Кабинет

Посты канала Abu Umer Ibnu Sadik

сначала новые

#6946Фото

~ መልእክት ለሙነወሪዮች¡ • √ ለነዚያ ለነሲሓዎች ጠበቃ ቆመው ከርመው፣ የጠበቃነት መንገድ ጨርሶ ሲዘጋባቸውና፣ ከነሱ የነበሩ ሰዎችም ሲነቁባቸው፣ ከጥፋታቸው ተውበት ማድረግ ሲገባቸው እኛ እንኮፈስባቸዋለን ብለው ለሰጉትና "ሳይቀድሙኝ ልቅደም" አይነት ጉዞ ለሚጓዙት የሙነወሩ መንጋዎች አድርሱልኝ። 1.ኛ አጥፊዎችን ሸሪዓ በሚያስፈርደው መልኩ ."على ما تقتضيه الشريعة" ማረም፣ የማረም አቅም በለው አካል ላይ ሸሪዓዊ ግዴታ ነው። የነሲሓዎችንም የሆነ የሌላሎችን ስህተት የማረም አቅም ካላችሁ እረሙ። እንደው "እንዲህ ቢሉኝ ምን መልስ እሰጣለሁ? እንዴት እንዳይመጡብኝ ማድረግ እችላለሁ?" በሚል ስጋት አትዋጡ። አይዟችሁ ምን አትገደዱ፤ አትቸገሩ። የሚኮፈስባችሁ የለምና። 2.ኛ ስለ ባለ ሴንተሮቹ በተገቢው መልስ የሰጡት የኛ ዉ¡ስታዞች ናቸው ማለት እራስህ ባስቀመጥከው መርህ መኮፈስ አይደለም እንዴ!? ለምን ትኮፈሳለህ ታዲያ? ሌላ ደሞ "ያኔ አብዘሃኞቻችሁ የኢኽዋንና የዚሁ መንጋ አጋፋሪዎች ነበራችሁ።" ስትል ማስረጃ ማቆም ትችላለህ? ከቻልክ ማስረጃ አቅርብ። ማቅረብ እንደማትችል ግን እኔ ብቻ ሳይሆን አንተም ታውቃለህ። = ስማቸውን የጠራሃቸውም ይሁን ሌላም አካል፤ በግዜው ለማወያየት ይጥሩ ነበር ስትል የጣሩት በባጢል እንዲደምሯቸው ነበረ? ነው ጉዳዩን በሸሪዓ እይታ ተወያይቶ ለመፍታት? ከቻልክ ይህንንም በማስረጃ መልስ ስጥ። በትልቁ ልታሰምርበት የሚገባው ደሞ ጅምርት በባለ ሴንተሮች ላይ ያደረጉት ረድ ስህተት እንደነበረና ረድ ያደረጉትም መስሏቸው እንደነበረ ኡስታዝህ¡ ኬሚሴው አስረግጦ ተናግሯል። መኮፈስ አምሮህ ልኮፈስ ብትል እንኳ መኮፈሻ የለህም። 3.ኛ እኔ የምለው "ሐታ እነዚህ ሰዎች ሙብተዲዖች ናቸው የሚል ድምዳሜ ላይ ብንደርስ እንኳ" ስትል! ከናንተ እነሱ ሙብተዲዕ ናቸው ብሎ የመደምደም አቅም "أهلية" ያለው አለ? ጀርሕና ተዕዲል ኢጅቲሃዲይ ነው ትሉ የለ? ከናንተ የተኛው የ Google ልጅ / የልጅ ልጅ ነው የኢጅቲሃድ ደረጃ የደረሰው? ኣ!? ጀርሕና ተዕዲል ኢጅቲሃዲይ ነው ብትል፣ አይደለምም ብትል ከናንተ ጀርሕ ተዖዲል ላይ የመሳተፍ አቅም ያለው የለም። ይሄንን ልትዘነጋና ልትረሳ አትሞክር። 4.ኛ እኛ "ለተሚዮች የምትሉን ሰዎች" ዲን ላይ የትኛውን ቢድዓ ነው ያመጣነው? ሸይኽ ዐብዲል-ሐሚድም ሆኑ ሌሎቹ በራሳቸው ጠንስሰው ያመጡት መርህ የቱ ነው? ንግግርህን በማስረጃ ማጠናከር ከቻልክ ሞክር እንጠብቅሃለን። 5.ኛ በተከሰተው ክስተት ሰርጎ ገብ "دخيل" ከሆንክ፣ በማታቀው ነገር ገብተህ ከመፃፍና ከመዘላበድ በፊት ከሁሉም በስተኩል ያለውን ተጨባጭ በተገቢው አጥና። ኺላፉ የሰፋው ከግዜ ወደ ግዜ የነ ዐሊይ አል-ሐለቢይን አንና የሌሎችንም ከንቱ ብዥታ ስትጋቱ ነው። ካለወቅክ አጥና። — በመጨረሻም ለሱና ወንድሞቼ የማስተላልፈው፤ እነኚህ አይናቸው ግንባር የሆነባቸው ሰዎች፣ እውነታውን ለመደባበቅ ቢሞክሩም እኛ ይሄንን የተምታታ አስተሳሰባቸውን በመጡበት እንመልስ። በሚጓዙት ዙሪያ ጥምጥሞሽ ምክንያት ለነሱ ሐቅ መቀበልን ከመመኘት ወደ ኋላ አንበል። የፅናትና የፍፁምነት ካርድ የተቀበለ ማንም የለም። አ'ሏህን ፅናትና ሐቅ መገጠምን እንጠይቅ። = ሁሉም ስህተቱን አርሞ፣ በሱና እና በሰለፊያ አንድ ሁኖ፣ የተውሒድን ደዕዋ በትክክለኛው አንድነት ወደፊት ማስቀጠል የሁል ግዜ ምኞታችን ይሁን። በሐቅ ላይ አንድ ሁነን ተውሒድና ሱናን ለማንገስ፣ ሺርክና ቢድዓን ለማርከስ በተገቢው ብንለፋ ምን ያህል ኡማውን ማንቃት እንችል እንደነበር አስባችሁታል!? ለማንኛውም እኛ ለሁሉም ከስህተት መመለስን እንመኛለን። ነገርግን በፍፁም ሙዳሀና አናደርግም። ."والمعصوم من عصمه الله" || የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abu_Hessan https://t.me/Abu_Hessan

Открыть в Telegram
Просмотры636+28%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#6945Превью ссылки

🕋🕋🕋አስደሳች ሰበር ዜና🕋🕋🕋        በታላቅ ጉጉት በሚጠበቀው ሁሉን አቀፍ የዳእዋ ፕሮግራም ላይ የሚቀርቡ 🖍አሊሞች 🖌መሻኢኾች 🖋ኡስታዞችና 🖊ዳኢዎች ዝርዝር ይፋ ሆነ በአካልና በኦንላይን የሚካሄደው የዚህ ብርቅዬ ፕሮግራም እንቁ ተሳታፊዎች 🪑🪑በአካል የሚገኙ 1⃣ ሸይኽ  አቡዘር ሐሰን... ከኮምቦልቻ 2⃣ ሸይኽ አብዱልሀሚድ... ከለተሞ 3⃣ ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት... ከሀራ 4⃣ ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ...  ከሀዋሳ 5⃣ ኡስታዝ ዐብዱልሀሚድ ... ከሀዋሳ 6⃣ ወንድም አቡ ዒምራን ... ከአድስ አበባ 📞☎️በ ONLINE  የሚሳተፉ 1⃣ ሸይኽ ሐሰን ገላው ... ከባህር ዳር 2⃣ ሸይኽ ዶክተር ሁሴን … ከአዲስ አበባ 3⃣ ሸይኽ ጡሃ ኸድር.... ከአዲስ አበባ 4⃣ ሸይኽ ሙሀመድ ጀማል.... ከኮምቦልቻ 5⃣ ሸይኽ ሁሴን ከረም... ከሀራ 6⃣ ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ.... ከባህር ዳር 7⃣ ሸይኽ መህቡብ... ከሳንኩራ 8⃣ ሸይኽ ሙባረክ... ከወልቂጤ 9⃣ ሸይኽ ኢስሚዒል ዘይኑ… ከተንታ 1⃣0⃣ ሸይኽ ሁሴን አባስ ...ከወርቄ 1⃣1⃣ ሸይኽ ሙሀመድ ሲራጅ ...ከሀሮ 1⃣2⃣ ሸይኽ ያሲን ሙሀመድ ... ከጎብየ 1⃣3⃣ ሸይኽ ሁሰይን አደም ... ከጎብዬ 1⃣4⃣ ሸይኽ አህመድ ወረታ...ከአዲስ አበባ 1⃣5⃣ ኡስታዝ ዐብዱናሲር  ...   ከመዲና 1⃣6⃣ ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን... ከአዲስ አበባ 1⃣7⃣ ኡስታዝ አብዱልቃድር ...  ከአዳማ 1⃣8⃣ ኡስታዝ በህረዲን ሻፊ ...  ከሀላባ 1⃣9⃣ ኡሰታዝ ታጁዲን ...ከወራቤ 2⃣0⃣ ኡስታዝ  ኢዘዲን... ከሁልባረግ 2⃣1⃣ኡስታዝ አብራር አወል  ...ከአድስ አበባ 2⃣2⃣ኡስታዝ ሀሰን ሙሀመድ ...   ከወለጋ 2⃣3⃣ኡስታዝ ሰዕድ  ...  ከባህር ዳር 2⃣4⃣ኡስታዝ ኸዲር   ...  ከሀላባ 2⃣5⃣ ሸምሱ ሷቢር   ... ከቡታጂራ 2⃣6⃣ ኡስታዝ ሙሀመድአሚን... ከሸዋሮቢት 2⃣7⃣ ኡስታዝ ሰልማን... ከመዲና 2⃣8⃣ ኡስታዝ ሰይፈዲን  ...ከወላይታ 2⃣9⃣ኡስታዝ ኪርማኒ ...   ከዱና በተጨማሪም       ↪️ወንድም ኢብኑ ሺፋ       ↪️ወንድም ኢብኑ ሙዘይን  እና ሌሎችም የቻናል ባለቤቶች የሚሳተፉ ይሆናል። የፕሮግራሙ መሪዎች ✅ኡስታዝ ባህሩ ተካ.... ከአዲስ አበባ ✅ኡስታዝ አብዱረህማን ሰኢድ....  ከመርሳ ✅ ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሐሰን... ከሀዋሳ ✅ኡስታዝ አቡበክር ዩሱፍ … ከባህር ዳር ✅ወንድም አቡ ዒምራን   ...  ከአድስ አበባ ✅ወንድም ጀማል ...  ከኢማራት                           ​📍 ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ቀንና ቦታ፦ ◦ ​📅 ​ቀን፦ ታህሳስ 3 እና 4 2019 ዓ.ል ◦ ​🏢 ​ቦታ፦          በአካል ለሚታደሙ👉 በሀዋሳ ከተማ ዳቶ ዑመሩል ፋሩቅ መድረሳ       ቀጥታ ስርጭት👉የሀዋሳ ሰለፊዮች የመስጅድ ቦታ ግዢ ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ ​📌 ልዩ ማሳሰቢያ፦ በዕለቱ ለመስጂድ ቦታ ግዢ የሚውል የኒያ (የገቢ ማሰባሰቢያ) ፕሮግራም ይኖራል። ፕሮግራሙ የሚተላለፍባቸው ቻናሎች 👉ቴሌግራም/telegram https://t.me/hawassajemea 👉IMO/ኢሞ👇 https://s.imoim.net/QHwuMR?from=copy_link የቻናልና የግሩፕ ባለቤቶች ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ በኢሞም በቴሌግራምም Forward/Share  በማድረግና ሀሳቡን በማሰራጨት  🔗ከጎናችን ሁኑ ስንል በአሏህ ስም እንጠንቃለን። አዘጋጅ፦የሀዋሳ ሰለፊዮች ጀመዓ ሰለፍይነት ያብባል፤           ተውሂድ  ይነግሳል። ቦታውም ይገዛ፤       መስጅዱም ይገነባል። ሼር- ሼር ይደረግ!

Открыть в Telegram
Просмотры502+1%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#6944Текст

ዐቂዳ ማለት ቃል ብቻ አይደለችም፤ የልብ እምነት ነዉ። አላህን እወዳለሁ ማለት ቀላል ነው። ነገር ግን ይህን ፍቅር በተውሒድ፣ በመታዘዝ እና ከሺርክ በመራቅ ማሳየት ነው እውነተኛው እምነት። አላህ سبحانه وتعالى ይላል፦ ﴿قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ ۝ لَا شَرِيكَ لَهُ﴾ “በላቸው፦ ሰላቴ፣ መስዋዕቴ፣ ሕይወቴና ሞቴ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ብቻ ነው። ለእርሱም አጋር የለውም።” 📖 ሱረቱል-አንዓም 6፥162–163 ይህ ነው የሰለፎች መንገድ፦ በአላህ ብቻ መተማመን፣ ዒባዳን ለአላህ ብቻ ማድረግ፣ ሺርክን መጠንቀቅ፣ ቁርአንንና ሱናን መከተል፣ የሶሐቦችንም መረዳት መንገድ ማክበር። ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «عَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ الْمَهْدِيِّينَ مِنْ بَعْدِي» “ሱናዬንና ከእኔ በኋላ ያሉትን መሪዎች የተመሩትን ሱና አጥብቃችሁ ያዙ።” 📚 ሱነን አቢ ዳውድ 4607፣ አት-ቲርሚዚ 2676 🖊ዐቂዳ በትክክል ከተማርን፣ ምን እንደምናመልክ፣ ለማን እንደምናመልክ እና ለምን እንደምናመልክ እናውቃለን። የሰለፎች መንገድ ሰውን ወደ ሰው አያስጠጋም፤ ወደ አላህ ያቀርበዋል። አሏህ ቀጥተኛዉን የሰለፎችን መንገድ የምንከተል ያድርገን

Открыть в Telegram
Просмотры457−8%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#6939Видео
Просмотры527+6%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#6937Фото
Просмотры544+10%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#6935Фото
Просмотры602+21%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#6934Текст
Просмотры598+21%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#6933Текст
Просмотры627+26%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#6932Текст
Просмотры565+14%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—