Кабинет

Посты канала አዲስ ሪፖርተር - NEWS

сначала новые

#32262Фото

«የተዘረፈውን የሕዝብ ሀብት በማስመለስ ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል» – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት   የ7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ሲሆን፣ ከቀረቡት ጉዳዮች መካከል ብልሹ አሠራር እና ሙስና ዋነኛው መሆኑ ተገልጿል።   የምክር ቤቱ አባላት በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ፣ ዜጎችን የሚያስለቅሱ እና ሥልጣናቸውን ለበደል የሚጠቀሙ አካላት መኖራቸው በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን እምነት እየሸረሸረ ይገኛል።   እነዚህ ጥቂት ሙሰኞች የሕዝብን ሀብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ እንደሚገኙ የጠቆሙት አባላቱ፣ ችግሩን ለመቅረፍ በዲጂታል ሥርዓት ላይ እንደ ሀገር እየተሠራ ቢሆንም ሙስና አሁንም ስጋት ሆኖ መቀጠሉን አመላክተዋል።   ለሀገር ልማት መዋል የሚገባው ሀብት በጥቂት ሙሰኞች ኪስ መግባቱ የትውልዱን ሞራል እየገደለ መሆኑን ያነሱት የምክር ቤቱ አባላት፣ ችግሩን ማውገዝ ብቻ በቂ ባለመሆኑ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ እና የዘረፉትን የሕዝብ ሀብት እንዲመልሱ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።   @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры1 230−68%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#32261Фото
Просмотры2 520−34%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч1 430
5 ч2 520
  1. Через 6 часов2 520
  2. Всего сейчас2 520
#32260Фото

ሲኤንኤን በኢትዮጵያ መቀመስ አለባቸው ያላቸውን 15 ምርጥ ምግቦች ይፋ አድርጓል ዓለም አቀፉ የዜና አውታር የሆነው ሲኤንኤን፡ የኢትዮጵያን የምግብ ባህል ልዩና ጣፋጭ ሲል በማድነቅ፣ ጎብኚዎች ሊቀምሷቸው የሚገቡ 15 ምርጥ የሀገሪቱን ምግቦች በዝርዝር አስቀምጧልል። በሲኤንኤን የጉዞ አምድ ላይ የቀረበው ዘገባ፣ የኢትዮጵያ የአመጋገብ ሥርዓት ከሌላው የአፍሪካ ክፍል የሚለይ የባህል ቅርስ ያለው መሆኑን ተገልጿል። ኢትዮጵያውያን በአንድ ገበታ ተሰብስበው ያለ ሹካና ማንኪያ በእጅና በእንጀራ የሚመገቡበት ማኅበራዊ ባህል እንዲሁም እስከ 16 ቅመማ ቅመሞችን የያዘው በርበሬ ለምግቦቹ ልዩ ጣዕም እንደሚሰጣቸው ተገልጿል። ዘገባው ከዘረዘራቸው ምግቦች መካከል ሸክላ ጥብስ፣ ክትፎ፣  ዶሮ ወጥ፣ ጥሬ ሥጋ፣ ዱለት፣ ዶሮ ወጥ፣ በያይነት፣ ጥህሎ፣ ፉል፣ እንቁላል ፍርፍር፣ሽሮ፣ የአትክልት ጁስ፣ ዳቦ ፍርፍር፣ ጥብስ እንዲሁም ፓስታ በእንጀራ  ይገኙበታል። ዘገባው አክሎም ኢትዮጵያ የጥራት ያለው ቡና መገኛ መሆኗን በማስታወስ፣ ከእነዚህ ጣፋጭ ምግቦች በኋላ የኢትዮጵያን ቡና መቅመስ  አስፈላጊ ነው ሲል አስነብቧል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры2 050−46%к среднему
Пересылки—
Реакции26
Комментарии—
#32259Фото

መርጌታ  ሊባኖስ  የባህል መድህኒት ፈውስ  የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል ☞  ለመፍትሄ ሀብት ☞  ለህመም ☞  ለመስተፋቅር ☞  ቡዳ ለበላው ☞  ለገበያ ☞  ሚስጥር የሚነግር ☞  ለቀለም(ለትምህርት) ☞  ለመፍትሔ ስራይ ☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ ☞  ሌባ የማያስነካ ☞  ለበረከት ☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) ☞  ለግርማ ሞገስ ☞  መርበቡተ ሰለሞን ☞  ለዓይነ ጥላ ☞  ለሁሉ መስተፋቅር ☞  ጸሎተ ዕለታት ☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ ☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) ☞  ለትዳር ☞  ለድምፅ 👉 0924431917 ይደውሉ መፍትሄ አለን 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🍀🌿🙏 መርጌታ    የባህል ህክምና ቀማሚ ከፈጣሪ በታች በተሰጠን ሰለሞናዊ ጥበባችን በአለም አቀፋ እዉቃና አግኝተን የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን🇪🇹። 📞09 24431917 📞09 24431917 👉 የብልት ማነስ 👉የመልፈስፈስ 👉ቶሎ የመጨረስ(የመርጨት) ችግር አለብዎት ባልሽስ አለበት      ለበለጠ መረጃ     👉በቴሌግራም ማውራት ለሚፈልግ ከታች ይጫኑ 👇👇👇 @mergitali በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሀለየ ይፌፅም                           🍀🌿 🙏በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር  ውጭም  ሆነ  ከአገር ውስጥ  መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን   🍀🌿🙏ልብ ይበሉ  ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ ራሳችሁን ከአጭበርባሪወች ጠብቁ!

Открыть в Telegram
Просмотры1 860−51%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#32258Фото

ለChatGPT ወይም ለGemini "ሰላም" ስትለው፣ እሱ በዚያው ቅጽበት አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውኃ ጭልጥ አድርጎ እንደሚጠጣ ታውቃለህ? 😂💧 የምንጠቀምበትን ኢንተርኔት፣ ክላውድ (Cloud) እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚያንቀሳቅሱት ግዙፍ የዳታ ማዕከላት (Data Centers) ጉሮሯቸው በጣም ደረቅ ነው! ሰርቨሮቻቸው ከመጠን በላይ ግለው እንዳይቃጠሉ ለማቀዝቀዝ በቀን እስከ 5 ሚሊዮን ጋሎን ንጹሕ ውኃ ይጠጣሉ። እስቲ ይህንን አስቡት አንድ ትልቅ የዳታ ማዕከል በቀን ከ1 እስከ 5 ሚሊዮን ጋሎን ውኃ ይጠቀማል። ይህ ማለት 50,000 ሕዝብ ያላትን አንዲት ሙሉ ከተማ የውኃ ፍጆታ ብቻውን ይጨርሳል ማለት ነው፤ ከእነዚህ ጋር ውኃ መጋራት ራሱ ይከብዳል! ዋናው ችግር ደግሞ የተጠቀሙት ውኃ ተመልሶ አለመገኘቱ ነው። "የጠጡት" ውኃ በትነት መልክ ወደ ሰማይ ስለሚወጣ፣ ተመልሶ ወደ ወንዙም ሆነ ወደ ቧንቧችን አይገባም። የሚገርመው ደግሞ ከ2022 ወዲህ ከተገነቡት አዳዲስ ማዕከላት መካከል ሁለት ሦስተኛው የተተከሉት ቀድሞውኑ ከፍተኛ የውኃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች መሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት የአካባቢው ገበሬ ቤተሰቡና እንስሳቱ በውኃ ጥም እየተቸገሩ፣ ሰርቨሮቹ ግን "ውኃ አምጡ" ይላሉ። ይበልጥ አሳሳቢው ግን የወደፊቱ ስጋት ነው! በቴክሳስ ብቻ በ2025 ወደ 49 ቢሊዮን ጋሎን ውኃ የጠጡት እነዚህ ማዕከላት፣ በ2030 ጥማታቸው ጨምሮ 399 ቢሊዮን ጋሎን ሊደርስ እንደሚችል ተተንብዮአል። ቴክኖሎጂው መልካም ነው፤ ሕይወታችንንም አቅልሎልናል። ሆኖም የሰው ልጅንና የተፈጥሮን ጉሮሮ እያደረቀ መሆን የለበትም አይደል? አዳዲስ የዳታ ማዕከላት ከመገንባታቸው በፊት "ውኃውን ከየት ነው የምታመጡት? ስንትስ ትጠቀማላችሁ?" ተብለው ሊጠየቁ ይገባል። @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры2 700−29%к среднему
Пересылки—
Реакции34
Комментарии—
#32257Фото
Просмотры3 430−10%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#32256Фото

ቡርኪናፋሶ 61.5ሚሊዮን ዶላር የፈጀ ግዙፍ የቴክኖሎጂ አካዳሚ መርቃ ከፈተች ቡርኪናፋሶ የወደፊት መሐንዲሶችን ለማፍራት፣ ሳይንሳዊ ነፃነትን ለማጎልበት እና የኢንዱስትሪ እድገትን ለማፋጠን ያለመ 61.5 ሚሊዮን ዶላር የፈጀ የቴክኖሎጂ አካዳሚ እ.ኤ.አ. ኅዳር 23 ቀን 2026 መርቃ ከፈተች። ​ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ፣ በሀገሪቱ ብሔራዊ በጀት በተመደበ 37.37 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እና በ11 ወራት ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀውን አካዳሚ ቴክኖሎጂክ ዱ ፋሶ የተሰኘውን ተቋም በይፋ መርቀው ከፍተዋል። ​60 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ካምፓስ፣ በመጀመሪያ ዙር 250 ተማሪዎችን ተቀብሎ የኒውክሌር ምህንድስና፣ አቪዬሽን (ኤሮኖቲክስ)፣ ማዕድን ማውጣት፣ ብረታ ብረት፣ ኢነርጂ እና የሳይበር ደህንነትን ጨምሮ በ11 ስትራቴጂካዊ የትምህርት መስኮች ስልጠና ይሰጣል። ​የሀገሪቱ አመራሮች ተቋሙን የገነቡት በሀገር ውስጥ የበቀለ የቴክኒክ ባለሙያዎችን ለማፍራትና የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን ይበልጥ ለማጠናከር በማለም ነው። @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры4 140+9%к среднему
Пересылки—
Реакции41
Комментарии—
#32255Фото

ጥንቃቄ ‼️ ሰዎች በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ጥሪ እየደረሳቸው ይገኛል፦ •  +947 •  +371 •  +563 •  +370 •  +255 ወይም በእነዚህ መነሻዎች የሚጀምሩ ማንኛውም ቁጥሮች፦ +371፣ +375፣ +381 እነዚህ አካላት አንድ ጊዜ ብቻ ደውለው ይዘጋሉ። ተመልሰው ከደወሉላቸው በ3 ሰከንድ ውስጥ በስልክዎ ላይ ያለውን የሰው ዝርዝር (Contact list) መውሰድ ይችላሉ፤ እንዲሁም በስልክዎ ላይ የባንክ ወይም የክሬዲት ካርድ መረጃዎች ካሉ በቀላሉ ያገኟቸዋል። የሀገራት መለያ ኮዶች፦ •  +375 - ቤላሩስ (Belarus) •  +371 - ላቲቪያ (Latvia) •  +381 - ሰርቢያ (Serbia) •  +563 - ቫልፓራይሶ (Valparaiso) •  +370 - ቪልኒየስ (Vilnius) •  +255 - ታንዛኒያ (Tanzania)                                                                                                                            መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች፦ 1.ለእነዚህ ቁጥሮች አይመልሱ ወይም ተመልሰው አይደውሉ። 2.ማንኛውም ደዋይ በስልክዎ ላይ #90 ወይም #09 እንዲጫኑ ቢጠይቅዎት በፍጹም እንዳያደርጉት። ይህ ዘዴ የእርስዎን ሲም ካርድ (SIM card) ለመቆጣጠር፣ በእርስዎ ወጪ ስልክ ለመደወል እና እርስዎን ለወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የሚጠቀሙበት አዲስ ሴራ ነው።                                                                ይህንን የጥሰት ሙከራ ለመከላከል ይህንን መልዕክት በተቻለዎት መጠን ለብዙ ጓደኞችዎ ያጋሩ (Forward ያድርጉ)!!! @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры4 790+26%к среднему
Пересылки—
Реакции30
Комментарии—
#32254Фото

🎈መገናኛ ዲያስፖራ  ጫካ ፕሮጀክት ፊትለፊት      ✅  100% ለከፈለ 35% በነፃ ነው      ✅ 40/60 አከፋፈል አመቻችተናል 👉 ባለ 1 መኝታ 60 ካሬ 👉 ባለ 2 መኝታ 90,99 ካሬ 👉 ባለ 3 መኝታ 120 -145 ካሬ ዋጋ እና አከፋፈል ☑️ ባለ 1 መኝታ 60 ካሬ         ጠቅላላ ክፍያ = 7.2 ሚልዮን ብር         ቅድመ ክፍያ 20% =  1.4ሚልዮን      🔑100% ለሚከፍል=4.6ሚሊዮን ብር ☑️ባለ 1 መኝታ 69ካሬ     ጠቅላላ ክፍያ=8.2 ሚሊዮን ብር    ቅድመ ክፍያ=1.6 ሚሊዮን ብር 🔑100 % ለሚከፍል=5.3 ሚሊዮን ብር ☑️ ባለ 2 መኝታ 90ካሬ        ጠቅላላ ክፍያ =  10.8 ሚልዮን ብር        ቅድመ ክፍያ 20% =  2.1 ሚልዮን ብር     🔑100% ለሚከፍል= 7 ሚሊዮን ብር ☑️  ባለ 2 መኝታ 99 ካሬ        ጠቅላላ ክፍያ = 11.8 ሚልዮን        ቅድመ ክፍያ 20% = 2.3 ሚልዮን    🔑100% ለሚከፍል=7.7 ሚሊዮን ብር ☑️ባለ 3 መኝታ 120 ካሬ           ጠቅላላ ክፍያ=14.4 ሚሊዮን ብር              ቅድመ ክፍያ=2.8 ሚሊዮን ብር   🔑100% ለሚከፍል=10 ሚሊዮን ብር ☑️ባለ 3 መኝታ 145  ካሬ          ጠቅላላ ክፍያ=17.4 ሚሊዮን ብር            ቅድመ ክፍያ=3.4 ሚሊዮን ብር 🔑100% ለሚከፍል=12.1 ሚሊዮን ብር      ቀሪ ክፍያ 👉 ያለ ምንም ዋጋ ጭማሪ 👉 ከወለድ ነፃ አከፍፈል 👉 በግንባታ ሂደት የሚከፈል ✅ WhatsApp call=https://wa.me/message/Z5LFLDJBTZUDK1 ✅Telegram =@Temerr34    ☎️ 09-82-15-16-64

Открыть в Telegram
Просмотры3 770−1%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#32252Фото

በጎጃምና በጎንደር ሕዝብ ላይ በጅምላ ስም ማጥፋትና የጥላቻ ንግግር ወንጀል ተፈጽሟል በሚል በአቶ ኢዩ ጩፋ ላይ ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ጥቆማ ቀረበ ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሰለሞን ገዛኸኝ፣ አቶ ኢዩ ጩፋ በሃይማኖት ስብከት ሽፋን በጎጃምና በጎንደር አካባቢ ሕዝብ ላይ በጅምላ ስም የማጥፋት፣ የማዋረድና የጥላቻ ንግግር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ትናንት ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ይፋዊ የወንጀል ጥቆማ አቅርበዋል። በጥቆማው ላይ እንደተመለከተው፣ ተጠሪው በኅዳር ወር 2019 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ በተካሄደ ስብሰባ ላይ የምዕራብ፣ የምሥራቅ፣ የሰሜን ጎጃምንና የአዊ አካባቢ ሕዝብን «መተተኞች» በማለት በጅምላ መፈረጃቸውና ይህም በማኅበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨቱ የሕዝቡን የሥራ ትጋትና እሴት የሚያንቋሽሽ፣ እንዲሁም ተወላጆቹን በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ በጥርጣሬ እንዲታዩ የሚያደርግ ነው ተብሏል። በተጨማሪም በሌላ የስብከት መድረክ ላይ የጎንደርንና የጎጃምን ሕዝብ ዒላማ በማድረግ «የጎጃም የሌ፣ የጎንደር የሌ፤ እዚህ ቤት የገባ ሁሉ ይቀጠቀጣል፣ ይረገጣል፤ የትም ይሥራ እናፈርሰዋለን» በማለት የጥላቻና የማስፈራሪያ ንግግር ማድረጋቸው በጥቆማ ደብዳቤው ተጠቅሷል። ድርጊቱ የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግን (ስም ማጥፋትና ሕዝብን ማነሳሳት)፣ የጥላቻ ንግግርንና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 እንዲሁም የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008ን የሚጥስ መሆኑን ጠበቃው ገልጸው፤ የቪዲዮ ማስረጃዎችን በማያያዝ ፖሊስ ተገቢውን ምርመራ አጣርቶ ተጠሪውን ለፍትሕ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры3 900+2%к среднему
Пересылки—
Реакции64
Комментарии—
#32251Фото

በመቐለ ከተማ ከሚገኙ 15 የነዳጅ ማደያዎች 12 ስራ ጀመሩ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ከሚገኙ 15 የነዳጅ ማደያዎች መካከል 12ቱ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋይ ግርማይ አስታወቁ። በመቐለ ከተማ 750 የሕዝብ ትራንስፖርት ታክሲዎች እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊው፣ ለነዚህ ታክሲዎች ቅድሚያ የነዳጅ አቅርቦት እንዲሰጣቸው በማድረግ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ እና አገልግሎት እንዲገቡ መደረጉን ገልፀዋል። የተወሰዱት እነዚህ እርምጃዎች በከተማዋ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን እንዲሁም የነዳጅ ስርጭትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ያለሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ነዳጅ ለታለመለት ዓላማ ብቻ መዋሉን እና አለመዋሉን ለመለየትና ለመቆጣጠር እንዲያስችል፣ የነዳጅ ሽያጭ በቴሌብር ዲጂታል ግብይት ብቻ እንዲፈጸም መመሪያ መውጣቱ ተገልጿል። በነዳጅ አቅርቦት ላይ ምንም ዓይነት መቆራረጥ ወይም እጥረት እንዳይፈጠር ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑንም የቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋይ ግርማይ ጨምረው ገልጸዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры4 400+16%к среднему
Пересылки—
Реакции21
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
22 ч4 290
24 ч4 400
  1. Через 24 часа4 400
  2. Всего сейчас4 400
#32249Фото

የከተማ አስተዳደሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ - ለሕንጻ ገንቢዎች በአዲስ አበባ ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሕንጻዎች በፍጥነትና በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ተጠናቀው ከቀጣዩ ዓመት በፊት ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የኮፕ 32 የዓለም አቀፍ መድረክ ዝግጅት አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር በከንቲባ ጽሕፈት ቤት ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው። በውይይቱ ላይ በከተማዋ የሚገኙ የሪል እስቴት ፣ የአፓርታማ ፣ የሆቴልና የገስት ሀውስ አልሚዎች እና የሕንፃ ባለሀብቶች ፣ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት መገኘታቸው ታውቋል። በከተማዋ የሚገኙ ነባር ሕንፃዎችም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ ታድሰው ለመድረኩ ዝግጁ እንዲደረጉ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል። ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ መመረጧ ለኢኮኖሚ ዕድገት ፣ ለቱሪዝም መስፋፋትና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ዕድል ይዞ የሚመጣ ነው። ኮንትራክተሮች ፣ አማካሪዎች ፣ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም የመሠረተ ልማት አቅራቢና የፋይናንስ ተቋማት በቅንጅት በመስራት ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры4 590+21%к среднему
Пересылки—
Реакции18
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
23 ч4 500
26 ч4 590
  1. Через 24 часа4 500
  2. Всего сейчас4 590
#32248Текст

መብራት አብርቶ መተኛት ለከፋ የልብ በሽታና ያለዕድሜ ሞት እንደሚዳርግ ተገለጸ‼️ በምሽት የመኝታ ሰዓት መብራት አብርቶ መተኛት ወይም ለደማቅ ብርሃን መጋለጥ ለከፋ የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች እንዲሁም ያለዕድሜ ለሚከሰት ሞት የመጋለጥ ዕድልን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር አንድ አዲስ ሳይንሳዊ ጥናት ይፋ አደረገ። «ጄኤምኤ ኔትወርክ ኦፕን»  በተሰኘው ታዋቂ የሕክምና ጆርናል ላይ የታተመው ይህ ጥናት፣ በእንቅልፍ ወቅት ለብርሃን መጋለጥና በልብ ጤንነት መካከል ያለውን ጥብቅ ቁርኝት በዝርዝር ፈትሿል ብሏል ቻነል 1። ተመራማሪዎቹ ጥናቱን ያካሄዱት በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙና ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ በሆኑ ወደ 88 ሺህ ገደማ ሰዎች ላይ ሲሆን፣ ሁሉም ተሳታፊዎች ጥናቱ በተጀመረበት ወቅት ምንም ዓይነት የልብና የደም ቧንቧ ሕመም ያልነበረባቸው ጤነኞች ነበሩ። የጥናቱ ቡድን ከእኩለ ሌሊት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ባለው የእንቅልፍ ጊዜ ውስጥ ተሳታፊዎቹ ለብርሃን ያላቸውን ተጋላጭነት በቅርበት የተከታተለ ሲሆን፣ የተገኘውን ውጤት ከተሳታፊዎቹ የረጅም ጊዜ የሕክምና መረጃዎች ጋር በማነጻጸር ገምግሟል። በዚህም መሠረት በምሽት ለከፍተኛ ብርሃን የተጋለጡ ሰዎች እንደ የልብ ደም ወሳጅ ቧንቧ በሽታ፣ የልብ ድካም፣ የልብ ምት መዛባት እና ስትሮክ ላሉ አደገኛ የጤና እክሎች የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል። በቁጥር ሲሰላም በጨለማ ከሚተኙት ጋር ሲነጻጸሩ ለደም ግፊት የመጋለጥ ዕድላቸው ከ45 እስከ 56 በመቶ፣ ለልብ ምት መዛባት የመጋለጥ ዕድላቸው ደግሞ ከ28 እስከ 32 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በሌላ በኩል ጥናቱ በቀን ክፍለ ጊዜ ለተፈጥሮ የፀሐይ ብርሃን በበቂ ሁኔታ የሚጋለጡ ሰዎች ለልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች የመጋለጥ ዕድላቸው በእጅጉ ዝቅተኛ መሆኑን አረጋግጧል። ስለሆነም የጤና ባለሙያዎችና ተመራማሪዎቹ ኅብረተሰቡ የልብ ጤንነቱን ለመጠበቅ አሁን ካሉት የሕክምና ምክሮች በተጨማሪ፣ በምሽት መኝታ ክፍልን በማጨለምና ለሰው ሠራሽ ብርሃን መጋለጥን በማስወገድ የልብ በሽታን መከላከል እንደሚችል አሳስበዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры4 750+25%к среднему
Пересылки—
Реакции18
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
24 ч4 650
27 ч4 750
  1. Через 24 часа4 650
  2. Всего сейчас4 750
#32246Фото
Просмотры4 390+15%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#32245Фото
Просмотры4 320+13%к среднему
Пересылки—
Реакции33
Комментарии—
#32244Фото

መርጌታ  ሊባኖስ  የባህል መድህኒት ፈውስ  የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል ☞  ለመፍትሄ ሀብት ☞  ለህመም ☞  ለመስተፋቅር ☞  ቡዳ ለበላው ☞  ለገበያ ☞  ሚስጥር የሚነግር ☞  ለቀለም(ለትምህርት) ☞  ለመፍትሔ ስራይ ☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ ☞  ሌባ የማያስነካ ☞  ለበረከት ☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) ☞  ለግርማ ሞገስ ☞  መርበቡተ ሰለሞን ☞  ለዓይነ ጥላ ☞  ለሁሉ መስተፋቅር ☞  ጸሎተ ዕለታት ☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ ☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) ☞  ለትዳር ☞  ለድምፅ 👉 0924431917 ይደውሉ መፍትሄ አለን 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🍀🌿🙏 መርጌታ    የባህል ህክምና ቀማሚ ከፈጣሪ በታች በተሰጠን ሰለሞናዊ ጥበባችን በአለም አቀፋ እዉቃና አግኝተን የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን🇪🇹። 📞09 24431917 📞09 24431917 👉 የብልት ማነስ 👉የመልፈስፈስ 👉ቶሎ የመጨረስ(የመርጨት) ችግር አለብዎት ባልሽስ አለበት      ለበለጠ መረጃ     👉በቴሌግራም ማውራት ለሚፈልግ ከታች ይጫኑ 👇👇👇 @mergitali በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሀለየ ይፌፅም                           🍀🌿 🙏በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር  ውጭም  ሆነ  ከአገር ውስጥ  መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን   🍀🌿🙏ልብ ይበሉ  ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ ራሳችሁን ከአጭበርባሪወች ጠብቁ!

Открыть в Telegram
Просмотры4 240+11%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#32243Фото

በኢትዮጵያ አብዛኞቹ ወጣቶች ኮንዶም ከመጠቀም ይልቅ ወደ “ፖስት ፒል” ማዘንበላቸውን አንድ ጥናት አመላከተ በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኞቹ ወጣቶች ኮንዶምን ከመጠቀም ይልቅ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንክብል (ፖስት ፒል) መጠቀምን እየመረጡ መሆኑን “ኤድስ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን” የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጥናትን ዋቢ አድርጎ አስታውቋል። ተቋሙ ይህንን የጥናት ግኝት ይፋ ያደረገው በአዲስ አበባ 5ኛው የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ጉባኤ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው። በተቋሙ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ቶለሳ ኦላና ጥናቱን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት በጥናቱ ግኝት መሠረት እንደ ሀገር ወጣቶች የኮንዶም አጠቃቀምን እየተዉ ወደ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች ማዘንበላቸው አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ጥናቱ እንደሚያመለክተው ወጣቶች ዋነኛ ትኩረት የሚሰጡት ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል ብቻ በመሆኑና ኮንዶምን በአግባቡ ባለመጠቀማቸው ምክንያት ለኤች.አይ.ቪ እና ለሌሎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት ለሚተላለፉ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተጋለጡ ይገኛሉ። አቶ ቶለሳ አክለውም ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች እርግዝናን ከመከላከል ባለፈ ከማንኛውም የአባለዘር በሽታዎች እና ከኤች.አይ.ቪ እንደማይከላከሉ ወጣቶች በቂ ግንዛቤ ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳስበዋል። የጤና ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በወጣቶች ዘንድ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላትና የኮንዶም አጠቃቀም ባህልን መልሶ ለማሳደግ የተቀናጀ ሥራ እንዲሠሩ ፋውንዴሽኑ ጥሪ አቅርቧል።via.አሀዱ @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры4 700+23%к среднему
Пересылки—
Реакции28
Комментарии—
#32242Фото
Просмотры4 660+22%к среднему
Пересылки—
Реакции20
Комментарии—
#32241Текст

በሰቆጣ ከተማ የተጣለው ቅጣት‼️ አማራ ክልል ዋግኸምራ ሰቆጣ ከተማ አላስፈላጊ ወጪዎችንና ጎጂ ልማዶችን ለመቀነስ አዳዲስ ክልከላዎችና ለማስቆም የተወሰኑ ውሳኔዎች። ​1. ከጋብቻ (ሰርግ) ጋር የተያያዙ ውሳኔዎች ​በእጮኝነት ጊዜ ልብስ ለማልበስ ከ5 ሰዎች በላይ ይዞ መሄድ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። ​በሰርግ ዋዜማ ለጥሎሽ/ልብስ ከ5 ሰዎች በላይ ይዞ መሄድ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። ​ከሰርግ በኋላ ለትውውቅ/ምላሽ (ቅልቅል) ከሰርግ ያልተናነሰ ድግስ መደገስ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። ​በሰርግ ጊዜ ከ25 ሰው በላይ መዝመት ወይም ለተለያዩ ፕሮግራሞች ዩኒፎርም (ተመሳሳይ ልብስ) መልበስ ዋናው ባለጉዳይ 30,000 ብር፤ ለብሰው የሚገኙ አካላት እያንዳንዳቸው 10,000 ብር ቅጣት። ​ለሰርግ በኪራይ ወይም በግዥ የሚዘጋጅ ስቴጅ (መድረክ) እና ከልክ ያለፈ ዲኮሬሽን መጠቀም 20,000 ብር ቅጣት የማይገኝ ሀብት/ማጫ በሐሰት መናገር ማጫ በተጨባጭ ታይቶ መባል አለበት (በዳስ አባቶች ይረጋገጣል)። ​2. ከልዩ ልዩ ድግሶችና በዓላት ጋር የተያያዙ ​በሠርግ እና በክርስትና ዕለት ቡፌ እና ኬክ ማዘጋጀት 50,000 ብር ቅጣት ​የተማሪዎች ከKG ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ የምረቃ ድግስ ማዘጋጀት 30,000 ብር ቅጣት። ​የቤቢ ሻወር (Baby Shower) እና የጋብቻ ዓመታዊ በዓል (Anniversary) ማክበር 10,000 ብር ቅጣት የጽዋ ማህበራት ዩኒፎርም መልበስ እና ታይታ ያለበት ድግስ ማዘጋጀት እያንዳንዱ አባል 10,000 ብር ቅጣት። ​በማንኛውም ፕሮግራም (ክርስትና፣ ልደት፣ ምንኩስና፣ ቤት ሲሰራ ወዘተ) አረቄ ይዞ መሄድ  ፈጽሞ የተከለከለ ነው፤ ተቀብሎ ያስተናገደ ባለቤት 20,000 ብር ይቀጣል። ​3. ከሀዘንና ከፍትሃት ጋር የተያያዙ ​በፍትሃት ጊዜ ከፍተኛ ድግስ መደገስ፣ በ40 ቀን መቃብር ላይ ሻማ ማብራትና ዳቦ መቁረስ 20,000 ብር ቅጣት በሃዘን ጊዜ ውሃ ይዞ መሄድ የተከለከለ ነው (በምትኩ ገንዘብ፣ ስኳር እና ቆሎ ጋብቻ እንዲወስዱ ተገልጧል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Открыть в Telegram
Просмотры5 030+32%к среднему
Пересылки—
Реакции87
Комментарии—