤዉን ለመሸፈን እየሞከረ እኔንጃ አላት እና ወረደ ነገር ግን እሱ በሩ ጋር ከመድረሱ በፊት በሩ ተበረገደ ና ሽጉጥ የያዘች ሴት ወደ ቤቱ ዘልቃ ገባች እና ሙሉዉን ለማግኘት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Открыть в Telegram