በሱዳን በደረሰ የድሮን ጥቃት 3 ሰዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች መቁሰላቸው ተገለፀ‼️ በሱዳን ካርቱም በሚገኘው ካራሪ አካባቢ በሲቪል ዜጎች ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሦስት ሰዎች ሲገደሉ፤10 ሰዎች ቆስለዋል። ከቆሰሉት መካከልም አምስት ሕፃናት እንደሚገኙ የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። የካርቱም ገዥ አህመድ ኦስማን ሃምዛ በአል-ናኦ ሆስፒታል በመገኘት የቆሰሉትን ሰዎች የጎበኙ ሲሆን፤የጤና ሚኒስቴሩ ዋና ዳይሬክተር ማህሙድ አል-ባድሪ እና የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ጃማል አል-ታይብ አብረዋቸው ተገኝተዋል። ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች እንደገለጹት፤ፍንዳታው በአንድ ክፍል ላይ ያለውን ጣሪያ አፍርሶ በሕንፃው ግድግዳዎችም ላይ ጉዳት አድርሷል። አሁን ላይ ፖሊሶች በፍርስራሹ ስር የተቀበሩትን የሟቾች አስከሬን አውጥተው የቆሰሉትን ወደ ሆስፒታል አስተላልፈዋል። የካርቱም ገዥ በሰዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ያሉ ሲቪል ዜጎችን ማጥቃትን በማውገዝ፤ድርጊቱን ‹‹ሥነ-ምግባር የጎደለው ባህሪ››ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ሚሊሻው በጦርነቱ ወቅት ተመሳሳይ ድርጊቶችን ሲፈጽም ቆይቷል ብለዋል። ሱዳን ከሚያዚያ 15 ቀን 2023 ጀምሮ በከባድ ጦርነት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን፤ግጭቱ የተቀሰቀሰው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከመደበኛው የሱዳን ጦር ጋር እንዴት እንደሚዋሃድ በተፈጠረ አለመግባባት ነው። ጦርነቱ እስካሁን በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞት ሲዳርግ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ደግሞ ከመኖሪያቸው አፈናቅሏል። በተጨማሪም ሆስፒታሎችንና ሌሎች የጤና ተቋማትን ጨምሮ የሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ሰፊ ውድመት ደርሷል። @Addis_Mereja
Открыть в TelegramПосты канала Addis መረጃ™
ኤርትራ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ባድመ ማስጠጋቷ ተሰማ የኤርትራ መንግሥት በባድመ ከተማ አካባቢ ከሚገኘው ሰንበል እስከ ጓል ገምሃሎ ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ወታደሮችን ማሰማራቱን የፈረንሳይ የዜና ወኪል (ኤ.ኤፍ.ፒ) ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ ኤርትራ ወደ ባድመ አካባቢ ተጨማሪ ሠራዊትና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሚሊሻዎችን አስጠግታለች፤ ይህም በኢትዮጵያ መንግሥትና በኤርትራ በሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች መካከል በመጪው ጊዜ ሰፊ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። ይህንን ተከትሎ በሁለቱም ወገን ወታደራዊ ዝግጅትና የሠራዊት ስምሪት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሽራሮና በሰንበል መካከል ያለውን ይዞታውን አጠናክሯል። በተጨማሪም ሠራዊቱ ከባድ ሞርታሮችን በማስጠጋት ሽራሮንና ሂረትን በሚያገናኘው መንገድ ላይ እንዲሁም ከሽራሮ ከተማ በስተሰሜን 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኙ ስፍራዎች ላይ በብዛት ሰፍሯል። በአካባቢው እየታየ ያለው ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴና የጦርነት ዝግጅት ዳግም ጦርነት ሊፈነዳ ይችላል የሚል ከፍተኛ ፍርሃት በመፍጠሩ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ጥለው ለመፈናቀል ተገደዋል። @Addis_Mereja
Открыть в Telegram😭አሳዛኝ ዜና በወልቂጤ መድረክ ላይ «ደረቴን አቃጠለኝ» በማለት ድንገት ሕመም እንደተሰማው ገልጾ ወዲያው ህይወቱ አልፏል💔😭 አመለ ሸጋው ተወዳጁ ወጣት ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። ህልፈተ ሕይወቱ ያጋጠመው በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የዘቢዳር ቢራ ፋብሪካ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተጋባዥ ድምፃዊነት በተገኘበት ወቅት መሆኑ ታውቋል። ድምፃዊው በስፍራው የተገኘው ቢጂአይ ወልቂጤ ብራንች የሠራተኞች ቀንን ሲያከብር ለተዘጋጀው መርሐ ግብር እንደነበር ተገልጿል። ድምፃዊው በዝግጅቱ ስፍራ መድረክ ላይ እንደወጣ ገና ከመጀመሩ ይቅርታ ብሎ የወረደ ሲሆን፣ በኋላም «ደረቴን አቃጠለኝ» በማለት ድንገት ሕመም እንደተሰማው ተገልጿል። ከቦታው በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ወልቂጤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲወሰድ ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል። በዘመናዊ ሙዚቃዎቹ ሰፊ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሚኪያስ ቸርነት፤ «አሁን ገባኝ»፣ «የኔ ደሃ»፣ «ግርማ ሞገሴ ነሽ»፣ «ናተይ» እንዲሁም ከድምፃዊ ያሬድ ነጉ ጋር በጋራ በተጫወቱት «ጉዳዬ» በተሰኙት ተወዳጅ ሥራዎቹ በአድማጮች ዘንድ በስፋት ይታወቃል። በተጨማሪም «10 ከ 10 ይገባሻል» እና «ሰላም አላት» የተሰኙ አልበሞችን እንዲሁም በቅርቡ «እንዳማረ» የተሰኘውን ነጠላ ዜማ ለአድማጮች አድርሶ ነበር። ለባለቤቱ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መጽናናትን ይሁን Via_ጉርሻ @Addis_Mereja
Открыть в Telegramየትራምፕ አውሮፕላን ከቻይና ሲመለስ በሳይበር ስለላ ስጋት ምክንያት ስልኮች በልዩ መያዣ እንዲያዙ መደረጋቸው ተገለፀ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና የመመለሻ ጉዞ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች በቻይና የተጠቀሙባቸውን ስልኮች ምልክት የሚያቋርጡ ልዩ መያዣዎች ውስጥ እንዲያስቀምጡ ተጠይቀዋል። የኋይት ሀውስ እርምጃውን የወሰደው ፕሬዚዳንቱ በቻይና ቆይታቸው ወቅት ሊከሰት የሚችል የሳይበር ስለላ ስጋትን ለመቀነስ መሆኑ ተገልጿል። የሲቢኤስ ኒውስ ዘጋቢ ጄኒፈር ጃኮብስ እንደገለጸችው፣ አውሮፕላኑ ሼንዘንን ለቅቆ ሲመለስ አንድ የኋይት ሀውስ ሰራተኛ የሰራተኞችን ጊዜያዊ የመጠባበቂያ ስልኮች ሰብስቦ መረጃቸው እንዲጠፋ ወይም እንዲሰረዙ አድርጓል። ጋዜጠኞቹም በቻይና የተጠቀሙባቸው ስልኮች ከአሜሪካ እስኪደርሱ ድረስ እንደሚቆዩ እና ከአውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ እንደሚመለሱላቸው ተነግሯቸዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለ እርምጃው ሲጠየቁ፣ “ጥንቃቄ ማድረግ ፈልገን ነበር፤ ሰዎች መጠቀም የሌለባቸውን ስልኮች ይዘው እንዳይኖሩ በጣም ጥንቃቄ አድርገናል” ሲሉ ለኤንቢሲ ኒውስ ተናግረዋል። በተጨማሪም፣ ብዙ ጋዜጠኞች ቻይና ከመድረሳቸው በፊት መደበኛ ስልኮቻቸውን፣ ላፕቶፖቻቸውን እና ስማርት ሰዓቶቻቸውን የመረጃ ምልክትን በሚከላከሉ የፋራዴይ መያዣዎች ውስጥ በኤር ፎርስ ዋን ላይ አስቀምጠው ነበር። በቻይና የግል ስልኮቻቸውን ይዘው የገቡ ጋዜጠኞች ግን እስከ አሜሪካ መመለሻ ሰአታቸው ድረስ የሞባይል አገልግሎት ሳይኖራቸው ቆይተዋል። ትራምፕን የተሸከመው አውሮፕላን ሐሙስ ምሽት በጆይንት ቤዝ አንድሪውስ ካረፈ በኋላ፣ በፋራዴይ መያዣዎች ውስጥ የተቀመጡት ስልኮች ለጋዜጠኞቹ ተመልሰዋል። @Addis_Mereja
Открыть в Telegram“ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ብትገጥም ከባድ ዋጋ ትከፍላለች‼️ የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተንታኞች ማስጠንቀቂያ በቀጣናው የጂኦፖለቲካ ሁኔታ ላይ የሚነሱ ትንታኔዎች፣ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ወታደራዊ ግጭት መግባቷ ከባድ የሆነ የፖለቲካ፣ የደህንነትና የኢኮኖሚ ዋጋ ሊያስከፍላት እንደሚችል ያመለክታሉ። እነ ቲቦር ናጊን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ፖለቲካና ዲፕሎማሲ ላይ የሚያተኩሩ ተንታኞች፣ በውስጣዊ ጦርነት ክፉኛ የተጎዳው የሱዳን መንግሥታዊና ወታደራዊ አቅም ተጨማሪ ግጭትን ለመሸከም ያለውን አቅም በጥንቃቄ መመዘን እንዳለበት ያሳስባሉ። ሱዳን አሁን ካለችበት ውስጣዊ ቀውስ ሳትወጣ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ሌላ የጦርነት አዙሪት መግባቷ፣ የቀረውን አቅሟን ከማሟጠጥ ባለፈ የሀገሪቱን ቀውስ ይበልጥ ሊያባብስ ይችላል። ኢትዮጵያ ግን የራሷን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የመጠበቅ ሙሉ መብት አላት። የሀገር ጥቅምን በጥበብ፣ በዲፕሎማሲና በተዘጋጀ የመከላከያ አቅም ማስጠበቅ የሚጠይቅበት ወቅት ነው። የቀጣናው ሰላም በግጭት ሳይሆን በጋራ መከባበርና በዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ መጠበቅ አለበት። ሆኖም ኢትዮጵያ ለሰላም የምታሳየው ቁርጠኝነት የራሷን ብሔራዊ ጥቅም የመጠበቅ አቅሟን አያሳንስም። @Addis_Mereja
Открыть в Telegram«በባድመ እና አካባቢዋ የድሮን እና ከባድ መሳሪያ ድምጽ በተደጋጋሚ እየተሰማ ነው» ነዋሪዎች ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሚዋሰኑባት የድንበር ከተማ ባድመ እና አካባቢዋ ከትናንት ረቡዕ ምሽት ጀምሮ ተደጋጋሚ የድሮን እና ከባድ መሳሪያዎች ድምጽ ይሰማ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ተናገሩ።በአካባቢው ያየለው ውጥረት ተባብሶ መቀጠሉን ዓለማቀፉ የግጭት ተከታታይ ተቋም (ACLED) እና አንድ የደህንነት ምንጭ አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ የፌደራል ኃይሎች እና አጋሮች እንዲሁም በኤርትራ መንግስት ወታደሮች እና አጋሮቹ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ወደ ሙሉ ጦርነት የመግባት አፋፍ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።ትናንት ረቡዕ ምሽት ከባድመ ከተማ በ15 ኪሎሜትሮች ርቀት በምትገኘው ዲያራ በተባለች ቀበሌ አካባቢ የድሮን እና የከባድ መሳሪያ ጥቃት ድምጾች መሰማታቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። በጥቃቶቹ በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ነው ነዋሪው የገለጹት ባለፈው ወር ከባድመ ተገፍቶ የወጣው የኤርትራ ጦር ባለፈው ሳምንት ከተማዋን መልሶ መቆጣጠሩን የግጭት ተቆጣጣሪው ተቋም (ACLED) ገልጿል።በባድመ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያዎች መካሄዳቸውንና የኢትዮጵያ ኃይሎች ወደ ኤርትራ ግዛት ዘልቀው በመግባት መልሰው መውጣታቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ የደህንነት ምንጭ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። የኤርትራ ኃይሎች በባድመ አቅራቢያ በሚገኙት ጓል ገምሃሎ እና ሰምበል በተባሉ ሁለት የድንበር መንደሮች ከፍተኛ ተጨማሪ ጦር እና ከባድ ወታደራዊ መሳሪያዎች ማሰማራታቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። በተጨማሪም ከትግራይ፣ ከአፋር እና ከአማራ ክልሎች የተውጣጡ የኢትዮጵያ አማጽያን ጥምረት ለኤርትራ ድጋፍ በመስጠት በባድመ አካባቢ እንደሚገኙ በዓለም ዙሪያ የሚደረጉ ግጭቶችን እየተከታተለ የሚሰንደው አክሌድ (ACLED) የተባለ ተቋም አስታውቋል።በኢትዮጵያ በኩል ምሽጎች መቆፈራቸውን አንድ የሰብአዊ እርዳታ ምንጭ ለዜና ወኪሉ (ኤ ኤፍ ፒ) ገልጸዋል።ሁለቱ አገራት ወታደሮች እጅግ ተለዋዋጭ በሆነ ግንባር ላይ በቅርብ ርቀት መስፈራቸው ቀጥተኛና ዘላቂ ጦርነት የመቀስቀስ አደጋ ከፍ ማድረጉን ተቋሙ አክሌድ አስጠንቅቋል።ስለ ወቅታዊው ሁኔታ ከኤ ኤፍ ፒ ለቀረበላቸው ጥያቄ እስካሁን ከሁለቱም መንግስታት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም። Via DW @Addis_Mereja
Открыть в Telegram"ኢራን የኑክሌር መሣሪያ እንድታገኝ አንፈቅድም" ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ እንዳታገኝ አሜሪካ እንደማትፈቅድ ተናግረዋል፡፡ ትራምፕ ይህን ያሉት ከሩሲያ እና ከቻይና መሪዎች ጋር በተደረገው የሶስትዮሽ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ባደረጉት አጭር ንግግር ነው። ፕሬዚዳንቱ አሜሪካ፣ ሩሲያ እና ቻይና ያላቸውን የኒኩሌር አቅም በመጥቀስ፣ በዓለም ላይ ያሉ የኒኩሌር መሣሪያዎችን ቁጥር ለመቀነስ ውይይት ለማድረግ በልዩ ሁኔታ የተቀመጡ እንደሆኑ ተናግረዋል። በተጨማሪም የኒኩሌር መስፋፋትን ስጋት ለመቋቋም በትብብር መሥራት “እጅግ አስፈላጊ” መሆኑን ጠቁመው፣ “ኢራን የኒኩሌር መሣሪያ እንድታገኝ አንፈቅድም” ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ትራምፕ ንግግራቸውን ወደ ዩክሬን ጦርነት በማስተላለፍ፣ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በጉዳዩ ላይ ረዘም ያለ ውይይት እንዳደረጉም ገልጸዋል። ትራምፕ፤ ፑቲን እና በግጭቱ ውስጥ ያለችው ሌላኛዋ ወገንም ጦርነቱን ለማቆም ፍላጎት እንዳላቸው ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። በተለይም ትራምፕ ከፑቲን ጋር ያደረጉት ውይይት እና ለሩሲያው መሪ የሰጡት አድናቆት ትኩረት ስቦ ውይይት እየፈጠረ ነው። @Addis_Mereja
Открыть в Telegramየኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ክልል የአየር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ማካሄድ መጀመሩ ተሰማ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ክልል ውስጥ የዝግጁነት እና የቴክኒክ የጦር ልምምድ እያካሄደ መሆኑን ተከትሎ፣ ሕብረተሰቡ የយሮፕላን ድምፆችን ሲሰማ በፍርሃትና በስጋት እንዳይደናገጥ ጥሪ ቀረበ። የሕዝብ ማስጠንቀቂያና የልምምዱ ዓላማ ነዋሪዎች ምንም ዓይነት ስጋትና ጭንቀት ሳይገባቸው መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲቀጥሉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። ይህ ወታደራዊ ልምምድ በአካባቢው መደረጉ የሰሜኑን አቅጣጫ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታዎች ለመቃኘት እንዲሁም ከኤርትራ ድንበር በኩል ሊከሰቱ የሚችሉ የትንኮሳ አደጋዎችን ለመመከት እና አጸፋ ለመስጠት ያለመ ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል። የሠራዊቱ የዝግጁነት ምዕራፍ የአየር ኃይሉ በዚህ መልከዓ ምድር አካባቢ እንዲህ ዓይነት ጥልቅ የዝግጁነት እንቅስቃሴዎችን ማድረጉ፣ በሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል የሚታዩ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶችንና የጸጥታ ሁኔታዎችን በብቃት ለመቆጣጠር ታቅዶ የሚከናወን መሆኑን የሚያሳይ ነው። @Addis_Mereja
Открыть в Telegramየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑካን እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች መቐለ ገቡ‼️ ልዑካኑ በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ መቐለ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች እና የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እና ሌሎች የባለአደራ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልኡካን ከዛሬ ኅዳር 8 ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ኦፊሴላዊ የሥራ ጉብኝት በመቐለ ከተማ ያካሂዳሉ። ልዑካኑ ከትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ ከሐይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሰብአዊ ዕርዳታ፣ ተፈናቃዮች፣ የዲዲአር (የትጥቅ የማስፈታት፣ የዲሞቢላይዜሽን እና የመልሶ ማቋቋም) ሂደት እንዲሁም የክልሉ ሰላም ጉዳይ ውይይት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው። @Addis_Mereja
Открыть в Telegramአቶ አደም ፋራህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ! አቶ አደም ፋራህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ኃላፊነቱን የተረከቡት ከሰኔ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተቋሙን ሲመሩ የቆዩትን እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ የሆኑትን ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳን በመተካት ነው። ሹመቱ የግዙፉ የመንግሥት የልማት ድርጅት ከፍተኛ አመራርን ከከፍተኛ የጦር መኮንን ወደ ከፍተኛ የፓርቲ ኃላፊ መሪነት ያዞረ ነው።ከሰኔ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት ሦስት ዓመት ከአምስት ወራት በኢትዮጵያአየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ሲመራ የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሥራ አመራር ቦርድ አዲስ ሰብሳቢ ተሾመለት። ይህንን ኃላፊነት የተረከቡት የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አደም ፋራህ ናቸው። አቶ አደም የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ ሆነው የሚሠሩ ከፍተኛ ባለሥልጣን ናቸው።ከዚህ በፊት ከሰኔ 2012 ዓ.ም እስከ መስከረም 2014 ዓ.ም ደግሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ፣ ከዚያ አስቀድሞ ደግሞ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነበሩ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሥራ አመራር ቦርድ በኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ሲመራ የቆየው በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ አላቸው የሚባሉት አቶ ግርማ ዋቄን በመተካት ነበር። Via DW @Addis_Mereja
Открыть в Telegramጋዜጠኛ ቤተልሄም ተስፋዬ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ትናንት በፌስቡክ ገጿ ላይ በአካባቢዋ ባለው የግንባታ ጫጫታ «በእሁዱ እንኳን ማረፍ መሞትም አይቻልም» ስትል የመጨረሻ ቃሏን አሰፍራ ነበር። በቤቷ መታጠቢያ ቤት ውስጥ በአጋጣሚ አዳልጧት በደረሰባት ድንገተኛ አደጋ፤ ጋዜጠኛ ቤተልሄም ተስፋዬ ይህችን ዓለም ለዘላለም ተሰናብታለች። 3 ጨቅላ ልጆቿን ትታ በድንገት ማለፏ በወዳጆቿ ዘንድ ከፍተኛ ሀዘን ፈጥሯል። የቀብር ሥነ-ሥርዓቷም ዛሬ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በኮተቤ ካራ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈጸማል። ለጋዜጠኛ ቤተልሔም ተስፋዬ ቤተሰቦች፣ ለሦስቱ ልጆቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿና ለሙያ አጋሮቿ ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን። ነፍስ ይማር! @Addis_Mereja
Открыть в Telegramቀጣይ የመንግስት ስልጠና ተረኞች የባንክ አመራር እንደሆነ ተጠቀሰ። መንግስት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በተለያየ ዙር ከፍተኛ የመንግስት ተሿሚዎችን ለስልጠና እየጠራ መሆኑ ይታወቃል።የፎርቹኑ ናሆም አየለ እንደዘገበው ደግሞ ቀጣይ ተረኞች የንግድ ባንኮች ፕሬዝደንቶች እና ምክትሎቻቸው ይሆናሉ። በአገሪቱ አንድ የመንግስትን ጨምሮ 32 የንግድ ባንኮች መኖራቸው ይታወሳል።አዲሱ የስልጠና እቅድ ከመንግስት ሹማምንት ባለፈ ወደ ግሉ ዘርፍ እየወረደ መሆኑን አመላካች ነው። ስልጠናው የመንግስት ቅድሚያ የፖሊስ አቅጣጫ የሚያሳይ ስለሚሆን የባንክ መሪዎች ስልጠናውን በመልካም ተመልክተውታል ነው የተባለው።ሰልጣኞች ከሁለት ሳምንት በኋላ በሁለት ዙር ወደ ስልጠናው እንደሚገቡ ነው የሚጠበቀው። @Addis_Mereja
Открыть в Telegramአሳዛኝ ዜና‼️ ዛሬ ህዳር 5/2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከደምበል አደባባይ ወደ ጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9፣ ከደምበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚያመራው መንገድ ላይ በሚገኘው ጋዜቦ አደባባይ አካባቢ ኅዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ገደማ በደረሰ የሥራ ላይ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋገጠ። አደጋው የደረሰው ሠራተኞቹ በግንባታ ላይ ባለ አንድ ሕንጻ ላይ የዕለት ሥራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ፣ ቆመውበት የነበረው ርብራብ በድንገት በመፍረሱ ከ12ኛ ፎቅ ላይ በመውደቃቸው ነው። በስፍራው የነበሩ ነዋሪዎችና መንገደኞች በድንገተኛው ክስተት ከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ውስጥ መውደቃቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ቶማስ እሸቴ ለኤኤምኤን በሰጡት መግለጫ፣ ሦስቱም ሠራተኞች ከሕንጻው ላይ በመውደቃቸው ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን አረጋግጠዋል። አያይዘውም የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች በጋራ በመሆን የአደጋውን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት ዝርዝር ሁኔታ ለማጣራት ምርመራ እያካሄዱ መሆኑን ጠቁመው፣ የምርመራው ውጤት ሲጠናቀቅ ተጨማሪ መረጃዎች ይፋ እንደሚደረጉ አስታውቀዋል። በደረሰው አሳዛኝ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን እንመኛለን።(AMN) @Addis_Mereja
Открыть в Telegramበትግራይ አፈሳን የሸሹ “800 ሺህ ወጣቶች” ወደሌሎች ኢትዮጵያ አካባቢዎች መሸሻቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ‼️ ትግራይ ውስጥ በነበረው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ምክንያት “እስከ 800 ሺህ" የሚደርሱ ወጣት የክልሉ ነዋሪዎች ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች መሸሻቸውን የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ይህንን የተናገሩት ሰሞነኛው የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች ግጭት በድጋሚ ከተነሳ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ትናንት አርብ ኅዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም. በክልሉ መዲና መቀለ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው። ኢታማዦር ሹሙ በቆይታቸው በክልሉ ከሚገኙ ከሠራዊት አዛዦች ጋር ግምገማ ማድረጋቸውን እንዲሁም “ወደ ሠራዊቱ አንዳንድ አሀዶች” በመሄድ ወታደሮችን ማግኘታቸውን ገልጸዋል። በመቀጠል ክልሉን የማስተዳደር ጊዜያዊ ኃላፊነትን ከተረከበው የባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር መወያየታቸውን አክለዋል። ከመቀለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በ2013 ዓ.ም. ከተነሳው ደም አፋሳሹ የሁለት ዓመት ጦርነት አንስቶ የነበሩ ክስተቶችን አንስተዋል። @Addis_Mereja
Открыть в Telegramማንቺስተር ዩናይትድ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን አዲሱ ዋና አሰልጣኙ አድርጎ ሾመ! ስምምነቱ ተጠናቋል! ማንቺስተር ዩናይትድ ለአዲሱ የአሰልጣኝነት ሹመት ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን መምረጡ ተረጋግጧል። ሁሉም የስምምነት ዝርዝሮች ተጠናቀው ፖቼቲኖ ረቡዕ ዕለት የቀረቡለትን ቅድመ ሁኔታዎች በሙሉ መቀበሉ ተገልጿል። የአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ለስምምነቱ አረንጓዴ መብራት ሰጥቷል። ይህም ፖቼቲኖ ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኝነት ሀላፊነቱ ተላቅቆ ወደ ኦልድ ትራፎርድ እንዲመጣ መንገዱን ከፍቷል። ከሉዊስ ቫን ሃል፣ ከዦዜ ሞሪንሆ፣ ከኤሪክ ቴን ሃግ እና ከሩቢን አሞሪም በኋላ ዩናይትድን ወደ ቀድሞ ክብሩ ለመመለስ አጥብቆ ይሻል። @Addis_Mereja
Открыть в Telegramበኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ግጭቱ መባባሱ ተገለጸ! በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ባድመ አካባቢ የጸጥታ ሁኔታው መባባሱን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ። በኢትዮጵያ በኩል የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች እና በኤርትራ በኩል የሚተኮሱ ከባድ መሣሪያዎች ወደ ሰፊ ወታደራዊ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ፈጥረዋል። በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎችም ሌሊቶችን በከፍተኛ ፍንዳታዎች እና ድብደባዎች እያሳለፉ መሆኑን ተናግረዋል። ሱቆችና ገበያዎች መዘጋታቸውን፣ እንዲሁም ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሉ አካባቢውን ለቀው እየተሰደዱ መሆናቸውን አስረድተዋል። Via AS @Addis_Mereja
Открыть в Telegramኢራን ወደ አሜሪካ የጦር መርከቦች ከ10 በላይ ሚሳኤሎችን ተኮሰች በደቡባዊ ኢራን ሆርሞዝጋን ግዛት ከምትገኘው ባንዳር አባስ ወደብ ተነስተው፣ በዓረብ ባሕር በሚንቀሳቀሱ የአሜሪካ የባሕር ኃይል የጦር መርከቦች ላይ ያነጣጠሩ ከ10 በላይ ፀረ-መርከብ ክሩዝ ሚሳኤሎች መተኮሳቸው ተነገረ። ይህንንም ተከትሎ በደቡባዊ የባሕር ዳርቻ በምትገኘው ሲሪክ ከተማ ከባድ ፍንዳታዎች መሰማታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ፍንዳታዎቹ አሜሪካ በሚሳኤል ማስወንጨፊያ ጣቢያዎች ላይ በወሰደችው የመከላከያ የአየር ጥቃት ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገምቷል። የኢራን መንግሥታዊ የዜና ወኪል (IRNA) በሲሪክ ከተማ ወታደራዊ ጥቃት መድረሱን ቢያረጋግጥም፣ የሚሳኤል ጥቃቱን ዝርዝር መረጃ፣ ዒላማዎችንና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ከይፋዊ ምንጮች ተጨማሪ ማረጋገጫ እየተጠበቀ ይገኛል። ከዓለም የነዳጅ አቅርቦት አንድ አምስተኛውን የሚያሸጋግረው ስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ በደረሱ ጥቃቶች ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት ነግሦበታል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በባሕር ወሽመጡ ላይ ያላትን ቁጥጥር አጠናክራ እንደምትቀጥልና ከኢራን ጋር አዲስ ስምምነት እንደማያስፈልጋት በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል። የአሜሪካ ባለሥልጣናትም በቀጣናው የተጣለውን የባሕር ላይ እገዳ ለማስፈጸምና ማዕቀብ የተጣለባቸውን ቁሳቁሶች ዝውውር ለመግታት የ“ታስክ ፎርስ አይረን ጌት” እንቅስቃሴ መጠናከሩን አጽንኦት ሰጥተዋል። ቀደም ሲል የተወሰዱ ወታደራዊ እርምጃዎችም በአሜሪካ የጦር መርከቦችና በንግድ መርከቦች ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን ለመከላከል የተደረጉ መሆናቸው ተገልጿል። (መናኸሪያ ሬዲዮ) @Addis_Mereja
Открыть в Telegram