📌 የተራራው ስብከት ትምህርት ክፍል አስራ ሁለት " ለቀደሙት። አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል። " ማቴ 5:21-22 @ACEBoleHermon
Открыть в TelegramПосты канала Apostolic church of Ethiopia, Bole Hermon Branch
Переслано из Apostolic church of Ethiopia, Bole Hermon Branch
ክፍል አስራ ሁለት @ACEBoleHermon
Открыть в Telegramየተወዳችሁ ቅዱሳን እንደተነጋገርነው ዛሬም ለአገልጋዮች ኮንፈረንስ ለአገልጋዮቻችን ጸሎት ቤት ተገኝተን ደግመን እንጸልያለን። " ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል። በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ።ጠላቶችንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፤ በእርሱ ግን ቅድስናዬ ያብባል።" መዝ 132:16-18 ተባረኩ!! @ACEBoleHermon
Открыть в Telegramቅዱሳን ሰላም ለናንተ ይሁን! " ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፥ ማስተዋልም ይጋርድሃል " ምሳሌ 2:11 ጥንቃቄውን ተጠቀሙበት!! መልዕክቱን ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ አሁኑኑ እንዲያስተላልፉ በትህትና እንጠይቃለን ይላል ማሳሰቢያው ሰዎች በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ጥሪ እየደረሳቸው ይገኛል፦ • +947 • +371 • +563 • +370 • +255 ወይም በእነዚህ መነሻዎች የሚጀምሩ ማንኛውም ቁጥሮች፦ +371፣ +375፣ +381 እነዚህ አካላት አንድ ጊዜ ብቻ ደውለው ይዘጋሉ። ተመልሰው ከደወሉላቸው በ3 ሰከንድ ውስጥ በስልክዎ ላይ ያለውን የሰው ዝርዝር (Contact list) መውሰድ ይችላሉ፤ እንዲሁም በስልክዎ ላይ የባንክ ወይም የክሬዲት ካርድ መረጃዎች ካሉ በቀላሉ ያገኟቸዋል። የሀገራት መለያ ኮዶች፦ • +375 - ቤላሩስ (Belarus) • +371 - ላቲቪያ (Latvia) • +381 - ሰርቢያ (Serbia) • +563 - ቫልፓራይሶ (Valparaiso) • +370 - ቪልኒየስ (Vilnius) • +255 - ታንዛኒያ (Tanzania) መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች፦ 1. ለእነዚህ ቁጥሮች አይመልሱ ወይም ተመልሰው አይደውሉ። 2. ማንኛውም ደዋይ በስልክዎ ላይ #90 ወይም #09 እንዲጫኑ ቢጠይቅዎት በፍጹም እንዳያደርጉት። ይህ ዘዴ የእርስዎን ሲም ካርድ (SIM card) ለመቆጣጠር፣ በእርስዎ ወጪ ስልክ ለመደወል እና እርስዎን ለወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የሚጠቀሙበት አዲስ ሴራ ነው። ይህ የጥሰት ሙከራ በአለም ዙሪያ እየሆነ ነው " ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።" 2 ጢሞቴዎስ 3:13 ጥንቃቄውን ተጠቀሙበት መልዕክቱ የተላለፈው:- ከሳይበር ወንጀል መከላከል ክፍል ነው አለማየሁ ፅ. (Alemayehu Ts) @ACEBoleHermon
Открыть в Telegramየተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ይብዛላችሁ። የወንድም ዳዊት ባለቤት የእህት መስከረም አባት ስላረፉ ስትመለስ እስክንደርሳት ባለችበት እንድታጽናኗት በዚህ ስልክ አግኟት ተባረኩ!! +251938095569 እህት መስከረም @ACEBoleHermon
Открыть в Telegramየተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ይብዛላችሁ ። የፊታችን እሁድ ህዳር 13,2019 ዓ.ም " ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤ " ሉቃስ 19:9 በሚል ርዕስ ቤታችንን ፣ ትዳራችንን ፣ ልጆቻችንን ፣ ኑሯችንን ፣ ላላገቡ ወጣቶችም ነጋቸውን የሚያድኑበትንና የምናድንበትን የምስጢር ቃል የትውልድ ሁሉ መጠጊያ ከሆነው ከሰራዊት ጌታ እንካፈላለን። "..እነሆ የጌታ ቀን ቀርቧአል!!!!!.... " ...አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ " ዘፍ 7፥1 ውዶች ሆይ..... ቀኑን ለዚህ ዋጅታችሁ ከመላው ቤተሰባችሁ ጋር በማለዳ ሁላችሁም እንድትገኙልን በክርስቶስ ፍቅር አደራ እንላለን። የመጨረሻው ዘመን መልዕክት ... መልዕክቱ ለሁሉ ይድረስ! ተባረኩ!!! @ACEBoleHermon
Открыть в Telegram📌 የተራራው ስብከት ክፍል 11 " .. ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።" ማቴዎስ 5:20 @ACEBoleHermon
Открыть в Telegramየተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ይብዛላችሁ ! የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አመታዊ የአገልጋዮች ሴሚናር ከህዳር 21-25 ቀን 2019 ዓ.ም በዋራ ቤቴል የኮንፍራንስ ማዕከል ላይ ይካሄዳል። በጉባኤው የሰበካና የቅርንጫፍ ሰበካ ኃላፊዎች፣ የንዑስ ሰበካ ተጠሪዎች፣ የአጥቢያ መጋቢዎችና በተለያየ ደረጃ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እያገለገሉ ያሉ የወንጌል አገልጋዮችና ባለቤቶቻቸው ከሃገር ውስጥና ከውጭ ይገኛሉ ። በዚህ ጉባኤ:- ".....የነብያት ጉባኤ ያገኙሃል .........የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።” 1ኛሳሙ 10፥6 በዚህ የህይወት ከፍታና ለውጥ በመታደስ አገልጋዮቻችን እንዲባረኩልንና ለበረከት እንዲሆኑልን ከህዳር 8 - 10 ,2019 ዓ/ም ለሦስት ቀን ለዚህ ጉባኤ ጾም ጸሎት እንዲደረግ ቤ/ን አሳስባለች። ቅዱሳን ሁላችሁ ጊዜ የምታገኙ በጸሎት ቤት ሌሎቻችን በያለንበት ሆነን አገልጋዮቻችንን እናስብ!!! " አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ። ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ። ጠላቶችንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፤ በእርሱ ግን ቅድስናዬ ያብባል። መዝ132፥15-18 ተባረኩ ! ለበረከትም ሁኑ!!! @ACEBoleHermon
Открыть в Telegramሰላም ለቅዱሳን በሙሉ! የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የኦዲዮቪዥዋልና ሥነ-ጽሑፍ ክፍል፤ በዘማሪ ሙሴ ሲሳይ የተዘጋጀውን "የነፍስ መልሕቅ" ቁጥር 1 የዝማሬ አልበም ሲያቀርብላችሁ በታላቅ ደስታ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ለራሱ ክብር እና ለቅዱሳኑ መታነጽ የሚሆን የዝማሬ ጸጋን ጨምሮ በተለያዩ ስጦታዎች ቤተክርስቲያኑን እየባረከ ስላለ እጅግ ደስ ይለናል። ይህንን አድካሚ የዝማሬ አልበም ሥራ ከጅማሮው አንስቶ በታላቅ መሥዋዕትነት ያዘጋጀውን ወንድም ሙሴ ሲሳይና በተለያዩ መንገዶች የተሳተፉትን ሁሉ የቤተክርስቲያን አምላክ ኢየሱስ በማያልቀው በረከት እንዲባርካቸው ጸሎታችንና ምኞታችን ነው። አልበሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ በ Apostolic Songs ላይ ዝግጁ የሚሆን ሲሆን ሁሉም ተጠቃሚዎቻችን በመተግበሪያው ውስጥ ባሉት የክፍያ አማራጮች በመጠቀም ዝማሬዎቹን ማውረድ እንደምትችሉ እንገልፃለን። በዚሁ አጋጣሚ በመተግበሪያው ላይ የተካተቱትን ተጨማሪ የክፍያ አማራጮችን ለማየት Apostolic Songs መተግበሪያን ወደ አዲሱ ስሪት ማዘመናችሁን [Update] ማድረጋችሁን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን። የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ሥነ-ጽሑፍ ክፍል ኅዳር 2019 ዓ.ም. @ACEBoleHermon
Открыть в Telegram📌 የተራራው ስብከት ትምህርት ክፍል 10/2 " እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም.... መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።" ማቴ 5:13-16 @ACEBoleHermon
Открыть в Telegram📌 የተራራው ትምህርት ክፍል 10/1 " እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። " ማቴ 5:13-14 @ACEBoleHermon
Открыть в Telegram📌 የተወደዳችሁ ውድ ቅዱሳን ማንም የማይቀርበት የምክክር ጉባኤ ፊታችን እሁድ ጥቅምት 15, 2019 ዓ/ም ይኖረናል። ከትልቅ አደራ ጋር ወሳኝ የሆነ ነገር እንመክራለን። መልዕክቱ ለሁሉ እንዲተላለፍ እንተጋገዝ ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ።
Открыть в Telegramአዲስ ነገር ከኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል! የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በምስራቅ አያት አጥቢያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የተዘጋጀውንና “የምስጋና ቅኝት” የተሰኘ በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ 15 ቅንብሮችን የያዘ አልበም ሲያቀርብላችሁ በታላቅ ደስታ ነው። ይህንን አልበም ያዘጋጁትንና በተለያየ መንገድ የተሳተፉትን ሁሉ የቤተክርስቲያን አምላክ ኢየሱስ በማያልቀው በረከት እንዲባርክ ጸሎታችንም ምኞታችንም ነው። አልበሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ በ Apostolic Songs ላይ ዝግጁ የሚሆን ሲሆን ሁሉም ተጠቃሚዎቻችን በመተግበሪው ውስጥ ባሉት የክፍያ አማራጮች በመጠቀም ቅንብሮቹን ማውረድ እንደምትችሉ እንገልፃለን። በዚሁ አጋጣሚ በመተግበሪያው ላይ የተካተቱትን ተጨማሪ የክፍያ አማራጮችን ለማየት Apostolic Songs መተግበሪያን ወደ አዲሱ ስሪት ማዘመናችሁን [Update] ማድረጋችሁን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን። የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል ጥቅምት 2019 ዓ.ም @ACEBoleHermon
Открыть в Telegramየተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ይብዛላችሁ። ዘወትር አርብ በሚኖረን የአዳር ጸሎት ዘወትር በመስዋዕት ኪዳን የምትቆሙ የምትገኙ ቅዱሳን እጅግ ከልቤ እባርካችኋለሁ ቤተክርስቲያንም ትባርካችኋለች። ነገ አርብ የእናቶች ኮንፈረንስ የሚጀምርበት ቀን ስለሆነ ሳምንት እንጂ ነገ አዳር ጸሎት አይኖረንም። ተነጋገሩ @ACEBoleHermon
Открыть в Telegram