Кабинет

Посты канала ዶ/ር ምህረት ደበበ እና ዶ/ር እዮብ ማሞ

сначала новые

#2287Текст

“ሰው “ መሆን ወጥ ያለ ቅመም ና ጨው ጣዕም እንደሌለው ሁሉ ደግነት የሌለበት ህይወት ባዶ ነው። ሰለሆነም ዓለማችንን ያቆሟት ጥቂት ጥሩ መአዛ ያላቸው። እንደ ጨው ነገርን የሚያጣፍጡና ከመበላሸት በሚጠብቁ ሰዎች ነው። በእርግጥ አለማችን ቀጥ ብላ ያለችው። ብዙ የወደቁ ሰዎችም ስላሉ ነው። ለዛ ነው ዓለምና ሰው በታሪክና በጊዜ ውስጥ ነው ያሉት የሚባለው። እንደሚታወቀው አንድ ሰው እራሱን የሚረዳው ሌላውን ሰው ሲረዳ ሳይሆን በቅድሚያ ሲረዳ ነው። እኛም ሆንን ሌላው ጥሩ መረዳት የሚያገኘው እኛ ስለራሳችንና ስለሌላው ያለው መረዳት በሌላው ውስጥ መሆኑን ስንገነዘብ ብቻ ነው። ኤማኑል ሌቪነስ የተባለው ስመ ገናና ፍላስፍ የቤተሰቦቹን ታሪክ አስታውሶ። ሌላይኛው ፊት የሚል ሀሳብ አለው ( The face of the other) ። እኔ መኖሬን የማውቀው ጎረቤቴ ቡና ሲጠራኝ ነው። እኔ መኖሬን የማውቀው የአንተን መልክ ሳይ ነው። ይላል ይኸ ማለት ደግሞ አንተን ሌላ ሰው እንዲገድልኸ ወይም ክፉ እንዲያደርግብኸ እንደማትወደው ሁሉ ሌላውም ፊት ስትመለከት እንደዛው ነው የሚፈልገው። አንተ መሞት እንደማትፈልገው ሁሉ ሌላውም ፊት የሚልኸ አንድ ነገር ነው እሱም አትግደለኝ። ሰው መሆን !!! ሰው ሀሳቡን ማጥራት ይችላል። ሰው ምርጫውን ማስተካከል ይችላል። ሰው ሀሳብ መምረጥ ይችላል። በምርጫ መምረጥ ያለብንን መምረጥ እንችላለን ይገባልም ነገር ግን የምርጫ ውጤት አይቀየርም። ምክንያቱም የሰው የመምረጥ አቅም ብቻ ሳይሆን ሰው መሆን በራሱ ግብ ነው። እንጂ ለሆነ ግብ means አይደሉም። ሰው እረቂቅ ፍጥረት ነው። ታላቁ አሰላሳይ አርስጣጢለስ Aristotle, things are contained of both essential and accidental qualities እንደሚለው essential qualityችን ስዎች ነን። በAccidental quality ግን እንለያያለን። ሰውነታችን essential ነው። አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሪም ብትሆን ሰው ነኸ። ረጅም ወይም አጭር፣ ወፍራም፣ ቀጭን፣ አማራ፣ኦሮሞ accidental ነው። ሰው መሆን ነው essenceu። ሰው መሆን ክብር ነው። ሰው መሆን መመረጥ ነው። ሰው መሆን ፀጋ ነው። ሰው መሆን ምስጢር ነው። ሰወ መሆን መራቀቅ ነው። ሰው መሆን ከራስ፣ ከቤተሰብ፣ ከአካባቢ፣ ከክልል፣ ከሀገር አና ከአህጉር አልፎ አለማቀፍዊነት ነው። ሰው መሆን ከቋንቋና ከነገድ ማለፍ ነው። ሰው መሆን ከገደብ በላይ እንደ ንስር ከፍ ብሎ መብረር ነው። ሰው መሆን ለሌላው ግድ መሰኘኘት ለሌላው መቆረስ ነው። ሰው መሆን ልዮነትንና አንድነትን ማጣመር ነው። ሰውነት ሰውነትን መገንዘብ ነው። ሰው መሆን መታደል ነው። ሰው መሆን ሰው መሆን ነው። ሰው መሆን የፍጣሪ ፎቶ መሆን ነው። ዮናስ ዘውዴ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры294−70%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#2286Текст

ጠዋት ስትነሱ! መጀመሪያ የምታስቡት ሃሳብ ምን እንደሆነ በሚገባ ተመልከቱትና ያላችሁበትን የስሜት ሁኔታ ይነግራችኋል፡፡ •  በእለቱ የምታከናውኗቸው ተግባሮቻችሁ ከባድ እንደሆኑ ካሰባችሁ እቅድ የማውጣት ክህሎት ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ትናንት ስሜታችሁ ላይ አጉል ተጽእኖ ስለነበረው ሰው ካሰባችሁና ከተረበሻችሁ የሰዎችን ሁኔታ አያያዝ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ምንም የምትሰሩት ስራ እንደሌላችሁ ካሰባችሁ የፈጠራ እና አዳዲስ ነገር የመጀመር አቅማችሁ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ሁኔታችሁ ሊለወጥ እንደማይችል የተስፋ መቁረጥ ሃሳብ ካሰባችሁ የሰዎችን የምክር እገዛ የመጠየቅና የመጠቀም ሁኔታ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ ሃሳቦቻችሁንና እነሱ የወለዷቸው ስሜቶቻችሁን በፍጹም ችላ አትበሏቸው፡፡ ተገቢውን ምላሽ ስጧቸው፡፡ ስላላችሁበት ሁኔታ ሰዎችን መውቀስ አቁሙና አንድ ነገር አድርጉ፡፡ ያላችሁበትን ሁኔታ ለመርሳት ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በመዋል አትደበቁ፡፡ ቀና በሉና ራሳችሁ ላይ ስሩ! join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры726−27%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#2284Текст

#አልፈልግምን_ፈልገው! ለአንድ ነገር ዋጋ ለመስጠት፣ ያ ነገር ያልሆነውን ነገር አለመቀበል አለብን፡፡ ለ X ዋጋ ለመስጠት X ያልሆነውን ውድቅ ማድረግ አለብን፡፡ ያ ‘አለመቀበል’ እሴቶቻችንንና ማንነታችንን ለመጠበቅ ተፈጥሯዊ እና አስፈላጊ አካል ነው። እኛ የምንገለፀው ላንቀበለው በምንመርጠው ነገር በመሆኑ፣ በራሳችን ውድቅ እንዳንሆን በመፍራት ምንም ነገር ‘አንፈልግም’ የማንል ከሆነ በመሰረቱ ምንም አይነት ማንነት የለንም ማለት ነው። በማንኛውም ዋጋ በመክፈል አለመፈለግን ውድቅ የማድረግ፣ ክርክርና ግጭትን የማስወገድ፣ እንዲሁም እና ሁሉንም ነገር ለማስማማት እና ህብር ለመፍጠር ሁሉንም ነገር በእኩልነት ለመቀበል የመሞከር ፍላጎት ጥልቅ እና ስውር ራስን ከፍ አድርጎ የማየት መንገድ ነው። ራሳቸውን ከፍ አድርገው የሚያዩ ሰዎች፣ ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት ሊሰማቸው እንደሚገባ ስለሚሰማቸው፣ እነሱንም ሆነ ሌላ ሰውን ሊያሳዝን ይችላል ብለው ስለሚያስቡ ማንኛውንም ነገር ‘አልፈልግም’ ከማለት ይቆጠባሉ። የትኛውንም ነገር ‘አልፈልግም’ ማለት ባለመቻላቸው ምክንያት ዋጋ የሌለውና ለራስ ብቻ ትኩረት የሚሰጥ በፍላጎት የሚገፋ ኑሮ ይኖራሉ፡፡ ግድ የሚሰጣቸው የማይቀረውን የህይወታቸውን ውድቀት በመሸሽና ስቃይን እንዳባረሩ በማስመሰል ለጥቂት ጊዜ ከፍታ ላይ መቆየት ነው፡፡ አለመፈለግ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ የሕይወት ክህሎት ነው፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 120+13%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#2283Текст

#አንዱ_ለአንዱ_መኖር_የተፈጥሮ_ህግ_ነው! "ተፈጥሮን በተረዳን ቁጥር አዕምሮአችን የመፍጠር አቅሙ እያደገ ይመጣል። ዓለም ላይ ያለው እያንዳንዱ የፈጠራ ስራ ውጤት ተፈጥሮን በጥልቀት ከመረዳት የመነጨ ነው። ተፈጥሮን በጥልቀት ከተረዳን በደንብ ማየት እንችላለን። ተፈጥሮን በሰከነ መንፈስ የተረዳ ሰው የፈጠራ ችሎታውን ከማሳደግ በተጨማሪ ለሌሎች ሰዎች ሕይወት የብርሃን ምንጭ ለመሆን ይጥራል፤ ሁሌም ቢሆን ሰጭ እንጂ ቀማኛ አይሆንም። ልብ በሉ ወንዞች የራሳቸውን ውኃ አይጠጡም፤ እጽዋት የራሳቸውን ንፁህ አየርን አይስቡም፤ ፀሐይና ጨረቃም ቢሆን ለራሳቸው ብርሃን አይሰጡም፤ ውብ አበባዎችም መልካም መዓዛቸውን ለራሳቸው አያሰራጩም። አንዱ ለአንዱ መኖር የተፈጥሮ ህግ ነው። እኛም ወደዚህ ምድር የመጣነው አንዳችን ለአንዳችን ለመኖር እንጅ አንዳችን ለሌላችን የስጋት ምንጭ ወይም ወጥመድ ለመሆን እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል።” “እውቀት እና ጥበብ ተፈጥሮን ከመረዳት ይመነጫሉ። ተፈጥሮን በትክክል የምንወድ ከሆነ በሁሉም ቦታ ላይ ውበት እናያለን፤ እውቀትና ጥበብም እንደ ቢራቢሮ በእየሄድንበት ሁሉ እንቀስማለን። ተፈጥሮን በማወቅ ራሳችንን እናገኛለን። ተፈጥሮ ለሚያዳምጣት ልዩ ቅላፄ ያለው ዜማ አላት። በጥቅሉ የሕይወት ግባችን እኛነታችን ከተፈጥሮ ጋር እንዲዛመድ በማድረግ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።" #ስሙር መጽሐፍ የተቀነጨበ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 420+43%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#2282Текст

#ከዚህ_ድንቅ_ሰው_ተማር! ⚽️ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ እጅግ ድሀ ከሆኑ ቤተሰቦች ተወለደ። የልጅነት ህይወቱ ጉስቁልና የበዛበት ነበር። አባቱ አትክልተኛ ሲሆን፤ የመጠጣት ልማድ ነበረበት። በቂ ገቢ ለቤተሰቡ ማስገኘት የማይችል ነበር። በዚህ የተነሳ ህይወቱን በጉበት ህመም አጥቷል። እናቱ ምግብ አብሳይና የጽዳት ሰራተኛ ነበረች። ያገኘችውን ለቤተሰቧ አብቃቅታ ትጠቀም ነበር። ሮናልዶ “እኔ የተነሳሁት ከምንም ነው። እጅግ ድሃ ከሆነ ቤተሰብ... በዙሪያዬ እንደነበሩት ልጆች አሻንጉሊቶች አልነበሩኝም። የልደትም ሆነ የገና ስጦታ አላገኝም ነበር። ከወንድሜ እና ከሁለት እህቶቼ ጋር ጠባብ ክፍል ውስጥ ነበር የምተኛው።”  ይላል። ⚽️ በዚህ ጊዜ ከቤቱ እየወጣ ከአካባቢው ልጆች ጋር ኳስ በመጫወት ችግሮቹን ወደኋላ በመተው ይጋፈጣል። ትኩረቱን እራሱን ምርጥ እና ተፈላጊ በማድረግ ላይ ያሳርፋል። በዚህም ሁሌም ፊቱ ላይ ፈገግታ የማይታጣበት ተስፈኛ መሆን ቻለ። ሮናልዶ በዚህ ጊዜ ነበር አባቱ በዝቅተኛ ክፍያ አትክልተኝነት ይሰራበት ለነበረው አንደሪና ቡድን መጫወት የጀመረው። ሮናልዶ በዚያ ለጋ እድሜው ችሎታው በግልጽ የሚታይ ቆንጆ ተከፋይ መሆን ጀመረ። ⚽️ በአስራ አንድ አመቱ የዲ ፖርቹጋልን ቀልብ ማረፊያ ሆነ። ባደገ ቁጥር ሁሉም ሰው አቅም እንዳለው አወቀ። ነገር ግን ትንሽ እና በጣም ቀጫጫ በመሆኑ ተፈላጊነቱን ፈተና ውስጥ ከተተው። ሮናልዶም ቀጫጫ መባሉን አይወደውም ነበር። በዚህም ሮናልዱ በአስራ አንድ አመቱ ሰውነቱን ለማሳደግ እና አቅሙን ለመጨማር ከማንም በላይ ጠንክሮ መስራት ጀመረ። በዚህም ሰውነቱን በቶሎ መቀየር ሆነለት። በትምህርት ቤት ውስጥ ከተማሪዎች ሁሉ የታወቀና የሚደነቅ ሆነ። በመምህራኖቹ ፊት ግን ደደብ የሚባል ነበር። ከትምህርት ቤትም እንዲባረር ተደርጓል። ⚽️ ከሚኖርበት ርቆ ሊዝበን የእስፖርት ትምህርት ቤት ሲገባ፤ የህይወቱ ትልቅ ፈተና ሆኖበታል። “እግር ኳስ ሁሉን ነገር ሰጠኝ። ነገር ግን ከቤቴ እንድርቅ አስገድዶኛል” ይላል ሮናልዶ። በ15 አመቱ በሊዝበት መጫወት ሲጀምር ነገሮች ከጅምራቸው ያበቃላቸው መስለው ነበር። ጤናው በልብ ህመም ታወከ። እንዳለመታደል ሆኖ እግር ኳስ እየተሯሯጠ ሊጫወት ይቅርና ለመኖርም መተንፈስ የሚከብደው ሆነ። ⚽️ ከዚያም ቀዶ ጥገና ሲደረግለት ትጉና ተስፈኛ የነበረው ሮናልዶ  ዳግም ጤናውን ሙሉ ለሙሉ ማግኘት ቻለ። ከዚያም እንደለመደው አላማውን ለማሳካት ከማንም በላይ ጥረቱን አጠናክሮ ቀጠለ። በፈረንጆቹ 2003 በ 15 ሚልዮን ዶላር ለማንቺስተር ዩናይትድ ቡድን ኮንትራት ፈረመ። ከዚያም የአለማችን ምርጥ ተጫዋች ለመሆን ራሱን ምቹ ማድረጉ ላይ አመነበት። አሰልጣኝ አሌክስ ፈርጉሰንም ሰባት ቁጥር ማልያን በመተማመን አለበሰው። በ 2009 ሮናልዶ ወደ ሪያል ማድሪድ ቡድን በአለማችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በ 94 ሚልዮን ዩሮ ተዘዋወረ። ከዚም በአመቱ በ 100 ሚልዮን ዩሮ ወደ ጁቤንትስ አቀና።  ይህም ከሰላሳ አመት በላይ በዚህ ልክ የተከፈለው የመጀመሪያው ታሪካዊ እግር ኳስ ተጫዋች ለመሆን በቃ። በዚህ ሁሉ መሃል ሮናልዶ ብዙ ስኬቶችን የራሱ ማድረግ ችሏል። ⚽️ እስካሁን ባለው እምነት ሁሌም ጠንክሮ በመስራት እንደሚያምን አለም ያወቀለት ተቀባይነቱ ነው። “እኔ ሁሌም በደጋፊዎች ፊት የሚደነቅና የሚወደድ ለመሆን አይደለም ጥረቴ፤ ልፋቴ የራሴን እርካታ ስለሚያስገኝልኝ-ም ነው።” ይላል ሮናልዶ። ከማንም ወደ (?) ☑️ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ያልተጋፈጠው የችግር ናዳ የለም። አቅሙን በማውራት ሳይሆን በማድረግ ስላሳየ፤ አለም ቁማ የምታጨበጭብለት ታታሪ ለመሆን በቅቷል። አንተስ ጥረትህን አሁን ትጀምረዋለህ ወይስ መቼም የማይመጣልህን ምቹ ጊዜ እየተጠባበክ በቅዠት ራስህን ታዳክማለህ? join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 410+42%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#2281Текст

አንተ ማግኔት ነህ የአዕምሮ አይኖችህን ከከፈትክ እና በውስጥህ ያለውን ሀይል መጠቀም ከቻልክ ወሰን የለሽ ሀብቶች በዙሪያህ እንዳሉ ልታይ ትችላለህ። ህይወትህን በደስታ ለመኖር የሚያስፈልግህን ሁሉ የያዘው የወርቅ ማዕድን በአንተ ውስጥ ነው። ብዙዎች አንቀላፍተዋል ምክንያቱም በውስጣቸው ስላለህ እምቅ ሀይል ስለማያውቁ ነው።  የማግኔትነት ባሕሪ ያለው ብረት የክብደቱ አሥራ ሁለት አጥፍ ያህል ያነሳል። ይህንኑ ብረት ማግኔታማ ባሕሪውን ብታሳጣው ላባ እንኳ አያነሳም። ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ። በራስ በመተማመን ስሜት የተሞሉ ማግኔቲዝድ ሰዎች እና በፍርሃትና በጥርጣሬ የተሞሉ ምንም የማይስቡ ሰዎች። እድሎች ይመጣሉ፣ “ላይሳካልኝ ይችላል፣ ገንዘቤን ላጣ እችላለሁ፣ ሰዎች ይሳቁብኛል” የምትል ከሆነ እድሎቹን ትገፋለህ። በህይወት ውስጥ ብዙ ርቀት አትጓዝም፤ ምክንያቱም ወደፊት ለመሄድ የምትፈራ ከሆነ ባለህበት ብቻ ትቆያለህ። አንተ ማግኔት ነህ... ወደፊት እየተጓዝክ መሳብህን ቀጥል!! ድብቁ አእምሮህ ድብቁ ኃይልህ መጽሐፍ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 300+31%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#2280Текст

#ዛሬ_የት_እንዳላችሁ_አትጨነቁ! "... እያንዳንዱ ሳይንቲስት የሆነ ቀን ላይ የሚያለቅስ ህጻን ልጅ ነበር፤ እያንዳንዱ ታላቅ ኪነ ሕንፃም የሆነ ቀን ላይ ባዶ ካርታ ብቻ ነበር።  ዛሬ የት እንዳላችሁ መጨነቁ አስፈላጊ አይደለም ነገር ግን ነገ የት እንደምትደርሱ ማለምና ማስኬድ ላይ ነው ትልቁ ቁም ነገር ያለው። ልብ በሉ አልበርት አንስታይን ሲወለድ ከንፅፅር ፅንሰ ሀሳብ ጋር አልተወለደም፤ አይዛክ ኒውተንም የእንቅስቃሴ ህጎቹን በእናቱ ማህፀን ውስጥ ቀምሮ አልወጣም፤ ዱባይ ውስጥ የሚገኘው ስምንት መቶ ሠላሳ ሜትር ገደማ የሚረዝመው “ቡርጅ ካሊፋ” የተሰኘው የዓለማችን ረዥሙ ኪነ ህንፃም ከሆነ ጊዜ በፊት ሕንፃ ሳይሆን ባዶ ካርታ ብቻ ነበር። ሁሉም ነገር ከባዶ ነው የሚጀምረው። ስለዚህ እናንተም በሙሉ ተስፋ ከጣራችሁ እና ዓላማችሁን ለማሳካት ቁርጠኛ ከሆናችሁ ከምንም እና ከየትም ተነስታችሁ የስኬትን ጫፍ መቆናጠጥ ትችላላችሁ” በማለት ሰሎሞን ተሰናብቷቸው ከክፍሉ ራመድ ራመድ ብሎ ወጣ። #ከስሙር_መጽሐፍ_የተቀነጨበ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 510+52%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
#2279Текст

የራስህ ስኬት ሰለባ ነህ! ጆርጅ ኦርዌል፣ “አንድ ሰው አፍንጫው ስር ያለውን ነገር ለማየት የማያቋርጥ ትግል ይጠይቃል፡፡” ይላል። እውነት ነው። እኛም የጭንቀቶቻችን እና የውጥረቶቻችን መፍትሄ ያለው አፍንጫችን ስር ሆኖ እኛ ግን መፍትሄ የማይሆኑ ማሽኖቻችን ላይ እንጣዳለን። ከዚያ  የራቁት ምስሎችንና ማስታወቂያዎችን በማየት ተጠምደን፣ በስፖርት የተገነባ ሰውነት ኖሮን በጣም ከምታምር አማላይ ሴት ጋር ተያይዘን መዞር የማንችለው ለምን እንደሆነ እናስባለን፡፡ ስለ “የመጀመሪያው ዓለም ችግሮች” እንቀልዳለን፣ ነገር ግን የራሳችን ስኬት ሰለባ ሆነናል። ባለፉት ሰላሳ አመታት ውስጥ ከውጥረት ጋር የተያያዙ የጤና ጉዳዮች፣ የጭንቀት፣ የድብርት ችግሮች ጨምረዋል። ምንም እንኳን ሁሉም ሰው ፍላት ስክሪን ቲቪ ያለው እና የገዛውን ዕቃ ቤቱ ድረስ እንዲመጣለት ማዘዝ የሚችል ቢሆንም፣ ባለፉት ሰላሳ አመታት ውስጥ ከውጥረት ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች ቁጥር በሚገርም ፍጥነት አሻቅቧል። በዚህም ምክንያት ችግራችን ቁሳዊ ሳይሆን፣ ህልውና ነው፤ መንፈሳዊ ነው።  ከአሁን በኋላ ስለ ምን ግድ ሊኖረን እንደሚገባን እንኳን እስከማናውቀው ድረስ በጣም ብዙ አስጨናቂ ነገሮች እና በጣም ብዙ እድሎች ያሉን ሆነናል። እኛ ግን በብዛት ከብዙ እድሎች ይልቅ ብዙ አስጨናቂ ነገሮችን እንመርጣለን፡፡ በዚያ ፈንታ እንዴት ብዙ እድሎችን እንምረጥ? join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 600+61%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#2278Текст
Просмотры2 040+105%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#2277Текст

እውነታን አምኖ የመቀበል (acceptance) አስፈላጊነት! አንዳንድ ሰዎች የተነሳሳና ስኬታማ ሕይወት ማለት ያሉበትን አስቸጋሪ ሁኔታ እንደሌለ መካድ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ አመለካከት ጊዜያዊ የሆነ “ደህና” የመሆን ስሜት ቢሰጠንም የችግራችንን ስር መሰረቱን ግን አይፈታውም፡፡  •  ያላችሁበትን ደስ የማይል የስሜት ሁኔታ አትካዱት፣ ነገር ግን ከሁኔታው ልትወጡ እንደምትችሉ ተስፋችሁን አትጣሉ፡፡ •  ያላችሁበትን የኢኮኖሚ ትግል አትካዱት፣ ነገር ግን ለውጥ ለማምጣት አቅዱና ስሩ፡፡ •  ያላችሁበትን በተለያዩ ምርጫዎች መካከል የመወላወል ሁኔታ አትካዱት፣ ያሏችሁን ምርጫዎች በትኖ በማየትና ምክር በመቀበል መወሰን ላይ ስሩ፡፡ •  አጠገባችሁ ካሉ ሰዎች ጋር አብሮ የመቀጠልን አስቸጋሪነት አትካዱት፣ ራሳችሁን በመለወጥና አቅማችሁን በማዳበር ግን አልፋችሁት መሄድ ላይ ስሩ፡፡ ያላችሁበትን ሁኔታ መቀበል ማለት ለሆነው፣ በመሆን ላይ ላለውና ወደፊትም ለሚሆነው ነገር ሃላፊነትን መውሰድ ማለት ነው፡፡ ይህ ሃላፊነት የመውሰድ ልምምድ ምንም አይነት መፍትሄ ለማምጣት የመጀመሪያው ደረጃ እና መነሻው ነው፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 840+85%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#2276Текст

አንድን ነገር አስር ሺህ ጊዜ! ሆንግኮንግ/አሜሪካዊው ብሩስ ሊ (Bruce Lee) ታዋቂ አክተር፣ ብቁ የማርሻል አርት ባለሞያና አስተማሪ፣ እንዲሁም ስመ-ጥር ፈላስፋ ነበር፡፡ ይህ ሰው አንድ ጊዜ ስለስኬቱ ምስጢር እንዲህ ሲል ተደመጠ፣ “አስር ሺህ አይነት የተለያዩ የካራቴ ምቶችን በአንድ ቀን ከተለማመደ ሰው ይልቅ እኔ የምፈራው አንድን አይነት የካራቴ ምት አስር ሺህ ጊዜ ደጋግሞ የተለማመደን ሰው ነው”፡፡ አንድ ቀን ተነስተን የተለያዩ ነገሮችን ስለሞከርን የትም እንደማንደርስ አመልካች የሆነ ሃሳብ ነው፡፡ አስር ሺ አይነት ነገሮችን ከመሞካከር፣ ዓላማችንንና ግባችንን ከለየን በኋላ ያንን አንድን ነገር አስር ሺህ ጊዜ አድምተን ብንደጋግመውና ብንለማመደው ለምነገባበት ስኬት ወሰን አይኖረውም፡፡ የዚህ እውነታ ምስጢር ያለው በመነሳሳት (Motivation) እና በዲሲፕሊን (Discipline) መካከል ያለውን ልዩነት ነው፡፡ የተነሳሳን አንድ ቀን ከምናደርጋቸው አስር ሺህ የዘመቻ ስራዎች ይልቅ የያዝነውን አንድ ነገር በዲሲፕሊን አስር ሺህ ጊዜ ብንደጋግመው የተሻለ ውጤትን እናገኛል፡፡ በመነሳሳት (Motivation) እና በዲሲፕሊን (Discipline) መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግለን አንድ ነገር ቢኖር መመሪያ (Instruction) የተሰኘው ነገር ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ከአንዱ የመነሳሳትና የመነቃቃት (Motivation) ስብሰባ ወደሌላኛው ሲዳክሩ ከርመው አሁንም እዚያው እንደረገጡ የሚቀሩት፣ ከተነሳሱና ከተነቃቁ በኋላ በቂ መመሪያዎችንና መርሆችን ስለማያገኙና በዚያ ላይ በዲሲፕሊን ደጋግመው ስማይሰሩ ነው፡፡ በመነሳሳት የጀመርነውን አንድ ነገር መመሪያ አግኝተንበት በዲሲፕሊን መቀጠልን እስከምንለምድ ድረስ ስኬት የህልም እንጀራ እንደሆነ ይቀራል፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры2 170+118%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#2275Текст

እንደገና የመኖር እድል ባገኝ! አንድ የሚከተሉትን የእድሜ ደረጃዎች ያለፈ ሰው ሁሉንም ነገር መለስ ብሎ ካሰበ በኋላ እንደዚህ አለ፡- በ18 አመታችን ላይ ሁሉም ሰው አይኖቹ በእኛ ላይ እንዳለና ስለእኛ ብቻ የሚያስብ እየመሰለን እንጨነቃለን፡፡ አሁን ሳስበው፣ እንደገና የመኖር እድሉን ባገኝ፣ ሰዎች ስለእኔ ከሚያስቡት ነገር ይልቅ የበለጠ ተጽእኖ ያለው እኔው በራሴ ላይ ያለኝን አመለካከትና የወደፊት ዓላማዬን በሚገባ የመለየቴ ጉዳይ እንደሆነ በማሰብ በእሱ ላይ እሰራ ነበር፡፡ በ40 አመታችን ላይ ቀስ በቀስ ስለእኛ ማንም ሰው ምንም ነገር አሰበም አላሰበም ግድ ወደማይሰጠን አመለካከት መለስ እንላለን፡፡ አሁን ሳስበው፣ እንደገና የመኖር እድሉን ባገኝ፣ ስለሰው ግድ የለኝም በሚለው አመለካከት ተጋርጄ የተጽእኖ ሰው ከመሆን እንዳልገታ በወጣትነቴ ወደማወቅ በመጣሁት ማንነቴና ዓላማዬ ላይ በመገንባት የተጽእኖ ሰው እሆን ነበር፡፡   በ60 አመታችን ላይ ማንም ሰው ስለእኛ አስቦም ሆነ ትዝ ብሎትም እንደማያውቅ ወደማስተዋል ስለምንመጣ በሌለ ነገር ስንወዛገብ እንደኖርን በማሰብ ወደመራራነት እንወርዳለን፡፡ አሁን ሳስበው፣ እንደገና የመኖር እድሉን ባገኝ ሰዎች በእኔ ላይ የሚያስቡትና እኔው ራሴ በራሴ ላይ የማሰበው ነገር ሲታረቅና በሚዛናዊነት ሲያዝ ብቻ እኔም አርፌ፣ ለሌላውም ተርፌ መኖር እንደምችል በመገንዘብ ሚዛናዊ ሕይወት እኖር ነበር፡፡ ይህ ሰው ከራሱ ልምምድ አንጻርና በራሱ እይታ የነገረን ነገር ለሁላችንም ተመሳሳይ የሆነ ተግባራዊነት ሊኖረውም ሆነ ላይኖረው ቢችልም፣ ከምልከታው ግን በየእድሜ ደረጃችን ቅድሚያ ልንሰጣቸውና አስታርቀን በሚዛናዊነት ልንይዛቸው ስለሚገቡን ነገሮች ያስታውሱናል፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 850+86%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#2274Текст

ከጥቃቅንና ደቃቃ አመለካከት መውጣት! ከጥቃቅንና ከደቃቃ ነገሮችና አመለካከቶች እስምትወጡ ድረስ ወደ ትልልቅና የላቀ ነገር ውስጥ መግባት ያስቸግራችኋል፡፡ በየእለቱ የምታስቧቸውን፣ የምትናገሯቸውንና ራሳችሁን በጣልቃ-ገብነት የምታገኙበትን ሁኔታዎች ተመልከቷቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ጥቃቅን ከሆኑና ከአጠቃላይ የሕይወታች ዓላማና አቅጣጫ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ከሆኑ የወደፊታችሁ እጅጉን አሳሳቢ እንደሆነ ላስታውሳችሁ፡፡ በየእለቱ ማን ምን እንዳደረገ፣ ማን ከማን ጋር እንደታየ፣ ማን ከማን ጋር እንደ ተወዳጀና እደተፋቀረ፣ ማን ስለማን ምን እንዳሰበና እንደተናገረ፣ ማን ምን እንደገዛ፣ ማን ምን እንደለበሰ . . . ጥቃቅንና ደቃቃ አመለካከት ያለውን ሰው አእምሮና ንግግር ይዞና ወጥሮ የሚውለው ነገር ብዙ ነው፡፡ የወደፊት ሕይወታችሁ ትልቅ፣ የላቀና የማትጸጸቱበት እንዲሆን ከፈለጋችሁ ከእንደዚህ አይነት አናሳ አመለካከቶች መውጣት የግድ ነው፡፡ •  ዓላማችሁንና እቅዶቻችሁን ተለቅ አድርጓቸው፡፡ •  ለትልቁ ዓላማችሁ የሚመጥኑ መጻህፍትን አንብቡ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎችን ተከታተሉ፡፡ •  ለትልቁ ዓላማችሁ የሚመጥኑ፣ እነሱም ትልልቅ ነገር የሚያልሙና የሚያወሩ ጓደኞች ላይ አተኩሩ፡፡ •  ጥቃቅን፣ ደቃቃ እና ዛሬ ተወርቶና ተደርጎ ለነገ ከማይሻገር ነገር ቀስ በቀስ ራሳችሁን አርቁ፡፡ •  የምታወሯቸው፣ የምታደርጓቸውና ጊዜያችሁን የምታውሉባቸው ነገሮች ወይ ለእናንተ ወይም ለሌሎች ሰዎች እድገትና ጥቅም የመዋሉን ጉዳይ ማሰብ ልምዳችሁ አድርጉ፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 960+97%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#2273Текст
Просмотры2 150+116%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#2272Текст

የራሳችን ሩጫ እና ግብ ጉዳይ! የራስን ግብ ከሌላው ሰው ግብ ጋር ማስተያየት ኋላ ቀርነትን ያስከትላል! የሌሎች ሰዎች እይታ፣ ፍላጎት፣ የውስጥ ግለትና ሌሎች ወሳኝ ነገሮች ከእኛ እጅግ ያነሱ ሆነው ከተገኙ በዚያ ሰው ገደብ እኛም ተገደብን ማለት ነው፡፡ የራስን ጤንነት ከሌላው ሰው ጤንነት አንጻር መመዘን እንዴት አደገኛ ነገር ነው! አልጋው ላይ ተኝቶ ሞቱን የሚጠብቀውን ሰው አይተን ቆመን መሄዳችንን እንደ ሙሉ ጤንነት ከቆጠርከው አደገኛ ንጽጽር ውስጥ ነው ያለነው (ስለዚያ ሰው የማዘናችንና እኛም ስላለንበት የተሻለ ሁኔታ ሊኖረን የሚገባ ፈጣሪን አመስጋኝነት እንደተጠበቀ ሆኖ)፡፡ የራስን ደረጃ ሌላው ሰው ከደረሰበት ደረጃ አንጻር ብቻ መመዘን ኋላ ቀርነትን ያስከትላል! ስኬታማና መስመር ውስጥ የገባ ሕይወት የመመዘኛችን ሁኔታ አንጻራዊ ሲሆን እጅግ አደገኛ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ የራሴን ደረጃ ከገባኝ ነገርና ካወጣሁት ግብ አንጻር ሳይሆን ሌላው ሰው ካለበት ሁኔታ ጋር ብቻ ካነጻጸርኩት ያለሁበትንና የምሄድበትን የማላውቅ ግራ የተጋባሁ ሰው ነኝ፡፡ ትኩረቴን የሳበው እኔ ወዳየሁትና “መድረስ አለብኝ” ወዳልኩት ከፍታ የመገስገሴ ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ ማን ምን ደረጃ ደረሰ የሚለው ጉዳይ ከሆነ ከወዲሁ የተሸነፍኩ ሰው ነኝ፡፡ የሌላውን ሰው ልህቀት ለእኛ እንደመነሳሳሻ እንጂ የወደፊ እምቅ ብቃታችን መመዘኛ አናድርገው፡፡ የሌላውን ሰው ኋላ ቀርነት ለእኛ መማሪያ እንጂ ባለንበት ደረጃ የመርኪያ ምክንያት አናድርገው፡፡  አቻችን ነው ብለን በምናስበው ሰው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያለን አመለካከት ስላስቀመጥነው ግብና መድረስ ስለምንችልበት ደረጃ ብዙ እንደሚያወራ አንዘንጋ፡፡ የራሳችንን ራእይ፣ ዓላማ፣ ግብና ደረጃ እናውጣና በዚያ ልክ እንሩጥ!!! join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры2 090+110%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#2271Текст

መስቀለኛው መንገድ “መስቀለኛ መንገድ ላይ ደረስኩ፣ መሄድ የምችለው በአንዱ መንገድ ላይ ብቻ ነው፡፡ ቆም ብዬ አሰብኩና ብዙ ሰዎች ያልሄዱበትን መንገድ መረጥኩ፡፡ የታሪኬ ታላቅ ነገር የጀመረው ያን ጊዜ ነበር” - Robert Frost ሁል ጊዜ መስቀለኛ መንገድ በፊትህ ይመጣል፡፡ በፊትህ ከሚጋረጡት መንገዶች መካከል አንዱ ቀላልና ብዙዎች የሄዱበት እንደሆነ ያስታውቃል፡፡ የተመነጠረና የብዙ ሰዎችን ኮቴ የያዘ መንገድ ነው፡፡ ሁለተኛው መንገድ ግን ከዚህ በፊት ብዘዎች እንዳልሄዱበት የሚያሳብቅ ጭር ያለ፣ ገና ያልተመነጠረና ያልተጠረገ መንገድ ነው፡፡ የምትመርጠው መንገድ ወሳኝ ነው፡፡ ብዙዎች የሄዱበትን መንገድ ስትመርጥ ብዙዎች የደረሱበት ፍጻሜ ላይ ትደርሳለህ፡፡ የዚህ ጎዳና ጥቅሙ ከዚህ በፊት ተሞክሮ ያለቀለት የመሆኑና ከስጋት ውጪ የሚመስል መሆኑ ነው፡፡ የዚህ ጎዳና ጉዳቱ ደግሞ ከአንተ ሁኔታ፣ ብቃት፣ ራእይና ከሰባት ቢልየን ሕዝብ ለየት የማለትህ ማንነት አንጻር ሌሎች ልትሄድባቸው ከምትችላቸው አዳዲስ ጎዳናዎች የመግታቱ ጉዳይ ነው፡፡ ብዙዎች ያልሄዱበትን መንገድ ስትሄድ ደግሞ ብዙዎች ያልደረሱበት አዲስ ፍጻሜ ላይ ትደርሳለህ፡፡ ይህኛው ጎዳና ምንም እንኳን ስጋት የሞላበት፣ ዝነኛ ያልሆነና እርግጠኝነት የማጣት ስሜት የሚሰጥ ጎዳና ቢሆንም፣ ለራስህና ለሕብረተሰብህ አዲስን ነገር የምታስተዋውቅበት፣ ከተርታው መንደር የምትወጣበትና ለሰዎች ጥቅም ቦግ ብለህ የምትታይበት (Shine የምታደርግበት) መንገድ ነው፡፡ •  ሌላ የላቀ መንገድ እየታየህ ሁሉም የሄደበትን ተራ መንገድ አትምረጥ፡፡ •  ሌላ የተሻለ ነገር በውስጥህ እያለ የተለመደውን እቅድ አታውጣ፡፡ •  ሌላ የላቀ መልእክት በውስጥህ እያለህ ሁሉም የሚያወራውን ተራ ወሬ አታውራ፡፡ •  አዳዲስ የግኝት እንቁዎች በውስጥህ አምቀህ ይዘህ ምንም ጥረት የማይጠይቀውንና በየመንገዱ የሚገኘውን ጠጠር ስትለቅም አትዋል፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры2 110+112%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#2270Текст

#ይገርማል! 🎆 በአንድ ወቅት፤ አንድ እጅግ ሀብታም የሆነ ሰአሊ በአንዲት ትንሽዬ መንደር ውስጥ ይኖር ነበር። እጅግ ማራኪ ስእሎችን በውድ ዋጋ በመሸጥም ነበር የሚተዳደረው። ታዲያ በመንደሯ የሚኖሩ ድሀ ሰዎች እጅግ ይጠሉት እና ስግብግብ እንደሆነ ያሙታል። 🎆 ወደ ቤቱም በመሄድ ''አንተ ብዙ ገንዘብ ያለህ ሰው ነህ። ነገር ግን በመንደሯ ያሉትን ድሆች አትደግፍም። ስጋ የሚሸጠውን ሰው ብትመለከት ያንተን ያህል ሃብታም አይደለም። ነገር ግን ከሚሸጠው ስጋ ላይ ለድሆች ያካፍላል። የመንደሩ ሰዎችም ይወዱታል። እንዲሁም ዳቦ ሻጩን ተመልከት እሱም ድሀ ሲሆን ብዙ ቤተሰቦች አሉት። ነገር ግን ለድሆች በነጻ ዳቦ ይሰጣል። አንተ ለምን በዚህ ልክ ስግብግብ ትሆናለህ?'' አሉት። ሰአሊውም ለወቀሳቸው መልስ ሳይሰጥ ሁሌም በፈገግታ ይመልሳቸው ነበር። 🎆 የመንደሯ ነዋሪዎችም የሰአሊው ፈገግታ ግራ ያጋባቸው ነበር። በዚህም ራስ ወዳድ እና ሀብት በመሰብሰብ ብቻ የተጠመደ ስግብግብ አድርገው ይቆጥሩት ነበር። አንድ ቀንም ሀብታሙ ሰአሊ በጠና ታመመ ነገር ግን አንድም የመንደሯ ኗሪ ሊጠይቀው ወይም ሊረዳው አልመጣም። ስለዚህ ብቻውን የሚኖረው ሰአሊ ህይወቱ ያልፋል። 🎆 ከዚያም በኋላ ስጋ-ሻጩ እና ዳቦ-ጋጋሪው ለመንደሩ ይሰጡት የነበረውን ስጋ እና ዳቦ መስጠት ያቆማሉ። ስለዚህ የመንደሩ ድሆች ለምን እርዳታቸውን እንዳቆሙ በሀዘን ተሞልተው ይጠይቃሉ። 🎆 ሁለቱም ከዚህ በፊት ወር እስከ ወር ለሚሰጧቸው ስጋ እና ዳቦ ህይወቱ ያለፈው ሰአሊ ሰው ይከፍላቸው እንደነበር እንዲሁም አሁን  ያ ሰው ስለሞተ ለስጋም ሆነ ለዳቦ ዋጋ የሚከፍላቸው እንደሌለ ይነግሯቸዋል። በዚህም የመንደሩ ኗሪዎች ይጠሉት እና ስግብግብ እያሉ ያሙት የነበረው ሰአሊ ይረዳቸው እንደነበር ይገነዘባሉ። ☑️ቁምነገሩ~ ሰዎችን በውጫዊ ገጽታቸው እና ስለ እነሱ በሚወራው አሉባልታ ልንገምታቸው አይገባም። እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች የሚያደርጉትን መልካም ነገር በግልጽ ማሳየት አይፈልጉም ማለት ክፉ ናቸው ማለት አይደለም። መልካምነት ራስ ጋር የሚቆይ ሰላም ነውና። join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры2 030+104%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#2269Текст

#ደስታ_የሚመጣው_ችግሮችን_በመፍታት_ነው በሕይወት ውስጥ ሁልጊዜም ችግሮች አሉ፡፡ አንድ ነገር ለማድረግ ስትሞክር ሌሎች ችግሮች መፈጠራቸው አይቀርም። ለምሳሌ፣ የጤና ችግርህን ስፖርት በመስራት ልትፈታው ስትወስን ጂም በጊዜ ለመድረስ በጊዜ መነሳት፣ በጣም እንዲያልብህ በርትተህ መስራትና ወደ ስራ ስትገባ በመጥፎ ጠረን ቢሮውን እንዳትበክል የግድ መታጠብ ስለሚያስፈልግህ ሌላ አዳዲስ ችግሮች ትፈጥራለህ፡፡ ከሴት ጓደኛህ ጋር በቂ ጊዜ ያለማሳለፍ ችግርህን ለመቅረፍ ማክሰኞ ምሽትን ሁልጊዜ የምትገናኙበት ጊዜ አድርገህ ስትመርጥ ሁለታችሁም እንዳይሰለቻችሁ ለማድረግና አሪፍ ራት መብላት ስላለባችሁ በዚያ ቀን የግድ በቂ ገንዘብ የመፈለግ ችግር ትፈጥራለህ፡፡ ችግሮች ይለዋወጣሉ ወይም ይሻሻላሉ እንጂ አይቆሙም፡፡ ደስታ የሚመጣው ችግሮችን ከመፍታት ነው፡፡ በእዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ ቁልፍ የሆነው ቃል “መፍታት” የሚለው ነው፡፡ ችግሮችንህ ችላ ካልክ ወይም ችግሮች እንደሌሉብህ የሚሰማህ ከሆነ፣ ራስህን በጣም አሳዛኝ እያደረግክ ነው፡፡ መፍታት የማትችለው ችግር እንዳለብህ የሚሰማህ ከሆነም አሁንም ራስህን በጣም አሳዛኝ እያደረግክ ነው፡፡ ምክንያቱም የደስታ ሚስጥራዊ ቅመም ያለው ችግሮችን መፍታት ላይ እንጂ ችግሮች የሌሉብህ መሆን ላይ አይደለም፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 970+98%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#2268Текст

#ህልመኛ_እና_እብድ_ሁን! ዴል ካርኒጌ እንዳለው ''ለሰው ልጅ አስቸጋሪ ወይም መጥፎ ጊዜ የሚባለው፣ አንድ ሰው የተሻለ አቅም እንዳለው አውቆ ነገር ግን አጠቃቀሙን ሳያውቅ ሲቀር ነው። '' ይሄን ከራስህ ህይወት ጋር አያይዘህ አስበው... የህይወትህ የመጨረሻ ቀን ላይ እንዳለህ ሲሰማህ እና ደግሞ ማድረግ የነበረብህን አሁን ልታደርገው እንደማትችል ስታውቅ። ያኔ ልታደርገው ያልቻልክበት ምክንያት ጓደኞችህ ሀሳብህን ሰምተው እንደ #እብድ ስለቆጠሩህ ይሆን? ቤተሰቦችህን ህልምህን አውቀው ''እሺ ህልመኛው ' እያሉ #ስላፌዙብህ ይሆን? የህይወትህ የመጨረሻ ቀን ላይ ይሄ ሁሉ የሰዎች ማጣጣል ምንም ሆኖ ቁጭት ከሚሆንብህ በፊት፣ አሁን #እብድ እና #ህልመኛ ተብለህ ውስጥህ ያለውን ልዩ አቅም እንዴት መጠቀም እንዳለብህ ብታውቅ ስኬታማ ትሆናለህ። አስታውስ የሚወቅሱህ፣ አይሆንም የሚሉህ ሰዎች እንደማይሆንልህ የሚያሳይ ማስረጃ የላቸውም። ማስፈራሪያቸውን ከምትሰማ ተግባራዊ ሆነህ ውጤትህን እንድታይ እመክርሃለሁ። ምንጊዜም የተሻለ የህይወት ደረጃን ስትመለከት እንዲህ አይነቶችን የፈተና መንገዶች ማቋረጥ ግድ ይልሃል። join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры2 070+108%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#2267Текст

በጎ አድራጎት የሕይወት ዘይቤ ሲሆን! አንዲት ሴት በመንገድ ላይ ተቀምጦ እንቁላል የሚሸጥን ሰው አገኘችና፣ “ዋጋው ስንት ነው አለችው፡፡ አንዱን በ50 ሳንቲም (የ Dollar ግማሽ) ነው የምሸጠው” ብሎ መለሰላት፡፡ እሷም፣ “ስድስቱን እንቁላል በሁለት Dollar ከሸጥክ ልግዛህ፣ አለዚያ ትቼህ መሄዴ ነው” አለችው፡፡ የመንገድ ላይ ሻጪውም፣ “ከነጋ ምንም ስላልሸጥኩኝና ገንዘቡን ለህልውናዬ ስለምፈልገው በፈለግሺው ዋጋ ግዢኝ” አላት፡፡ ሁለት Dollar ከፍላ ስድስቱን እንቁላል ይዛ በአሸናፊነት ስሜት ሄደች፡፡ ይህች ሴት በዚያው ቀን ከሰዓት በኋላ ከአንድ ጓደኛዋ ጋር አንድ ያማረ ሬስቶራንት ሄዱና ምግብ በማዘዝ የተወሰነውን በልተው ብዙ ተረፋቸው፡፡ በመጨረሻም፣ ሂሳብ ሲመጣ ዋጋው 150 Dollar ነበር፡፡ ሴትዬዋም 200 Dollar ሰጥታው የሬስቶራንቱን ባለቤት መልሱን ለቲፕ እንዲያስቀረው ነገረችው፡፡ የዚህ ታሪክ ጸሃፊ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፡ “ከችግረኞችና አቅም ከሌላቸው ስንገዛ የበላይነትን የምናሳየው፣ ጨከን የምንለውና እስከመጨረሻዋ ሳንቲም ድረስ የምንከራከረው፣ የእኛ ልግስና ለማያስፈልጋቸው ደግሞ ካለልክ ልግስናችንን ለማሳየት የምንሞክረውና ብዙ ገንዘብ የምንረጨው ለምንድን ነው?” ጸሃፊው፣ ከዚህች ሴት በተቃራኒ፣ አንድን ነገር ከአንድ ችግረኛ ሻጭ ሲገዛ ከተጠየቀው ዋጋ በላይ የከፈለን ሰው አጭር ታሪክም ያጋራል፡፡ ልጆቹ ያደረገውን አይተው፣ “አባ፣ ለምንድን ከተጠየከው መጠን በላይ የከፈልከው?” ብለው ሲጠይቁት፣ “ይህ አይነቱ በጎ አድራጎት የሕይወት ዘይቤዬ ነው” ብሎ መለሰላቸው፡፡ በጎ አድራጎት የታይታ ሳይሆን የሕይወት ዘይቤ ሲሆን! join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book

Открыть в Telegram
Просмотры1 950+96%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—