Кабинет

Посты канала C R R S A - የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ

сначала новые

#14430Превью ссылки

ኤጀንሲው የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ላይ ለሁሉም ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ   CRRSA: ህዳር 19/2019 ዓ.ም     የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ሁሉም አመራሮች እና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡   የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የተሰጠው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በመጡ የዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ሲሆን የሪፎርሙ ዓላማ አገልግሎት  ሰጪ ተቋማትን ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ የነዋሪዎችን እርካታና አመኔታ ማሳደግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡    በሥልጠናው የሲቪል ሰርቪሱን ታሪካዊ ዳራ፣ የሪፎርሙን አስፈላጊነትና ዓላማ፣ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲን እንዲሁም ሰባቱን ዋና ዋና የፖሊሲ አምዶች የሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ተካተው ቀርበዋል።በተጨማሪም የመንግሥት ሠራተኞችን ብቃት በምዘና የማረጋገጥና የማሳደግ ሂደት፣ የዲጂታል አገልግሎት ግንባታ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማጠናከር በማጠናከር ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል እንደሚገኙበት ተነግሯል።    የሪፎርሙ ዋና ዓላማ ብቁ፣ ነፃና ገለልተኛ የሲቪል ሰርቪስ በመገንባት ግልጽ፣ ፈጣን፣ ፍትሐዊና ጥራት ያለው አገልግሎት ለሕዝብ ማቅረብን መሆኑ ስልጠናው በተሰጠባቸው የተለያዩ መድረኮች ቀርቧል፡፡    ኤጀንሲው የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርምን ተግባራዊ ለማድረግ የዌቭ ሁለት ከተመደቡ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በተለያዩ አራት ማዕከላት በመክፈል ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ ሁሉም አመራሮች እና ባለሙያዎች እንድወስዱ አድርጓል፡፡   ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ይደውለው የኤጀንሲውን የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች  ይከታተሉ     የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et   ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et   ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686   ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress   ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/@CRRSA1935   ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/@aacrrsa_head_office   ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/   ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

Открыть в Telegram
Просмотры681−50%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#14413Фото

ባሉበት ሆነው በእጅ ስልክዎ ወይም ኮምፒውተርዎን በመጠቀም አገልግሎት ያግኙ   CRRSA: ህዳር 18/2019 ዓ.ም የሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የተገልጋዩን   ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ለማሟላት የሚያስችለውን የኦንላይን  አገልግሎት መተግበሪያ  በስራ ላይ ማዋሉ ይታወቃል ፡፡ ውድ የከተማችን ነዋሪዎች! ባሉበት ሆነው በእጅ ስልክዎ ወይም ኮምፒውተርዎን በመጠቀም የነዋሪነት መታወቂያዎን ከፋይዳ (Fayda) ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር እንዲሁም የአገልግሎት ጥያቄዎችን በኦንላይን ማቅረብ ይችላሉ። በአሁኑ ወቅት ኤጀንሲው.         *የልደት ሰርተፊኬት      .*የነዋሪነት መታወቂያ እድሳት    .*ያላገባ/ች ማስረጃ  አገልግሎቶችን በኦንላይን  እየሰጠ ይገኛል   ስለሆነም አገልግሎቱን ይህን ማስፈንጠሪያ    https://portal.aacrrsa.gov.et ይጠቀሙ   «አንድ ጊዜ ይመዝገቡ፤ በሁሉም ቦታ ይገልገሉ!»   ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ይደውለው የኤጀንሲውን  የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች  ይከታተሉ    የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686 ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/@CRRSA1935 ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/@aacrrsa_head_office

Открыть в Telegram
Просмотры1 160−16%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#14411Превью ссылки

ባሉበት ሆነው በእጅ ስልክዎ ወይም ኮምፒውተርዎን በመጠቀም አገልግሎት ያግኙ CRRSA: ህዳር16/2019 ዓ.ም የሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የተገልጋዩን   ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ለማሟላት የሚያስችለውን የኦንላይን  አገልግሎት መተግበሪያ  በስራ ላይ ማዋሉ ይታወቃል ፡፡ ውድ የከተማችን ነዋሪዎች! ባሉበት ሆነው በእጅ ስልክዎ ወይም ኮምፒውተርዎን በመጠቀም የነዋሪነት መታወቂያዎን ከፋይዳ (Fayda) ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር እንዲሁም የአገልግሎት ጥያቄዎችን በኦንላይን ማቅረብ ይችላሉ። በአሁኑ ወቅት ኤጀንሲው.        *የልደት ሰርተፊኬት      .*የነዋሪነት መታወቂያ እድሳት    .*ያላገባ/ች ማስረጃ  አገልግሎቶችን በኦንላይን  እየሰጠ ይገኛል ስለሆነም አገልግሎቱን ይህን ማስፈንጠሪያ https://portal.aacrrsa.gov.et ይጠቀሙ  ስለ አገልግሎቱ የበለጠ ለመረዳት ከስር ያለውን የቪዲዮ መረጃ ይመልከቱ፤ጥያቄዎን በኦንላይን አቅርበው ሲጠናቀቅ በፈለጉት ጊዜ መጥተው መውሰድ ይችላሉ!  «አንድ ጊዜ ይመዝገቡ፤ በሁሉም ቦታ ይገልገሉ!» የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ   ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ይደውለው የኤጀንሲውን የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች  ይከታተሉ     የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et   ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et   ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686   ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress   ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/@CRRSA1935   ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/@aacrrsa_head_office   ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/   ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

Открыть в Telegram
Просмотры1 710+24%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#14410Видео

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በኦንላይን አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ያውቃሉ?   CRRSA፡ ህዳር 15/2019 ዓ.ም     አዲስ አበባ   ኤጀንሲው የህብረተሰቡን  ፍላጎት ለማርካት እና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የልደት ሰርቲፊኬት፣የያላገባ እና ዲጂታል  የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎቶችን ባሉበት ሆነው በእጅ ስልክዎ አልያም በኮምፒውተርዎ  በመጠቀም ባሉበት ሆነው አገልግሎት ያግኙ፡፡   ስለአጠቃቀሙ ከታች የተጫነውን ቪዲዮ ይከታተሉ    «አንድ ጊዜ ይመዝገቡ፤ በሁሉም ቦታ ይገልገሉ!»     ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ይደውሉ   የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et   ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et     ፌስቡክ(Facebook):https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686     ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress   ዩቱዩብ (youtube): https://www.youtube.com/@CRRSA193 ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/@aacrrsa_head_office   ኢንስታግራም(Instagram)https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/ ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

Открыть в Telegram
Просмотры2 800+104%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#14409Превью ссылки

የሙስና ሰንሰለትን ለመበጠስ የተቋማት ግልጽነት፤ተጠያቂነትና የተቀናጀ ትግል ያስፈልጋል ፡- አቶ ዮሴፍ ንጉሴ   CRRSA፡ ህዳር 14/2019 ዓ.ም     አዲስ አበባ   የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ «ሥዉር ትስስሮችን በማጋለጥ፤ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!» በሚል መሪ ቃል 23ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ ፓናል ውይይት አካሄደ።   የኤጀንሲው የሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አስናቀች ሙህዬ የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የሙስናን ምንነት፣ መንስኤዎች፣ በተቋማትና በሕብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ተቋማዊ ተፅዕኖ እንዲሁም ለመከላከል መከተል ስለሚገባው የተቀናጀ ስትራቴጂ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።   ሙስና የአንድ ግለሰብ የሥነ-ምግባር ችግር ብቻ ሳይሆን የተቋማትን ተዓማኒነት የአገልግሎት ፍትሐዊነትና የሕዝብን እምነት የሚጎዳ ሰፊ ችግር መሆኑን የገለጹ ሲሆን በተለይም ሥውር ትስስሮች የጥቅም ግጭቶች ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም የሕግና የአሠራር ክፍተቶች ለሙስና ወለድ ወንጀሎች መፈጠርና መስፋፋት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ አመላክተዋል።   የሙስና ትግል በወቅታዊ ዘመቻዎች ብቻ የሚገደብ ሳይሆን በተቋማት የዕለት ተዕለት አሠራር ውስጥ የሚካተት ቀጣይነት ያለውና ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና በሕግ የበላይነት ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበትም ዳይሬክተሯ የተናገሩ ሲሆን የሙስና ምልክቶችን ቀድሞ በመለየት የቁጥጥር ሥርዓቶችን ማጠናከር እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽ ማድረግና የሕዝብ ተሳትፎን ማሳደግ የፀረ-ሙስና ትግሉ ቁልፍ መሣሪያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።   በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ሙስና የሕዝብንና የመንግሥት ተቋማት እምነት ከማሳጣት ባለፈ የአገልግሎት ፍትሐዊነትንና የአገርን የእድገት ጉዞ የሚጎዳ መሆኑን ገልጸዋል።   ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የመንግሥት ተቋማት የሕዝብን እምነት ለማግኘትና ለማስቀጠል በሕግ የበላይነት፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና በብቃት ላይ የተመሠረተ አሠራር መከተል እንዳለባቸው የጠቀሱ ሲሆን የሀገር ልማትና የመንግሥት የለውጥ ጥረቶች ውጤታማ እንዲሆኑ የሕዝብ ሀብትና ሀላፊነት በአግባቡ መጠበቅ እንዳለበት በመግለጽ እያንዳንዱ አመራርና ሠራተኛ በሥራው ታማኝነትንና ሙያዊ ሥነ-ምግባርን ማስቀደም እንደሚገባው ተናግረዋል።   አቶ ዮሴፍ በኤጀንሲው ከሚሰጡ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የጥቅም ግጭቶችን፣ የሕግ ጥሰቶችንና ማንኛውንም ከሙስና ጋር የተያያዘ አሠራር ለመከላከል ተቋማዊ ቁጥጥርን ማጠናከርና ለሕዝብ ክፍት የሆነ የአገልግሎት ሥርዓት መገንባት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው የፀረ-ሙስና ትግል የተወሰኑ አካላት ኃላፊነት ሳይሆን የተቋሙ አመራር ፣ሠራተኛና አገልግሎት ተጠቃሚ የጋራ ተሳትፎን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑንም አስገንዝበዋል።   በመጨረሻም በተነሱ ሀሳቦችና አስተያየቶች ዙሪያ በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡   ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ይደውሉ   የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et   ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et     ፌስቡክ(Facebook):https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686     ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress   ዩቱዩብ (youtube): https://www.youtube.com/@CRRSA193 ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/@aacrrsa_head_office   ኢንስታግራም(Instagram)https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/ ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

Открыть в Telegram
Просмотры1 630+19%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#14398Превью ссылки

ኤጀንሲው በ13ኛው የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ውድድር " የአራተኛ ደረጃ እዉቅና ሰርተፊኬት" ተሸላሚ ሆነ CRRSA: ህዳር 14/2019ዓ.ም አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተወዳዳሪ አገልግሎት ሰጪ ተቋም መሆን እንዲችል በ13ኛው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ውድድር( EQA) ላይ የተሳተፈ ሲሆን በዚሁ መሰረት በታላቁ ቤተ-መንግስት ህዳር 12/2019 ዓ.ም በተዘጋጀው የእውቅና መድረክ የአራተኛ ደረጃ የጥራት እዉቅና ሰርተፊኬት / Fourth level Quality Recognition Certificare / ተሸላሚ ሆኗል። ተቋሙ ለህዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል ከተለመደው አሰራር በመውጣት ተወዳዳሪ ሊያደርገው የሚችሉ አለም አቀፍ መስፈርትን መሰረት ያደረገ አዲስ ሲስተም አልምቶ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በማምጣት ተገልጋዮች ከቤታቸዉ ሆነዉ በኦንላይን (https://portal.aacrrsa.gov.et) አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት አሰራር በመዘርጋት የተገልጋዩን እርካታ አሁን ካለበት ለመጨመር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተነግሯል። ኤጀንሲው በ13ኛው ሃገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር ላይ አመልክተው ከተወዳደሩ እና የደረጃውን እውቅና ካገኙ ጥቂት ድርጅቶች ብቸኛ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋም በመሆን የደረጃዉን እዉቅና ያገኘ ሲሆን በዉድድሩ በማመልከት፣ መመዘኛዎችን በመሙላት እንዲሁም የተሰሩ ስራዎች የመስክ ምልከታ ሂደትን ጭምር አልፏል። ተቋሙ በህዝብ የተመሰከረለት ጥራት ያለው አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሆኖ ማየት እስኪቻል የሃገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር ተሳታፊ ሆኖ እንደሚቀጥል በዕለቱ ሽልማቱን ተገኝተው የወሰዱት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ የተናገሩ ሲሆን ውድድሩን የመንግስት ተቋማት በስፋት እንዲሳተፉና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ደረጃቸዉን እንዲፈትሹ፤ እንዲያሻሽሉ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን እንዲያቁ የሚያስችል የዉድድር ዓይነት መሆኑን ገልፀዋል።       ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ይደውሉ የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et ፌስቡክ(Facebook):https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686 ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress ዩቱዩብ (youtube): https://www.youtube.com/@CRRSA193 ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/@aacrrsa_head_office ኢንስታግራም(Instagram)https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/ ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

Открыть в Telegram
Просмотры1 580+15%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—